መግቢያ
- የሀገራችን ርዕይ “በህዝብ ተሳትፎና መፈቃቀድ ላይ የተመሠረተ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትና መልካም አስተዳደር የሰፈነባት ፣ የማህበራዊ ፍትህ የነገሰባት ፣ ከድህነት ተላቅቃ መካከለኛ ገቢ ያላት ኢትዮጵያን እውን ማድረግ ነው፡፡
- ይህንንም ርዕይ ለማሳካት የተለያዩ የዕድገት አማራጮችን በመጠቀም ህዝቦቿን ከድህነት እና ከኋላ ቀርነት ለማላቀቅ ጥረት እያደረገች ትገኛለች” (የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የመን/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት,2008 ዓ.ም) ፡፡
- እድገቱ ማህበራዊ ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ እምርታዎችን ማዕከል ባደረገ መልኩ የተቀረፀ ሲሆን በሁሉም መስክ አጥጋቢ ውጤት ተመዝግቧል ለማለት ይቻላል፡፡
- በተጨማሪም ፍትሐዊ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተደራሽነትን ከማስፋፋት ጎን ለጎን የትምህርት ጥራትና አግባብነትን ለማረጋገጥ እንዲቻል ከተለያዩ ባለድርሻ አካላትና የልማት አጋር ድርጅቶች ጋር በመቀናጀት ዘርፈ-ብዙ ተግባራት በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡
- የቴክኖሎጂ ሽግግርና እምርታዊ የኢኮኖሚ ዕድገት ለመገንባት ካለው ጽኑ ፍላጎት በመነሣት የመጀመሪያውን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ /GTP-I/ በመንደፍ ወሳኝ የዕድገት መሠረቶችን በመጣል ተጨባጭ ውጤቶችን ለማስመዝገብ የተቻለ ሲሆን የልማቱን ቀጣይነት ለማረጋገጥ የተዘጋጀውን የ2ኛውን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ /GTP- II / በስኬት ያጠናቀቅንበት ጊዜ ላይ እንገኛለን፡፡
- በዚህም መሠረት የዩኒቨርሲቲዎችን ጥቅል የቅበላ አቅማቸውን በማሳደግ የሰለጠነ የሰው ኃይልን ከአገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት ፍላጎት ጋር ለማጣጣም እንዲቻል በመቱ ዩኒቨርስቲ ሥር በጋምቤላ የግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ፋካልቲ ከ2005 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በአራት ዲፓርትመንቶች ሲሰራ ቆይቶ በሚያዝያ 28 ቀን 2006 ዓ.ም የመሠረት ድንጋይ ተጥሎ በሚኒስትሮች ምክር ቤት በደንብ ቁጥር 317/06 ተቋቁሞ ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ተገቢዉን ሃላፊነት እየተወጣ ይገኛል ፡፡
- ዩኒቨርሲቲው በ2007 ዓ.ም በ2 ፋካሊቲ በ13 ትምህርት ክፍሎች 947 ተማሪዎችን ፣ በ2008 ዓ.ም በ4 ፋካሊቲ በ18 ትምህርት ክፍሎች 1,668 ተማሪዎችን በመቀበል እና በመቱ ዩኒቨርሲቲ ስር ከነበሩት በመደበኛው መርሃ-ግብር 243 በእረፍት ቀናትና በክረምት መርሃ-ግብር 73 በድምሩ 316 ተማሪዎችን ለመጀመሪያ ጊዜ ለማስመረቅ ችሏል ፡፡
- በ2009 ዓ.ም በ5 ፋካሊቲ በ27 ትምህርት ክፍሎች 2,176 ተማሪዎችን በመቀበል በመደበኛው መርሃ-ግብር 425 ፣ በእረፍት ቀናትና በክረምት መርሃ-ግብር 52 በድምሩ 477 ተማሪዎችን ለማስመረቅ ችሏል፡፡
- በ2010 ዓ.ም በ1 ኮሌጅ በ4 ፋካሊቲ በ2 ትምህርት ቤቶች እና በ31 ትምህርት ክፍሎች 3,978 ተማሪዎችን በመቀበል በመደበኛው 730 በእረፍት ቀናት እና በክረምቱ መርሃ-ግብር 354 በድምሩ 1,084 ተማሪዎችን አስመርቋል ፡፡
- በ2011 ዓ.ም በ2 ኮሌጅ በ3 ፋካሊቲ በ2 ትምህርት ቤቶች እና በ31 ትምህርት ክፍሎች 5,015 በቅድመ ምረቃ 330 በድህረ-ምረቃ ፕሮግራም በድምሩ 5,345 ተማሪዎችን በመቀበል በመደበኛ መርሃ-ግብር 557 በእረፍት ቀናት 264 በክረምት መረሃ ግብር 79 በድምሩ 900 በሁለተኛ ዲግሪ በእረፍት ቀናት መርሃ-ግብር 49 ተማሪዎች በጠቅላላ 949 ተማሪዎች አስመርቋል ፡፡
- በ2012 ዓ.ም በ2 ኮሌጅ በ3 ፋካሊቲ በ2 ትምህርት ቤቶች እና በ31 ትምህርት ክፍሎች በቅድመ ምረቃ በመደበኛው 7,712 ፣ በድህረ ምረቃ ፕሮግራም 450 በጠቅላላ ዩኒቨርሲቲው የቅበላ አቅሙን 8,162 ማድረስ ችሏል ፡፡
- ከዚሁ በመነሳት ዩኒቨርሲቲው የ2013 በጀት ዓመት ዕቅድ በማዘጋጀት ወደ ስራ በመግባት በአራቱም ፕሮግራሞች ማለትም፡- በአስተዳደር ፣ በመማር ማስተማር ፣ በጥናትና ምርምር እና በማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፎች የ1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ከዚህ በታች እንደሚከተለዉ ቀርቧል፡፡
- በ2013 ዓ.ም የአገልግሎት አድማሱን በማስፋት በሴኔት ይሁንታ ባገኘባቸው ተጨማሪ 3 ትምህርት ክፍሎች፣ 3 የድህረ ምረቃ መስኮች እንዲሁም በአሁን ሰዓት አገልግሎት እየሰጠባቸው በሚገኙ 31 ትምህርት ክፍሎች 2,309 ነባር መደበኛ ተማሪዎች፣ 1,700 አዲስ ገቢ ተማሪዎች፣150 የድሕረ ምረቃ ተማሪዎች፣ 36 የዳግም ቅበላ ተጠቃሚ መደበኛ ተማሪዎች በድምሩ 4,195 የመደበኛ መርሀ ግብር ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ተዘጋጅቶ የነበረ
- በአለም አቀፍ ደረጃ በተንሰራፋው ኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ዕቅዱን በመከለስ በ2012 ዓ.ም 2ኛ ሰምስተር ላይ ተቋርጦ የነበረውን የገፅ ለገፅ ትምህርት መልሶ ለማስጀመር በ3 ምዕራፎች በመከፋፈል በመጀመሪያው ምዕራፍ 1,027 ዕጩ ምሩቃንን ለማስተናገድ ዝግጁትን አጠናቋል፡፡
- ከዚሁ በመነሳት ዩኒቨርሲቲዉ የበጀት ዓመቱን ዕቅድ በማዘጋጀት ወደ ስራ በመግባት በአራቱም ዘርፎች ማለትም ፡- በመማር ማስተማር፣ በጥናትና ምርምር፣ ማኅበረሰብ አገልግሎት እና በአስተዳደር ዘርፎች የ1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ከዚህ በታች እንደሚከተለዉ ቀርቧል፡፡
- ከ2012 በጀት ዓመት አጋማሽ ጀምሮ የኮቪድ 19 ፓንደሚክ ስርጭት ለመግታት መንግስት በወሰነዉ መሠረት ዩኒቨርሲቲዉ ለኳራንታይን (ለወረርሽኙ ተጠርጣሪዎች ማቆያና መታከሚያ) ሆኖ እስከ መስከረም 2013 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ ሲያገለግል ቆይቷል፡፡
- ይሁን እንጂ ዓለም አቀፍ የጤና ተቋምና የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር ኅብረተሰቡ ስለ ኮቪድ 19 በቅ ግንዛቤ በማግኘቱና የበሽታዉ ባሕሪ ራስን በመጠበቅ በጥንቃቄ የዕለት ተዕለት ተግባሮችን ማከናወን የሚያግድ ያለመሆኑን ተረጋግጧል፡፡
- ለአብነት የግቢ ጽዳት ማድረግ፣ የመማሪያ ክፍሎች ማጽዳትና ማስተካከል፤ ተማሪዎች የሚሆን ቀለብ መግዛት፣ የኮቪድ 19 መከላከያ የሚሆን የአፍ ጭምብልና ሳኒታይዘር መግዛት፣ የመታጠቢያ ገንዳዎችና የዉሃ ሮቶዎችን ማሟላት፣ ለሠራተኞች ፣ ለአከባቢዉ ማኅበረሰብ፣ ለኃይማኖት አባቶችና ታዋቂ ግለሰቦች የመማር ማስተማሩን ስራ ምቹና ሰላማዊ ለማድረግ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠት…ወዘተ ተከናዉኗል፡፡
ክፍል አንድ
1. የዩኒቨርሲቲው ተልዕኮ ፣ ርዕይ እና እሴቶች
1.1. ርዕይ
- ብቁ ባለሙያና ተመራማሪ ዜጋ በማፍራት በ2022 ዓ.ም በአፍሪካ ደረጃ ታዋቂ የጥናትና ምርምር ማዕከል መሆን ፤
1.2. ተልዕኮ
- ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ጥራትና አግባብነት ያለው ትምህርትና ስልጠና በመስጠት በዕውቀት ፣ በክህሎትና በመልካም ስነ-ምግባር የታነጹ ዜጎችን በማፍራት ፤ እንዲሁም ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በማስተዋወቅና በማስረጽ ለአካባቢውና ለሀገሪቱ ልማት ጉልህ አስተዋጽኦ የሚያደርግ ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምር ማካሄድ ነው፡
1.3. እሴቶች ፤
- ብዝሃነትና አሳታፊነት ፤
- ታማኝነት ፤
- እኩልነት ፤
- ዉጤታማነት ፤
- የትምህርት ነፃነት ፤
- ልህቀት ፤
1.4. የዩኒቨርሲቲዉ መሪ ቃል
- ከማህበረሰቡ ጋር ነን !
