ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ለ6ኛ ጊዜ አስመረቀ፡፡

ጥር 23/2013 ዓ.ም ጋምቤላ – ኢትዮጵያ ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌን ጨምሮ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ  የመንገዶች ፈንድ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተርና የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ክቡር አቶ ረሽድ መሀመድ፣ የጋምቤላ ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር ክቡር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ፣ የክልሉ ም/ርዕሰ መስተዳደርና ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ታንኳይ ጆክ፣ የጋምቤላ ሕ/ብ/ክ/መንግስት ም/ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ ክቡር አቶ ጁል ናንጋል፣ የጋምቤላ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊና የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ስራ አመራር ቦርድ ም/ሰብሳቢ ክቡር አቶ ላክደር ላክባክ እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡጁሉ ኡኮክ፣ ም/ፕሬዚዳንቶች፣ የሴኔት አባላት፣ ዲኖች፣ ዳይሬክተሮች ፣ የትምህርት ክፍል ኃላፊዎችና አስተባባሪዎች በተገኙበት ጥር 23/2013 ዓ.ም በመደበኛውና በእረፍት ቀናት  በመጀመሪያና በሁተኛ ዲግሪ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን  ተማሪዎች ለ6ኛ ጊዜ አስመርቋል፡፡ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡጁሉ ኡኮክ ዩኒቨርሲቲው በ27 የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውና ሴኔቱ ያጸደቀላቸው በቅድመ-ምረቃ በመደበኛው ወንድ 596 ሴት 389 ድምር 985 በእረፍት ቀናት ወንድ 169 ሴት 30 ድምር 199  በድህረ-ምረቃ ወንድ 40 ሴት 5 ድምር 45 በጠቅላላው 1 ሺህ 229 ተማሪዎችን አስመርቋል ብለዋል፡፡ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ኢትዮጵያ በቀጣይ ዓመታት ሰላም፣ ልማትና ብልጽግና የሰፈነባት ሆና እንድትቀጥል እያንዳንዱ ሰው በእኩልነትና በወንድማማችንት መንፈስ ተጋግዞ ሀገራችን ከእያንዳንዳችን የምትፈልገውን ኢትዮጵያዊ ጨዋነትን፣ የስራ ትጋትን፣ የሙያ ክብርንና ለህዝቦቿ የላቀ ፍቅርን ካሳየን ለዓለም የምትተርፍ ባለብዙ ፀጋ ሀገር መሆኗን ተናግረዋል፡፡ Read More …