ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የ2016 ዓ.ም የአገር-አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና በመጀመሪያ ዙር የሚፈተኑ በቁጥር 6175 የሚሆኑ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎችን ከቀን 30/10/2016 ዓ.ም ጀምሮ በመቀበል ላይ ይገኛል፡፡ ዉድ ተማሪዎቻችን እንኳን ወደ ነገዉ ዩኒቨርሲቲያችሁ በሠላም መጣችሁ እያልን በዩኒቨርሲቲያችን ዉስጥ መልካም የቆይታ እና የፈተና ጊዜ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን፡፡
Author: Site Admin
ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ በ2016 የትምህርት ዘመን ለአቅም ማሻሻያ/ Remedial Program የተመደቡ ተማሪዎችን እየተቀበለ ይገኛል፤
ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም ለአቅም ማሻሻያ/Remedial Program የተመደቡ ተማሪዎችን እየተቀበለ ይገኛል፤ በቅበላ ስነ-ስርዓቱ ላይ የዩኒቨርሲቲውን ፕሬዝዳንት ዶ/ር ድሪባ ኢትቻን ጨምሮ የቢዝነስና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዮናስ ከፍያለው፣ የቀበሌ አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ተገኝተዋል። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ድሪባ አዲስ ገቢ ተማሪዎችን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የሚኖራቸው ቆይታ የተሳካና የፈተና ውጤታቸውም ያማረ እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል። ዩኒቨርሲቲው የተመደቡለትን 2067 ተማሪዎች እስከ ነገ ጥር 10/2016 ዓ.ም ድረስ ይቀበላል። ከፍተኛ አመራሮቹ ከአቀባበል በኋላ አዲስ ስራ የጀመረውን የተማሪዎች መመገቢያ አዳራሽም ጎብኝተዋል።