ክፍል ሁለት
2. በዝግጅት ምዕራፍ የተከናወኑ ተግባራት፤
2.1. በዩኒቨርሲቲው የሥራ አመራር ቦርድ የተከናወኑ ተግባራት
- የ2012 ዓ.ም ዕቅድ አፈፃፀምን በመገምገም ለቀጣይ በጀት ዓመት መነሻ የሚሆኑ በጥንካሬና በድክመት የታዩ ነጥቦች ተለይተው ለቀጣይ በጀት ዓመት ግብዓት እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡
- በ2013 ዓ.ም ዕቅድ አዘገጃጀትና አተገባበር ዙሪያ ከዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች ጋር በጥልቀት በመወያየትና በመገምገም ዕቅዱ እንዲዳብር ተደርጓል፡፡
2.2. በዩኒቨርሲቲው ደረጃ የተከናወኑ ተግባራት ፤
2.2.1. ከዕቅድ ዝግጅት አንፃር፡-
- የ2012 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀምን በመገምገም ጠንካራ ጎኖች እንዲጎለብቱና ክፍተቶቹን በግብዓትነት በመጠቀም የ2013 ዓ.ም መሪ ዕቅድ ተዘጋጅቷል ፤
- ከዘርፎች ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ በመነሳት የፈጻሚዎች የአፈጻጸም ግምገማ ተካሂዷል፣
- የ2013 በጀት ዓመት ዕቅድ ማስፈጸሚያ የሚሆን ለመደበኛ ስራዎች ብር 207,744,411.00 (ሁለት መቶ ሰባት ሚሊዮን ሰባት መቶ አርባ አራት ሺህ አራት መቶ አስራ አንድ ብር)፣ ለካፒታል ፕሮጀክቶች ብር 550,000,000.00 (አምስት መቶ አምሳ ሚሊዮን ብር) በድምሩ ብር 757,744,411.00 (ሰባት መቶ አምሳ ሰባት ሚሊዮን ሰባት መቶ አርባ አራት ሺህ አራት መቶ አስራ አንድ ብር) ጸድቋል፡
- ከመንግስት ግምጃ ቤት 199,445,131.00 (አንድ መቶ ዘጠና ዘጠኝ ሚሊዮን አራት መቶ አርባ አምስት ሺህ አንድ መቶ ሰላሳ አንድ ብር) ሲሆን ከዉስጥ ገቢ ብር 8,299,280.00 (ስምንት ሚሊዮን ሁለት መቶ ዘጠና ዘጠኝ ሺህ ሁለት መቶ ሰማንያ ብር) ነዉ፡፡
2.2.2. በዩኒቨርሲቲው ሥር በሚገኙ የሥራ ዘርፎች
2.2.2.1 በመማር ማስተማር ዘርፍ፡-
- የ2012 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀምን በመገምገም የትምህርት ክፍሎች ለ2013 በጀት ዓመት መነሻ የሚሆኑ ነጥቦች ተለይቷል፤
- በ2013 ዓ.ም የሚሰጡ ኮርሶች ከተለዩ በኋላ የመምህራንን ድልድል በማድረግ መምህር ላልተገኘላቸው ኮርሶች በወቅቱ ቅጥር ተካሂዷል፤
- የትምህርት ክፍሎችን የቅበላ አቅም ያገናዘበ ለመማር ማስተማር የሚያገለግሉ ግብዓቶችን የማሟላት ሥራ ተሰርቷል፤
2.2.2.2. በጥናትና ምርምር ዘርፍ፡–
2.2.2.3. በማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ፡–
2.2.2.4. በአስተዳደር ዘርፍ፡–
- የኮቪድ- 19 ታማሚዎች ስታከሙበት የነበሩ መኝታ ክፍሎች በሙሉ በጤና ቢሮ አማይካይነት በኬሚካል ሪጭት ተደርጎላቸዋል፤
- በመኝታ ክፍሎች ዙሪያ ያሉ ሣሮች ጸድቷል፡፡
- ለኮቪድ- 19 ቅድመ መከላከል አገልግሎት የሚዉሉ ክፍሎች ተለይቶ ተዘጋጅቶዋል፤
- ለተማሪዎች መጠጥ ውሀ አገልግሎት የሚውል 2 አዲስ ባለ 10,000 ሺህ ሮቶ አገልግሎት እንዲሰጥ ተደርጓል፤
- በምግብ ማከማቻ መጋዝን ዉስጥ እህል እንዳይበላሽ 70 ጣውላዎችና 120 ሞራሌ ተገዝቶ የእህል ማስቀመጫ ተሠርቷል፤
- በኮቪድ-19 ፕሮቶኮል መሠረት የተማሪዎች መመገቢያ አዳራሽ ውስጥ የተማሪዎች መቀመጫ ተራርቀዉ እንዲቀመጡ በቀለም የመለየት ስራ ተሰርቷል፤
- ለቅድመ ዝግጅት ስራ የመጡ 14 የተማሪዎች ሕብረት ኮሚቴ አባላት የምግብ አገልግሎት በማግኘት ላይ ይገኛሉ፤
- የኮቨድ-19 ስርጭት ለመከላከል መሰለፊያ ቦታ ተማሪዎች ርቀታቸውን ጠብቀው እንዲሰለፉ በቁጥር የመለየት ስራ ተሠርቷል፤
- ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጠቋሚ ዕቅድ በመነሳት የተቋሙ ዕቅድ ተዘጋጅቶ ከዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ጋር በመወያየት እንዲዳብር ተደርጓል፤
- የተማሪዎችን የመኝታ ፣ የምግብ ፣ የሕክምና ፣ የመፀዳጃ ቤቶችን ንፅሕና ለመጠበቅ የሚያስችል ዝግጅት ተደርጓል፤
- ክፍተት ባለባቸው የስራ ክፍሎች የሰው ኃይል የማሟላት ሥራ ተሰርቷል ፤
- የተማሪዎችን ቅበላ በሚመለከት ኮሚቴ ተቋቁሞ ከአከባቢው ማህበረሰብ ፣ ከሀገር ሽማግሌዎች ፣ ከሀይማኖት አባቶችና ከጽጥታ አካላት ጋር ዉይይት ተደርጓል ፤
ክፍል ሶስት
3.1 ቁልፍ ተግባራት /የተቋማዊ ለውጥ ሥራዎች አፈፃፀም በተመለከተ፡-
- በ2 መድረኮች የዩኒቨርሲቲዉ ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች፣ ዳይሬክተሮች፣ ዲኖች፣ አስተባባሪዎች፣ ቡድን መሪዎች እንዲሁም የትምህርት ክፍል ኃላፊዎች የስራ አፈጻጸም ግምገማ ተካሄዷል፤
3.2 የመደበኛ ስራዎች (ውጤት ተኮር) የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት፤
ዕይታ 1፡- ተገልጋይ
ግብ 1፡- የደንበኞችና ባለድርሻ አካላት ዕርካታን ማሳደግ፤
- ምክንያቶች የመመረቂያ ጽሁፍ ያላቀረቡ የሁለተኛ ባች ድህረ ምረቃ ተማሪዎች እንዲያቀርቡ ጥሪ ከተደረገላቸዉ መካከል አምስት ተማሪዎች የመመረቂያ ጹሑፋቸዉን ገቢ አድርገዋል፡፡ ከሦስተኛ ባች 44 ተማሪዎች የመመረቂያ ፕሮፖዛሎቻቸው በተጋባዥ ገምጋሚዎች (External Evaluator) እንዲገመገምላቸዉ ገቢ አድርገዋል፤
ሰንጠረዥ 1. የ2012 ዓ.ም የእረፍት ቀናት መርሀ–ግብር ምሩቃን ዝርዝር ሁኔታ መግለጫ
ተ.ቁ | የትምህርት መስክ | የተመረቁ ተማሪዎች | ድምር | |
ሀ. | በመጀመሪያ ዲግሪ | ወንድ | ሴት | |
Biology | 24 | 0 | 24 | |
Accounting and Finance | 29 | 12 | 41 | |
Economics | 21 | 4 | 25 | |
Logistics and Supply Chain Mgmt. | 19 | 0 | 19 | |
Management | 22 | 8 | 30 | |
Gender and Development Study | 16 | 4 | 20 | |
Public Administration and Dev’t Mgmt. | 21 | 1 | 22 | |
ንዑስ ድምር | 152 | 29 | 181 | |
ለ. | በ2ኛ ዲግሪ | ወንድ | ሴት | ድምር |
Business Administration | 9 | 3 | 12 | |
Development Study | 18 | 1 | 19 | |
Project Planning and Management | 11 | 0 | 11 | |
ንዑስ ድምር | 38 | 4 | 42 | |
ጠቅላላ ድምር | 190 | 33 | 223 |
- በጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት ስር ሶስት አስተባባሪዎች ተመድበዋል፤
