Gambella University held a thank-you program for the former President and Vice Presidents of the University; November 9/2016 Gambella University held a thank-you program for the former President and Vice Presidents of the University. The ceremony was held at the Giwa Hotel, and the president of the university, Dr. Diriba Eticha, who spoke at the ceremony, said, “It should be a tradition to honor and thank people when they step down.” The former senior leaders said that they will still contribute to the development of the university and thanked the new leadership for the ceremony. Finally, they were presented with a certificate from the new president of the university, Dr. Diriba Eticha.
Category: Events
የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና አካዳሚክ ሠራተኞች ለአገር መከላከያ ሠራዊት የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ ።
ህዳር 09/2013 ዓ.ም ጋምቤላ-ኢትዮጵያ የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳርና አካዳሚክ ሠራተኞች በዛሬው ዕለት ህዳር 09/2020 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ በመሰብሰ በሰሜኑ የሐገራችን ክፍል የህግ የበላይነትን ለማስከበር መስዋዕትነት እየከፈለ ለሚገኘው የሐገር መከላከያ ሠራዊት ከወር ደሞወዛቸው የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ተስማምተዋል። Click here for more…የዩኒቨርሲቲው ሠራተኞች የገንዘብ ድጋፍ ያደረጉት በአመራር ደረጃ የሚገኙና አመራር ደረጃ ባልሆኑ የአስተዳደር ሠራተኛና በመምህርነት ደረጃ ተብሎ ለሁለት በመክፍል ነው ። በአመራር ደረጃ ያልሆኑ የአስተዳደር ሠራተኞችና መምህራን ከወር ደሞዛቸው 10% ለጀግናው የሐገር መከላከያ ሠራዊት ለመስጠት የተስማሙ ሲሆን በከፍተኛ፣ መካከለኛና ዝቅተኛ አመራር ደረጃዎች የሚገኙ ሠራተኞች ደግሞ 20% ከወር ደሞወዛቸው ለመስጠት ቃል ገብተዋል ። በፍላጎትም ማንኛውም ግለሰብ ከወር ደሞወዙ የፈለገውን ያክል መለገስ የሚችል መሆኑን በስብሰባው ላይ ተጠቅሷል ። በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲው እንደ አንድ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም የሚጠበቅበትን ለመወጣት ለሐገር መከላከያ ሠራዊት የሚሆን 1ሚሊዬን ብር ድጋፍ ማድረጉን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡጅሉ ኡኮክ የገለፁ ሲሆን ከራሳቸው የወር ደሞወዝ 40 % ለመስጠትም በመድረኩ ፊት ቃል ገብተዋል ።
ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ክብር እቆማለሁ መርሃ ግብር በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ተካሔደ ።
ህዳር 08/2013 ዓ.ም ጋምቤላ- ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት ህዳር 8 ቀን 2013 ዓ.ም ከረፋዱ 5፡ 30 ላይ በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ “ለሐገር መከላከያ ሠራዊት ክብር እቆማለሁ!” መርሃ ግብር ለአንድ ደቂቃ ያክል ቀኝ እጅን ግራ ደረት ላይ በማሳረፍና ለአንድ ደቂቃ በማጨብጨብ ሥነ -ሥርዓቱ ተካሔዷል ። click Gambella University በሥነ -ሥርዓቱ ላይ አራቱም የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንቶችና ሠራተኞች የተገኙ ሲሆን ዓላማውም ግንባር ላይ ፣ ለሀገር ሉዓላዊነትና የህግ የበላይነትን ለማስከበር በተሠማራበት ሁሉ ከፍተኛ ድል እያስመዘገበ ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሰራዊት በክብር መቆማቸውን ለማሳየት ነው ። ክብርና ሞገስ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት!!