- ለመዉጫ ፈተናው የሚቀመጡ የ5ኛ ዓመት የህግ ተማሪዎች ስም ዝርዝር ወደ ሀገር አቀፍ ፈተናዎችና ምዘናና ኤጄንሲ እና ለኢ.ፌ.ዲ.ሪ የህግ፤ የፍትህ፤ የሥልጠና እና የምርምር ኢንስቲትዩት ተልኳል፤
- በግል የመዉጫ ፈተና በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ለመውሰድ ላመለከቱ ተማሪዎች ጥሪ በማድረግ ከመደበኛ ተማሪዎች ጋር የመውጫ ፈተናውን የሚወስዱበት ሁኔታ ተመቻችቷል፤
- ተቋሙ በሚያካሄዳቸዉ ስራዎች ላይ በመሳተፍ መረጃዎችን በፎቶግራፍና በጽሁፍ በመያዝ ተደራሽ እንዲሆን ተደርጓል፤
- በአዲሱ የመምህራን መኖሪያ ሕንፃ ፣ በተማሪዎች መኝታ ቤት እና በመማሪያ ክፍሎች ዙሪያ የምንጣሮ የመሬት መደልደል ሥራ ተካሂዷል፤
- በግቢ ውስጥ ለተተከሉት ችግኞች በሽቦ የመከለል ሥራ ተሰርቷል፤
- በቤተ-መፅሐፍት ጀርባና መማሪያ ክፍሎች አካባቢ ያሉት የኮንክሪት መቀመጫዎች በቀለም እንዲዋቡ ተደርገዋል፤
- ከዋና በር እስክ ተማሪዎች ዶርም ያለው አስፋልት ግራና ቀኝ በቀለም ተውበዋል፤
- ሰባት ሽንት ቤቶች ተመጥጧል፤
- በኮምፒዩተር ላቦራቶሪ ውስጥ ያሉ ዘጠና ዴስክቶፕ ኮምፕዩተሮች ለተማሪዎች መማሪያ ዝግጁ እንዲሆን ተደርገዋል፤
- ይህም ከታቀደው በአንደኛ ሩብ ዓመት 22% መከናወኑን ያመለክታል፤
ግብ 2፡- የደንበኞችንና የባለ ድርሻ አካላትን ቁጥር መጨመር፤
- የድህረ ምረቃ ትምህርት ፈላጊዎች ፍላጎትን መሰረት ባደረገ በማስታወቂያ በመጋበዝ ተደራሽ በማድረግ አጥጋቢ ቁጥር ያለው አመልካች ተገኝቷል፣
- በመደበኛዉ መርሃ-ግብር የድህረ-ምረቃ ተማሪዎችን ለመቀበል አስፈላጊ ዝግጅት ተደርጎ በእንስሳት እርባታ ትምህርት ምዝገባ እየተካሄደ ነዉ፤
- ከመንግስት መ/ቤቶች ጋር በምርምር ዘርፍ ትስስር ለመፍጠር ከጋምቤላ ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ጋር “የዓሳ ሃብት ልማት ቴክኖሎጂ ፕሮጀክት (Fish Resource Development Technology Project) በሚል ርእስ ዩኒቨርሲቲዉ እንዲያስተባበር የዉል ስምምነት ተፈራርመዋል፤
- ከጋምቤላ ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የSocio-economic Data ጥናት ለማድረግ መምህራን ንድፈ ሃሰቡን እንዲያዘጋጁ ተደርጓል፤
- በኢትዮጵያ በወሰን አስተዳድርና ማንነት በኩል በክልሉ የሚገኙ ወረዳዎች ጥናት ለማስጠናት በጠየቀው መሰረት ተመራማሪዎች ለጥናቱ የሚሆን ንድፈ ሃሳብ አዘጋጅተው ለጠያቂው መ/ቤት ተልኳል፤
- በምርምር ፖሊሲና መመሪያ መሰረት በፋካሊቲ፣ በኮሌጅና በትምህርት ቤት የምርምርና ማህበረሰብ ካዎንሲል ኮሚቴ በአዲስ መልክ ተደራጅቷል፤
- በዩኒቨርሲቲው የኢንዱስትሪ ትስስር መመሪያ ሰነድ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል፤
- ስምንት የዉጭ ሀገር መምህራን ከሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሥራ ፍቃድ እንዲያገኙ ተደርጓል፤
- በዩኒቨርሲቲውና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጋምቤላ ሀገረ ስብከት ተክለኃይማኖት ገዳም ጋር የድንበር ወሰን ስምምነት ተደርጓል፤
- ይህም ከታቀደው በአንደኛ ሩብ ዓመት 21.25% መከናወኑን ያመለክታል፡፡
ዕይታ 2፡- ፋይናንስ
ግብ 3፡- የሀብት አጠቃቀም ውጤታማነትን ማሻሻል፣
ሀ. መደበኛ በጀት አፈፃፀም ፤
- በአስተዳደር የተሰጠ ድጋፍና አገልግሎት ለዓመቱ ከተመደበው ብር 51,197,814.00 / አምሳ አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ዘጠና ሰባት ሺህ ስምንት መቶ አስራ አራት/ ብር ውስጥ በአንደኛ ሩብ ዓመት ብር 11,516,413.00 /አስራ አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ አስራ ስድስት ሺህ አራት መቶ አስራ ሶስት/ ብር ወጪ ሲሆን 22.5% የተጠቀምን መሆኑን ያመለክታል ፤
- ለተማሪዎች አገልግሎት ለዓመቱ ከተመደበው ብር 32,661,880.00 ሰላሳ ሁለት ሚሊዮንስድስት መቶ ስድሳ አንድ ሺህ ስምንት መቶ ሰማኒያ/ ብር ውስጥ በአንደኛ ሩብ ዓመት 1,043,991.00/ አንድ ሚሊዮን አርባ ሶስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና አንድ/ ብር ወጪ ሲሆን 3.20% የተጠቀምን መሆኑን ያመለክታል፤
- ለመማር ማስተማር አገልግሎት ለዓመቱ ከተመደበው ብር 112,393,927.00 /አንድ መቶ አስራ ሁለት ሚሊዮን ሶስት መቶ ዘጠና ሶስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሃያ ሰባት/ ብር በዘጠኝ ወር ውስጥ ብር 24,290,731.00 / ሃያ አራት ሚሊዮን ሁለት መቶ ዘጠና ሺህ ሰባት መቶ ሰላሳ አንድ/ ብር ወጪ ሲሆን 21.6% የተጠቀምን መሆኑን ያመለክታል፤
- በጥናትና ምርምር ዘርፍ ለዓመቱ ከተመደበው ብር 7,580,070.00/ ሰባት ሚሊዮን አምስት መቶ ሰማንያ ሺህ ሰባ / ብር ስሆን በአንደኛ ሩብ ወጪ ያልወጣ መሆኑን ያመለክታል፤
- በማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ ለዓመቱ ከተመደበው ብር 2,505,420.00 /ሁለት ሚሊዮን አምስት መቶ አምስት ሺህ አራት መቶ ሃያ/ ብር በአንደኛ ሩብ አመት ብር 85,300.00 /ሰማኒያ አምስት ሺህ ሶስት መቶ / ብር ወጪ ሲሆን 3.4% የተጠቀምን መሆኑን ያመለክታል፤
- በዩኒቨርሲቲ ኢንዱስቲሪ ትስስር አገልግሎት ዘርፍ ለዓመቱ ከተመደበው ብር 1,405,300.00/ አንድ ሚሊዮን አራት መቶ አምስት ሺህ ሶስት መቶ / ብር ሲሆን በአንደኛ ሩብ ወጪ ያልወጣ መሆኑን ያመለክታል፤
ሀ. መደበኛ በጀት
ፕሮግራሞች | የዓመቱ በጀት | የ1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ | የ1ኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸም | ልዩነት | የሩብ ኣመቱ በመቶኛ | የዓመቱ በመቶኛ | ||
ስራ አመራርና አስተዳደር | 51,197,814.00 | 12,000,814.00 | 11,516,413.00 | 484,401 | 96% | 22.49% | ||
መማር ማስተማር እና ተማሪዎች አገልግሎት | 145,055,807.00 | 32,556,000.00 | 25,334,722.00 | 7,221,278 | 78% | 17.47% | ||
ጥናትና ምርምር | 7,580,070.00 | 2,000,000.00 | – | 2,000,000 | 0% | 0.00% | ||
ማህሰ/አገ/ አጫጭር ስልጠናዎች | 2,505,420.00 | 520,000.00 | 85,300.00 | 434,700 | 16% | 3.40% | ||
ማህሰ/አገ/ ቴክኖሎጂ ሽግግር | 1,405,300.00 | 250,000.00 | – | 250,000 | 0% | 0.00% | ||
ድምር | 207,744,411.00 | 47,326,814.00 | 36,936,435.00 | 10,390,379.00 | 38% | 17.78% | ||
- ከ2008 አስከ 2012 ዓ/ም የነበሩ የኦዲት ግኝቶች ምላሽ ተሰጥቷል፤
- ለ34 የ5ኛ ዓመት የሕግ ተማሪዎች መውጫ ፈተና (Exit Exam) ላይ እንዲቀመጡ ለእያንዳንዱ ተማሪ ብር 664.00 (ስድስት መቶ ስልሳ አራት ብር) በጠቅላላው ብር 22,576.00 / ሃያ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ስባ ስድስት ብር/ ለሀገር አቀፍ ፈተናዎች ድርጅት ገቢ ተደርጓል፤
- 10 ሺህ ሊትር ነዳጅ በብር 195,000.00 በመግዛት አገልግሎት ላይ እንዲውል ተደርጓል፤
- ካሉት 25 መኪናዎች ዉስጥ አምስት ለጥገና ወደ ጋራዥ የገቡ ፣ 14 በሥራ ላይ ያሉ ስሆን አንዱ በብልሽት የቆመ እና አምስት የሚወገዱ ናቸዉ፤
- በመደበኛ በጀት የክዋኔ ኦዲት የ2012 በጀት ዓመት የ4ኛ ሩብ ዓመት የአጠቃላይ ሪፖርት ቀርቧል፡፡
- የ2011 እና 2012 በጀት ዓመት በዋና ኦዲተር መ/ቤት ከገንዘብ ሚኒስቴር የተጠየቁ የኦዲት ግኝት ላይ ማስተካከያ ተደረጓል፤
- ከገንዘብ ሚኒስቴር ተፈቅዶ የመጣ ገንዘብ በመንግስት ፋይናንስ አዋጆች ደንቦችና መመሪያዎች መሠረት ሥራ ላይ መዋሉን በሂሳብ ምርመራ ተራጋግጧል፤
- በግንባታ ሥራ ላይ የተሰማሩ የህንፃ ተቋራጮች ያስያዙት የባንክ ዋስትና ወቅታዊነቱ ተራጋግጧል፤
- የ2012 በጀት ዓመት የሳጥንና የንብረት ቆጠራ ተደርጓል፤
- በእያንዳንዱ የሥራ ክፍል የ2013 ዓመት የግዥ ፍላጎት ዕቅድ እንዲያቀርቡ ተደርገዋል፤
- በወቅቱ የገበያ ጥናት በማድረግ አስቸከኳይ ግዥ አስፈላጊ በሆነበት ወቅት የግዥ ፕርፎርማ የማሰባሰብ ስራ ተሰርቷል፤
- ቋሚ እቃዎች በዋጋ ማቅረቢያ እና በቀጥታ ግዥ ዘዴ ተገዝተው ገቢ እየተደረጉ ይገኛሉ፤
- አላቂ እቃዎችን በዋጋ ማቅረቢያ እና ቀጥታ የግዥ ዘዴ ተገዝተው ገቢ ሲሆን ተጫራቾች ባሸነፉት የዕቃ አይነት ሳይሆን ተመሳሳይ ስላቀረቡ እንዲቀይሩ በመደረጉ ምክንያት ያልገቡና በሂደት ላይ ያሉ ይገኛሉ፤
- ለአስቸኳይ የግንባታ ጥገና የሴራሚክ፤ የኩሽና ስራ ፤ የሰራተኞች ልብስ መቀየሪያ ስራ ፤ የሮቶ ማስቀመጫ ስራዎች በዋጋ ማቅረቢያ የጨረታ ዘዴ መሰረት ያሸነፈዉ ድርጅት በስራ ላይ ይገኛል፤
- ስድስት ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር፣ ሁለት ከክልሉ ጤና ቢሮ በእርዳታ የተበረከተልን እና አስር በግዥ በድምሩ አስራ ስምንት የሙቀት መለኪያ መሳሪያዎች ለኮቪድ 19 ወረርሽን መመርመሪያ አገልግሎት ላይ ዉሏል፤
- በ2012 በጀት ዓመት የተጀመሩ ለተማሪዎች አገልግሎት የሚውል የኩሽና እቃዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ ግልፅ ጨረታ ወጥቶ አሸናፊ የተለየ ቢሆንም በወቅቱ በበጀት ክፍያ መዘግየት ምክንያት በ2013 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት 30% ተከፍሏቸዉ በሂደት ላይ ይገኛል፤
- በ2012 በጀት ዓመት ተጀምሮ የነበረው Installation, integration and Training of integrated Student Information Management System እና implementation and commissioning of one card system and security infrastructure project on turnkey basis የግንባታ ግዥ በ1ኛ ሩብ ዓመት 30% ተከፍሏቸዉ ስራው በሂደት ላይ ይገኛል፤
- በየሎቱ የወጡ የተፈጨ የጤፍ ዱቄትና ደረቅ እንጀራ፣ የጥራጥሬ ምግቦች፤ አትክልት ምግቦች፤ የዳቦ፤ የክርስቲያን እና የሙስሊም ሥጋ ፣ የታሸገ ውሃ ፣ የመጠጥ ውሃ ማመላለሻ ቦቴ ኪራይ ፣ የማገዶ እንጨት፣ የውሃ ማጠራቀሚያ ሮቶ ግዥ እንዲፈጸም በግልፅ ጨረታ ተደርጎ አሸናፊዉ ተለይቶ አቅራቦቱ በሂደት ላይ ይገኛል፤
- የህትመት አገልግሎት ግልፅ ጨረታ ቢወጣም ተጫራች ባለመገኘቱ በውስን ጨረታ ለመግዛት በሂደት ላይ ይገኛል፤
- የማዕቀፍ ግዥ ለመፈፀም ከፌዴራል ግዥ አሰተዳደር ኤጀንሲ ጋር በመቀናጅት ግዥ እንዲከናወን ለመስራት በሂደት ላይ ይገኛል፤
- የተማሪዎች ልብስ ማጠቢያና ሻዎር ቤት፤ጊዜያዊ ደረቅ ሽንት ቤት፤ የዲ ኤስ ቲቪ ቤት፤ አነስተኛ ጋራዥ፣ የአጥር እና የጥበቃ ቤት ታዎር ግንባታ ግልፅ ጨረታ ወጥቶ በግምገማ ሂደት ላይ ይገኛል፤
- ለ17 የዩኒቨርሲቲው የስራ አመራሮች የህግ አስተያየትና የማማከር አገልግሎት ተሰጥቷል፤
- 11 ፍራሾች ከተማሪዎች ዶርም በምሸት ማንነታቸዉ ባልታወቁ ግለሰቦች በመወሰዱ በወቅቱ ተረኛ የነበሩ አራት የጥበቃ ሠራተኞች ኃላፊነታቸዉን ባለመወጣታቸዉ ክስ ተመስርቶባቸዉ በጊዜ ቀጠሮ ወደ ማረሚያ ገብተዋል፤
- አንድ መምህር ከሥራ ያለአግባብ ተባረርኩ ብሎ ወደ ሥራ እንዲመለስና የኋላ ክፊያ እንዲከፈለዉ ለኢፌዲሪ ስቪል ስርቪስ አሰተዳደር ኮሚሸን ፍርድ ቤት ክስ በማቅረቡ ዩኒቨርሲቲ በፍርድ ቤት ያደረገዉ የክርክር ማሰረጃዎች ግልፅ በመሆኑ ለዩኒቨርሲቲ ተወስኗል፤
- የዩኒቨርሲቲውን ጥቅም በሚነካ ሁኔታ ለሚደረጉ የተለያዩ ውሎችና ስምምነቶች አራት ተገቢ ውሎች በማረጋገጥ ወደ ሥራ ተገብቷል፣
- ይህም ከታቀደው በአንደኛ ሩብ ዓመት 22.75% መከናወኑን ያመለክታል፡፡
ግብ 4፡- የውስጥ ገቢ አቅምን ማሳደግ
- በአቦቦ ወረዳ የሚገኘውን የዩንቨርስቲውን የእርሻ ቦታ ህጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ ለመቀበል ከወረዳዉ መስተዳድር ም/ቤት ጋር ውይይት ተደርጓል፤
- ከውስጥ ገቢ ማመንጫ በዓመቱ ይሰበሰባል ተብሎ ከታቀደው ብር 8,299,280 /ስምንት ሚሊዮን ሁለት መቶ ዘጠና ዘጠኝ ሺህ ሁለት መቶ ሰማኒያ ብር/ በአንደኛ ሩብ ዓመት ብር 20,600.00 /ሃያ ሺህ ስድስት መቶ ብር/ ተሰብስቧል፤
- በግቢ ዉስጥ የንግድ ቦታ ተከራይተዉ ከሚሠሩ የአንዱ ነጋዴ ውል ታድሷል፤
- ከGIZ በመተባበር ለስልጠና ማዕከል የሚያገለግልና ለተቋሙ እንደ ገቢ ማመንጫ ማገልገል የሚችል የግብርና ስልጠና ማዕከል ግንባታ እየተከናወነ ይገኛል፤
- ይህም ከታቀደው በአንደኛ ሩብ ዓመት 17.5% መከናወኑን ያመለክታል፡፡
ዕይታ 3፡- የውስጥ አሠራር
ግብ 5፡- የትምህርት ጥራትና አግባብነትን ማሳደግ
ሰንጠረዥ 2. የ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ክራሽ ፕሮግራም መደበኛ ተመራቂ ተማሪዎች ዝርዝር ሁኔታ መግለጫ
S.N | Faculty/College/School | GC List | Entry year | Total | Remark | |
M | F | |||||
A. | School of Law | |||||
1 | Law | 23 | 10 | 2010E.C | 33 | |
B. | College of Agriculture | |||||
1 | Agricultural economics | 36 | 13 | 2010E.C | 49 | |
2 | Animal Production & Technology | 20 | 21 | 2010E.C | 41 | |
3 | Disaster Risk management | 27 | 19 | 2010E.C | 46 | |
4 | NARM | 35 | 15 | 2010E.C | 50 | |
5 | Horticulture | 22 | 21 | 2010E.C | 43 | |
6 | Soil Resource | 24 | 20 | 2010E.C | 44 | |
7 | Plant science | 21 | 23 | 2010E.C | 44 | |
8 | RDAE | 18 | 28 | 2010E.C | 46 | |
9 | Wild life & ecotourism mgt | 21 | 26 | 2010E.C | 47 | |
C. | Faculty of Natural & Computational Sciences | |||||
1 | Biology | 20 | 21 | 2010E.C | 41 | |
2 | Chemistry | 30 | 5 | 2010E.C | 35 | |
3 | Physics | 8 | 17 | 2010E.C | 25 | |
4 | Mathematics | 7 | 22 | 2010E.C | 29 | |
5 | Computer Science | 24 | 11 | 2009E.C | 35 | |
6 | Statistics | 18 | 15 | 2010E.C | 33 |
ሰንጠረዥ 2. የ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ክራሽ ፕሮግራም መደበኛ ተመራቂ ተማሪዎች ዝርዝር ሁኔታ መግለጫ
S.N | Faculty/College/School | GC List | Entry year | Total | Remark | |
M | F | |||||
D. | Faculty of Social Sciences & Humanities | |||||
1 | Gender | 14 | 17 | 2010E.C | 31 | |
2 | English | 17 | 7 | 2010E.C | 24 | |
3 | Psychology | 17 | 10 | 2010E.C | 27 | |
4 | Sociology | 16 | 10 | 2010E.C | 26 | |
E. | Faculty of Bussines & Economics | |||||
1 | Accounting | 30 | 13 | 2010E.C | 43 | |
2 | Cooperative | 22 | 6 | 2010E.C | 28 | |
3 | Economics | 35 | 8 | 2010E.C | 43 | |
4 | Marketing | 18 | 18 | 2010E.C | 36 | |
5 | Logistics | 33 | 10 | 2010E.C | 43 | |
6 | Public | 33 | 9 | 2010E.C | 42 | |
7 | Management | 33 | 10 | 2010E.C | 43 | |
Total | 622 | 405 | 1027 |
ሠንጠረዥ 3: በ2013 ትምህርት ዘመን የመምህራንና ላቦራቶሪ ቴክንሺያን የቅጥር ፍላጎት እና የተቀጠሩ መምህራን ብዛት
ተ.ቁ | ኮሌጅ/ፋካሊቲ/ት/ቤት | ትምህርት ክፍል | የቅጥር ፍላጎት እና የተቀጠሩ መምህራን ብዛት | |||
ላቦራቶሪ ቴክንሺያን | ለክቸረር | |||||
ፍላጎት | የተቀጠሩ | ፍላጎት | የተቀጠሩ | |||
1 | ተፈጥሮ እና ቀመር ሳይንስ ፋካሊቲ | ፊዚክስ | 1 | 1 | 2 | 3 |
ሒሳብ | 0 | 0 | 2 | 1 | ||
ባዮሎጂ | 1 | 1 | 0 | 0 | ||
ኬሚስትሪ | 1 | 1 | 0 | 0 | ||
ኮምፕዉተር ሳይንስ | 0 | 0 | 1 | 0 | ||
2 | ግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ | አደጋ መከላከል እና ዘላቂ ልማት | 0 | 0 | 2 | 2 |
ገጠር ልማትና ግብርና ኤክስቴንሽን | 0 | 0 | 1 | 1 | ||
እንስሳት እርባታና ቴክኖሎጅ | 1 | 1 | 0 | 0 | ||
አፈርና ዉሃ ሀብት ተፋሰስ ማኔጅመንት | 1 | 1 | 0 | 0 | ||
ዕፅዋት ሳይንስ | 1 | 1 | 0 | 0 | ||
ተፈጥሮ ሀብት አያያዝ | 1 | 1 | 0 | 0 | ||
3 | ምህንድስናና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ | ምግብ ምህንድስና | 1 | 1 | 2 | 1 |
ሲቪል ምህንድስና | 1 | 1 | 2 | 2 | ||
ሜካኒካል ምህንድስና | 1 | 1 | 3 | 3 | ||
ዉሃ ሀብት እና መስኖ ምህንድስና | 1 | 1 | 3 | 3 | ||
4 | ማህበራዊ ሳይንስና ሥነ-ሰብ ፋካሊቲ | እንግሊዝኛ | 0 | 0 | 4 | 1 |
ሶሾሎጂ እና ሶሻል አንትሮፖሎጂ | 0 | 0 | 2 | 1 | ||
ስነ-ልቦና | 0 | 0 | 3 | 3 | ||
ጂኦግራፊና ታሪክ | 0 | 0 | 2 | 2 | ||
ስርአተ ጾታ እና ልማት ጥናት | 0 | 0 | 4 | 3 | ||
5 | ቢዝነስና ምጣኔ ሀብት ፋካሊቲ | ማርኬቲንግ ማነጅመንት | 0 | 0 | 2 | 1 |
ኮፕረቲቭ | 0 | 0 | 1 | 0 | ||
6 | ህግ ት/ቤት | ህግ ት/ክፍል | 1 | 0 | 6 | 0 |
ድምር | 12 | 11 | 42 | 27 |
ግብ 6፡- የትምህርት ፍትሃዊነት እና ተደራሽነትን ማሳደግ
- በዩኒቨርሲቲው ቆይታቸው በጥናትና ምርምር ስራዎቻቸው እንዲሁም በማስተማር ስራ ላበረከቱት አስተዋፅኦ በ2013 የትምህርት ዘመን ለሶስት መምህራን የረዳት ፕሮፌሰርነት (Assistant Professor) ማዕረግ ዕድገት ተሰጥቷቸዋል፤
- በ2013 በጀት ዓመት መምህራን የጥናት እና ምርምር ንድፈ ሃሳብ እንዲያቀርቡ ግንዛቤ ተሰጥቷቸዋል፤
- የ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የድህረ ምረቃ ትምህርት ፈላጊዎችን ለመሳብ በግልፅ ማስታወቂያ በመጋበዝ ተደራሽ ተደርጓል፤
- ይህም ከታቀደው በአንደኛ ሩብ ዓመት 23% መከናወኑን ያመለክታል፡፡
ግብ 7፡- የአጋሮችን ተሳትፎ ማሳደግ
- በጋምቤላ ከተማ ውስጥ ከሚገኙት ሰባት መንግሰታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት (plan international, Stempower, GIZ project, Digital Library and Fisher project) የጋራ ስምምነት ሰነድ ተፈርሟል፤
- በዩኒቨርሲቲ ሚኒ-ሙዝየም (culture center) ለመክፈት ከጋምቤላ ክልል ባህልና ቱሪዚም ቢሮ ጋር ለመስራት ፍላጎታችንን በመግለጽ በቢሮው የተዘጋጁ ሰነዶች፣ መጽሄቶች፣ ባህላዊ ቁሳቁሶች፣ አልባሳት እንዲሁም የሙዝየም ምልከታ ተደርጓል፤
- ነጻ የህግ ድጋፍ ፕሮጀክት በዩኒቨርስቲዉ እና UNDP መካከል MOU ከተፈረመ በኋላ በሶስት ወረዳዎች (ጋምቤላ ወረዳ፣ኢታንግ ልዩ ወረዳ፣ ጎግ ወረዳ ) እና በጋምቤላ ከተማ መስተዳድር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ላይ ስራ ተጀምሯል፤
- የመምህራንና ትምህርት ክፍሎች እነዲሁም የተማሪዎችን ግንኙነት ለማጠናከር የተለያዩ የቴለግራም ግሩፖችን በመክፈት ግንኙነቶች እንዲጠናከሩ ተደርጓል፤
- ይህም ከታቀደው በአንደኛ ሩብ ዓመት 23.25% መከናወኑን ያመለክታል፤
ግብ 8፡- የተጠናከረ የጥናትና ምርምር ስራ ማካሄድ
- በጋምቤላ ክልል በአኝዋ ዞንና በኑዌር ዞን በሚገኙ አከባቢዎች በተከሰተው የጎርፍ መጥለቅለቅ የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ 20 ተመራማሪዎች በተጽህኖ ዳሰሳ ጥናት (Impact Assesement Survey) በማድረግ ማህበረሰቡን ከጎርፉ አደጋ ለመታደግ ዘላቂ መፍትሄ በማፈላለግ ላይ ይገኛል፤
- ይህም ከታቀደው በአንደኛ ሩብ ዓመት 16.5% መከናወኑን ያመለክታል፡፡
ግብ 9፡- የተጠናከረ የማህበረሰብ አገልግሎት መስጠት
- በዩኒቨርሲቲው ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደቱን በተሳለጠ መልኩ ለማካሄድ በጋምቤላ ከተማ ከ5ቱም ቀበሌዎች ከተወጣጡ የሃይማኖት አባቶች እና ከሀገር ሽማግሌዎች (12 ሴትና 39 ወንድ በድምሩ 51) ጋር ዉይይት ተደርጓል፤
- ከጋምቤላ ከተማ ከ5ቱም ቀበሌዎች ከተለያዩ ማህበራት የተወጣጡ ወጣቶች ለ25 ሴትና ለ50 ወንድ በድምሩ 75 ወጣቶችን ማወያየት ተችሏል፤
- ከመከላክያ ሰራዊት፤ ከፌድራል ፖሊስ፤ ከፀጥታ እና ደህንነት ቢሮ፤ ከፖሊስ ኮሚሽን፤ ከልዩ ኃይል ፖሊስ፤ ከጋምቤላ ከተማ ፖሊስ ፅ/ቤት ለ11 ሴትና ለ43 ወንድ በደምሩ ከ54 የፀጥታ አካላት ጋር ዉይይት ተደርጓል፤
- በጋምቤላ ከተማ የሚገኙ ትምህረት ቤቶች ጋር ዩኒቨርሲቲዉን ባማከለ መልኩ ለመስራት እስቲም ፓወር ከተባለ የግል ድርጅት 31 ዴስክ ቶፕ 63 አይነት የቤተ-ሙከራ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ርክክብ ተደርጓል፤
- ከኦሮሚያ ክልል ተፈናቅለው ለመጡ 315 ሰዎች የምሳ ግብዣ ለ2 ቀናት እና የመመገቢያ ሳሀን ድጋፍ ተደርጎላቸዋል፤
- ይህም ከታቀደው በአንደኛ ሩብ ዓመት 24.75% መከናወኑን ያመለክታል፤
ግብ 10፡- የቴክኖሎጂ ሽግግር ልማትና የኢንዱስትሪ ትስስርን ማሳደግ
- እሰቲም ከተባለዉ መንግስታዊ ያለሆነ ደርጅት ግንኙነት በመፍጠር 31 ዴስክቶፖች እና 63 የተለያዩ የኤሌክትሮንክስ ዕቃዎች በስጦታ ተገኝቷል፤
- ከባለድርሻ አካላት ጋር ለሚደረገዉ የጋራ ምክክር መድረክ የመግባቢያ ሰነድ ተፈርሟል፤
- ይህም ከታቀደው በአንደኛ ሩብ ዓመት 15 % መከናወኑን ያመለክታል፡፡
ግብ 11፡- ምቹ የስራ ሁኔታን በመፍጠር ተቋማዊ የስራ ባህልን ማጎልበት
- ከክልሉ ጤና ቢሮ ለኮቪድ-19 መከላከያ የሚያገለግሉ አራት በእግር የሚከፈት የቆሻሻ ማጠራቀሚያ በድጋፍ ተገኝቷል፤
- ለመድሀኒት ማስቀመጫ የሚሆን አንድ ፍሪጅ ግዥ ተከናዉኗል፤
- የተሰባበሩ የክሊኒክ ሁለት መስኮቶችና አንድ መግቢያ በር ተጠግኗል፤
- የዩኒቨርሲቲውን ደህንነት ለማሰጠበቅ የደህንነት መቆጣጠሪያ ካሜራ (Security system) ለመዘርጋት በሂደት ላይ ይገኛል፤
- የጥበቃን ስራ ከእጅ ንክኪ ውጪ ለማድረግ የኤሌክትሮኒክ ፍተሻ ስራ ተጀምሯል፤
- ለፋካልቲ ዲኖችና ለትምህርት ክፍል ኃላፊዎች ቢሮዎች እንዲመቻቹ ተደርጓል፤
- 150 ዓመታዊ መጽሄት ለማሳተም መረጃዎችን ከዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በማሰባሰብ እና በማደራጀት ዝግጅታችንን አጠናቀን ለህትመት በዝግጅት ላይ እንገኛለን፤
- ለታካሚ ተማሪዎች ማረፊያ የሚሆን ሶስት አግዳሚ ወንበሮች ለተማሪዎች ክሊኒክ ተገዝተዋል፤
- የትልቁና የመካከለኛ ምግብ ቤት አደራሽ ሙሉ ጥገና እድሳት ተደርጓል፤
- የተበላሹ የ180 የዶርም/ የተማሪዎች ማደሪያ/ በሮችና መስኮቶች ተሰርቷል፤
- ከ1-45 ያለው 7 ብሎክ የቁልፍ ጥገና እንዲሁም የበር ጥገና ተደርጓል፤ በአጠቃላይ 329 ክፍል የበርና የቁልፍ ጥገና ተደርጓል፤
- በምግብ ቤት ዙሪያ የፈሳሽ ማስወገጃ መስመር እንዲፀዳ ተደርጓል፤
- ይህም ከታቀደው በአንደኛ ሩብ ዓመት 21.25% መከናወኑን ያመለክታል፡፡
ግብ 12፡- ተቋማዊ ለውጥና መልካም አስተዳደርን ማጠናከር
- ለተማሪዎች ቀለብ የሚውሉ ግብአቶችን በሚያቀርቡና በተረካቢ መካከል የነበሩ ችግሮችን ለመፍታት ከ37 ወንድና ከ2 ሴት በድምሩ ከ39 ሰዎች ጋር ውይይት በማድረግ የመፍትሄ አቅጣጫ ተሰጥቷል፤
- የመምህራን የመገምገሚያ ቅጽ ወይም ቼክ ሊስት ተዘጋጅቶ የመምህራን ብቃት ምዘና መስፈርቶች (Performance Evaluation criteria or Teacher Assessment) ተዘጋጅቷል፤
- ይህም ከታቀደው በአንደኛ ሩብ ዓመት 19.5 % መከናወኑን ያመለክታል፤
ግብ 13፡- የዘርፈ ብዙ ጉዳዮችን አሰራር ማጎልበት፤
- ለዩኒቨርሲቲዉ አካል ጉዳተኞች ምቹ የስራ አካባቢ ለመፍጠር የአካል ጉዳተኛ መንገድ (Ramp) ለመስራት ቦታዎችን በመለየት ለግንባታ ፕሮጀክቶች ፅ/ቤት ደብዳቤ በመፃፍ ስራዉ ተጀምሯል፤
- UNFPA በክልሉ ኤች አይ ቪ/ኤድስ መ/መ/ ፅ/ቤት በኩል የተለያዩ ቁሳቁስ (ሚክሰር 1፤ሞንታርቦ 1፤43 ኢንች ኮሬኔት ቲቪ 1፤ ቲቪ ስታንድ 1፤ስታብላይዘር 1፤ቬንትሌተር 1 እና ሲዲ 1 ድጋፍ ተደርጎልናል፤
- ይህም በአንደኛ ሩብ ዓመት ከታቀደው 19.5% መከናወኑን ያመለክታል፡፡
ግብ 14፡- የሰው ኃይል ዕውቀት ክህሎትና ተነሳሽነት ብቃትን ማሳደግ
- ተከታታይነት ያለዉ የመምህራን ሙያ ልማት፣ የመምህራን አቅም ግንባታ፣ የማስተማር ስነ ዜደና የኢንግሊዘኛ ቋንቋ ማሻሻል ላይ፡-
- ለ72 መምህራን የከፍተኛ ዲፕሎማ ፕሮግራም (HDP) ስልጠና ተሰጥቷል፤
- ለ27 አዲስ ለተቀጣሩ መምህራን የInduction ስልጠና ተሰጥቷል፤
- የኔትዎርክ መሠረተ ልማት ዝርጋታዉ ተጠናቆ፤ ስራው ለመጀመር ለባለሙያዎች አስፈላጊውን ስልጠና ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት ስራ ተጠናቋል፤
- በሁለተኛ ዲግሪ 27 መምህራን እንዲሁም በመጀመሪያ ዲግሪ ላብ ቴክኒሽያን 11 በድምሩ 38 የአካዳሚክ ሰራተኞች ቅጥር ተፈጽሟል፤
- በሀገር ውስጥ 2ኛ እና 3ኛ ድግሪ እንድማሩ ዕድል ላገኙ መምህራን አስፈላጊዉ ሁሉ ተደርጎላቸዉ ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ መግባት ጀምረዋል፤
- የሬጂስተራርን አሰራር ለማዘመን ለተከታታይ 15 ቀናት ለ16 ባለሙያዎች በዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ስልጠና ተሰጥቷል፤
- አዲስ የተቀጠሩ ሠራተኞች ከነባር ሠራተኞች ጋር ፕሮፋይላቸዉ ተሰርቶላቸዋል፣
- ለ5ኛ ባች ለሚገቡ ተማሪዎች ከአስተዳድር ሠራተኞች በአራት የትምህርት ክፍል የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ ተድርጓል፤
- ይህም ከታቀደው በአንደኛ ሩብ ዓመት 18.44% መከናወኑን ያመለክታል፣
ግብ 15፡- የተቋማዊ ዕድገት የሚያግዙ ግብዓቶችን መሠረተ ልማት ማሳደግ
- መደበኛ የስልክ መስመሮች እና የኢንተርኔት አገልግሎት ስቋረጥ እንዲሰሩ ተደርጓል፤
- በተከለሰው የአካዳሚክ ካለንደር መሠረት የሀገር ውስጥ እና የውጪ ሀገር መምህራን ወደ ስራ ገበታቸው እንዲመለሱ ጥሪ ተደርጓል፤
- 80 ላፕቶፕ፣40 ዲስክቶፕ ኮምፒዉተር ፣ 52 ፕሪንተርና 8 ኮፒ ማሽን ጥገና ተከናውኗል፤
- 4 ቢል ቦርድ፣ 50 የዩኒቨርሲቲው አርማ የያዘ ሲኒ፣ 3 ትልቁና 2 መካከለኛውና 50 ትንሹ የዩኒቨርሲቲው ባንዲራ ለማሳተም ዝግጅቱ ተጠናቋል፤
- ስለ ኮቪድ -19 ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ግንዛቤ ለመስጠት ፖስተሮች፣ ብሮሸሮችና ፍላየሮች በግቢው ውስጥ ተለጥፏል፤
- የተከናወኑ መረጃዎች በአግባቡ በጽሁፍና በፎቶግራፍ ተደራጅተው እንዲቀመጡ ተደርጓል፤
- ወቅታዊ መረጃ ለህብረተሰቡ በሬዲዮና በሶሻል ሚዲያ ተደራሽ ተደርጓል፤
- ይህም ከታቀደው በአንደኛ ሩብ ዓመት 18.44% መከናወኑን ያመለክታል፤
ሠንጠረዥ 4፡- የ2013ዓ/ም አንደኛ ሩብ ዓመት የግንባታ ፕሮጀክት ሪፖርት ማጠቃለያ | ||||||||||||||||||||||
የበጀት ኮድ | የፕሮግራም ፤የፕሮጀክቱ ስም | የተጀመረበት ወርና ዓ/ም | ፕሮጀክቱው የሚጠናቂቀበት ጊዜ | የፕሮጀክቱ ጠቅላላ ወጪ | ሪፖርቱ እሰከ ተደረገ ጊዜ ድርስ የወጣ ወጪ | የ2013 ዓ/ም በጀት ዓመቱ ዕቅድና አፈጻፃም | የ1ኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸም | |||||||||||||||
በውለታ መሠረት ማጠናቂቅ የነበረበት ጊዜ | በተሻሻለው ዕቅድ/Revised Plan/ | በመጀመሪያው ዕቅድ/Orginal Plan/ | በተሻሻለው ዕቅድ/Revised Plan/ | የፈዚካል ሥራዎች ዕቅድ | 2013 የጸደቅለን በጀት | ከ2013 በጀት ላይ የወጣ ወጪ | የፊዚካል ሥራዎች | የ2013 ዓ/ም በጀት | ||||||||||||||
የታቀደ | የተከናወነ | የታቀደ | የተከናወነ | ክንውን በመቶኛ | ||||||||||||||||||
1 | 2 | 3 | 4 | 5 | 6 | 7 | 8 | 9 | 11 | 12 | 13 | 14 | 15 | |||||||||
001 | አይሲቲ ፕሮጀክት | ሐምሌ 21/2012- | ጥር 30/2013 | – | 95,000,000.00 | 95,000,000.00 | 51,183,610.00 | 100% | 35,000,000.00 | 183,610.00 | 100% | 0.19% | 700,000.00 | 183,610.00 | 0.52% | |||||||
002 | የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታ ግንባታ | ህዳር 30/2013 | ሴኔ 25/2014 | – | 90,000,000.00 | 90,000,000.00 | 8,863,684.16 | 100% | 67,958,500.00 | 8,863,684.16 | 100% | 0% | 0.00 | 8,863,684.16 | 13.04% | |||||||
003 | የተማሪዎች መኝታ ቤቶች ግንባታ | ግንቦት 25/2008 | ሰኔ 22/2009 | መጋቢት 9/2013 ዓ/ም | 582,743,490.58 | 688,651,635.37 | 467,614,914.48 | 100% | 116,478,500.00 | 1,663,085.41 | 100% | 80.24% | 49,699,600.00 | 1,663,085.41 | 1.43% | |||||||
004 | የመማሪያ ክፍሎች ግንባታ | ግንቦት 25/2008 | ሰኔ 22/2009 | ጥር/2013 | 211,461,876.08 | 263,590,796.18 | 191,707,982.23 | 100% | 48,400,000.00 | 5,647,273.12 | 100% | 90.66% | 10,500,000.00 | 5,647,273.12 | 11.67% | |||||||
005 | የተማሪዎች መመገቢያ አዳራሽና ኩሽና ግንባታ | ግንቦት 25/2008 | ሰኔ 22/2009 | መጋቢት 9/2013 ዓ/ም | 58,491,901.73 | 78,671,607.83 | 37,557,650.10 | 100% | 32,300,000.00 | 11,324,447.61 | 100% | 64.21% | 14,500,000.00 | 11,324,447.61 | 35.06% | |||||||
006 | ላቦራቶሪ እና ላይብራሪ ግንባታ | ግንቦት 25/2008 | ናሐሴ 28/2009 | ጥር/2013 | 277,111,575.10 | 340,999,482.03 | 322,897,117.30 | 100% | 31,790,000.00 | 0.00 | 100% | 94.69% | 16,500,000.00 | 0.00 | 0.00% | |||||||
007 | የአስተዳደር ህንጻዎችና ቢሮዎች ግንባታ | ግንቦት 25/2008 | ናሐሴ 28/2009 | መጋቢት 9/2013 ዓ/ም | 193,040,488.71 | 221,507,563.48 | 153,671,196.83 | 100% | 36,550,000.00 | 0.00 | 100% | 79.61% | 14,025,500.00 | 0.00 | 0.00% | |||||||
008 | የመሰረተ ልማት ግንባታና ፋሲሊቲዎች ዝርጋታ | ግንቦት 25/2008 | ናሐሴ 28/2009 | ጥር/2013 | 64,839,653.05 | 81,091,233.64 | 58,239,457.43 | 100% | 59,925,000.00 | 2,171,495.18 | 100% | 89.82% | 21,000,000.00 | 2,171,495.18 | 3.62% | |||||||
014 | የዘበኛ ቤት፤የግቢ በርና የአጥር ስራ | ታህሳት 21/2012 ዓ/ም | መጋቢት 9/2012 ዓ/ም | ጥር/2013 | 44,138,708.45 | 44,138,708.45 | 20,718,853.23 | 100% | 27,200,000.00 | 0.00 | 100% | 46.94% | 5,000,000.00 | 0.00 | 0.00% | |||||||
015 | የቤት ውስጥ ሙቀት መቆጣጠሪያ(AC) ግንባታ | ህዳር 25/2013 | መጋቢት 9/2013 ዓ/ም | – | 35,000,000.00 | 35,000,000.00 | 0.00 | 100% | 12,444,000.00 | 0.00 | 100% | 0.00% | 6,000,000.00 | 0.00 | 0.00% | |||||||
የበጀት ኮድ | የፕሮግራም ፤የፕሮጀክቱ ስም | የተጀመረበት ወርና ዓ/ም | ፕሮጀክቱው የሚጠናቂቀበት ጊዜ | የፕሮጀክቱ ጠቅላላ ወጪ | ሪፖርቱ እሰከ ተደረገ ጊዜ ድርስ የወጣ ወጪ | የ2013 ዓ/ም በጀት ዓመቱ ዕቅድና አፈጻፃም | የ1ኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸም | ||||||||||||
በውለታ መሠረት ማጠናቂቅ የነበረበት ጊዜ | በተሻሻለው ዕቅድ/Revised Plan/ | በመጀመሪያው ዕቅድ/Orginal Plan/ | በተሻሻለው ዕቅድ/Revised Plan/ | የፈዚካል ሥራዎች ዕቅድ | 2013 የጸደቅለን በጀት | ከ2013 በጀት ላይ የወጣ ወጪ | የፊዚካል ሥራዎች | የ2013 ዓ/ም በጀት | |||||||||||
የታቀደ | የተከናወነ | የታቀደ | የተከናወነ | ክንውን በመቶኛ | |||||||||||||||
018 | በ2010 የተጀመሩ መሰረተ ልማት ግንባታ | ጥር 30/2013 | ሴኔ 25/2014 | – | 78,000,000.00 | 78,000,000.00 | – | 100% | 36,054,000.00 | 0.00 | 100% | 0.00% | 19,640,000.00 | 0.00 | 0.00% | ||||
023 | የተማሪዎች ክሊነክ ግንባታ | ጥር 30/2013 | ሴኔ 25/2014 | – | 100,000,000.00 | 100,000,000.00 | – | 100% | 39,100,000.00 | 0.00 | 100% | 0.00% | 0.00 | 0.00 | 0.00% | ||||
024 | የተማሪዎች ሸንት ቤቶች ግንባታ | ታህሳት 21/2012 ዓ/ም | መጋቢት 9/2012 ዓ/ም | ጥር/2013 | 2,685,641.38 | 2,750,977.94 | 2,541,220.55 | 100% | 1,700,000.00 | 0.00 | 100% | 94.62% | 600,000.00 | 0.00 | 0.00% | ||||
025 | የተማሪዎች ልብስ ማጠቢያ ግንባታ | ታህሳት 21/2012 ዓ/ም | መጋቢት 9/2012 ዓ/ም | ጥር/2013 | 3,462,520.95 | 4,274,472.85 | 2,860,803.89 | 100% | 1,700,000.00 | 0.00 | 100% | 82.62% | 600,000.00 | 0.00 | 0.00% | ||||
026 | የተማሪዎች ሻዎር ቤት ግንባታ | ሰኔ 27/2011 ዓ/ም | ነሐሴ 3/2011 ዓ/ም | ጥር/2013 | 3,019,256.00 | 3,925,038.00 | 0.00 | 100% | 1,700,000.00 | 0.00 | 100% | 0.00% | 450,000.00 | 0.00 | 0.00% | ||||
027 | የተማሪዎች መዝናኛ ቲቪ አዳራሸ ግንባታ | ሰኔ 27/2011 ዓ/ም | ነሐሴ 3/2011 ዓ/ም | ጥር/2013 | 3,019,256.00 | 3,925,038.00 | 1,911,461.20 | 100% | 1,700,000.00 | 0.00 | 100% | 63.31% | 300,000.00 | 0.00 | 0.00% | ||||
1,842,014,368.02 | 2,131,526,553.77 | 1,319,767,951.40 | 100% | 550,000,000.00 | 29,853,595.48 | 100% | 49.18% | 159,515,100.00 | 29,853,595.48 | 5.43% | |||||||||
ግብ 16፡- የአመራር ፣ አደረጃጀትና አሠራር ሥርዓት ብቃት ማሻሻል፤
- የጨረታ ሂደቶች ደንብ እና መመሪያ መሠረት እንዲከናወን ማድረግ ተችሏል፤
- በፌዴራል ስነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን አዘጋጅነት ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር በነበረዉ የጋራ የምክክር መድረክ ላይ በመሳተፍ ከሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች የአሰራር ተሞክሮ መቅሰም የራሳችንን ማጋራት ተችሏል፤
- ደንብ ቁጥር 144/2000 ጨምሮ የተለያዩ የፀረ-ሙስናን አዋጆች እና መመሪያዎች በዩኒቨርሲቲው ዕውቅና አግኝተው እንዲፈፀሙ ተደርሽ ተደርጓል፤
- የሰራተኞች የኃብት ምዝገባ እና የማሳወቅ ስራ ለፌዴራል ስነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን እና ለሚመለከታቸው የስራ ክፍሎች ማዳረስ ተችሏል፤
- ይህም ከታቀደው በአንደኛ ሩብ ዓመት 18.44% መከናወኑን ያመለክታል፤
ግብ 17፡- የክትትል ፣ ድጋፍ ፣ ግምገማና ግብረ-መልስ አሰራርን ማጎልበት፤
- በአስተዳደርና በአካዳሚክ ዘርፎች የሚገኙት የስራ ክፍሎች በስራ አፈጻጸማቸዉ ያለባቸዉን ክፍተት ለመለየት እና ለማረም በተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች ግምገማ ተከናዉኗል፤
- ሠራተኞች የመንግስት የስራ ሰዓት በአግባቡ እንዲጠቀሙ ተከታታይነት ያለዉ ቁጥጥር ተደርጓል፣
- የኢንፎርሜሽን ኮሙኒካሽን ቴክኖሎጂ ፕሮጀክቶች በታቀደዉ ጊዜና በሚጠበቀዉ ጥራት ተጠናቀዉ ወደ ስራ እንዲገቡ የክትትልና ድጋፍ ስራዎች ተሠርቷል፤
- ውጤት ያልሞላላቸዉ 399 የርቀትና ተከታታይ ተማሪዎችን ከኮሌጆችና ፋካልቲዎች ጋር በመሆን የመለየት ስራ ተሰርቷል፣
- የ2013 ዓ.ም ዕቅድን በማቀናጀትና በማጠናከር ለሚመለከታቸው አካላት እንዲደርስ ክትትል ተደርጓል፤
- ሁሉም ኮርሶች ሃርሞናይዝድ ካሪኩለሙ በሚያዘው ምዘናዎች እንዲተግብሩ ክትትልና ድጋፍ ተደርጓል፤
- የፈተና ገምጋሚና ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ በማቋቋም ፈተናዎች እንዲገመገሙና ቅሬታዎችም ሲያጋጥሙ በጊዜ እንዲፈቱ ተደርጓል፤
- የትምህርት ክፍሎች ዕቅድ በትክክለኛው ጊዜ መተግበሩ ክትትል ተደርጓል፤
- በተከታታይ ምዘና አሰጣጥና አፈፃፀም ዙሪያ የሚነሱ ችግሮችን አስቀድሞ በመለየት ክትትልና ድጋፍ ተደርጓል፤
- ይህም ከታቀደው በአንደኛ ሩብ ዓመት 18.44% መከናወኑን ያመለክታል፤
ክፍል አራት
4.1. ማጠቃለያ
4.2. በበጀት ዓመቱ ዕቅድ አፈፃፀም ወቅት ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ የመፍትሔዎች
4.2.1 ያጋጠሙ ችግሮች
ሀ/ ከክህሎት አንፃር ፤
- በተለያዩ መድረኮች የዕቅድና የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት በወቅቱ እንዲቀርብ ቢገለጽም ጥቂት የስራ ክፍሎች በሚሰጠዉ ጊዜ ገደብ ዉስጥ አለማቅረብ
- በአንዳንድ ፈፃሚዎች በኩል ተገልጋይ /ደንበኛ ተኮር አገልግሎት አሰጣጥ በሚለው ጽንሰ ሀሣብ ላይ የግንዛቤ እጥረት መኖር ፤
- በአንዳንድ የሥራ መስኮች የቅጥር ማስታወቂያዎች ሲወጣ ተፈላጊ ተወዳዳሪዎችን በገበያ ላይ ያለመገኘት ፤
ለ. ከአመለካከት አንፃር ፤
- በአንዳንድ የስራ ክፍል ኃላፊዎች የራሳቸውን የስራ ድርሻ በውል ባለማወቅ ምክንያት በራሳቸው ጥረት ሥራዎችን ከመሥራት ይልቅ የጠባቂነት ስሜት መታየት ፤
- በአንዳንድ ሠራተኞች በኩል መብትና ግዴታን አውቆ የተሰጠውን ሃላፊነት በአግባቡ ያለ መወጣት ችግር ፤
- በአንዳንድ የስራ ክፍሎች የሪፖርት አቀራረብ ስርዓት እንዲሁም በየዕለቱ የሚሰሩትን ተግባራት በማስታወሻ ባለመያዛቸው ምክንያት በሚያቀርቡት ሪፖርቶች ላይ ክፍተት መኖሩ ፤
ሐ. ከግብዓት አንፃር፤
- በበጀት ወጪ አጠያየቅ ረገድ ደንብና መመሪያው ያልተከተለ መሆኑ ፤
- በቂ የማጣቀሻ መጽሐፍት አለመኖር ፤
- የላብራቶሪ /የተግባር ትምህርት/ መለማመጃ እጥረት ፤
- የኢንተርኔት አገልግሎት በበቂ ሁኔታ አለመኖር ፤
መ. ከአቅም በላይ የሆኑ ችግሮች፤
- የመጠጥ ዉሃ አቅርቦት እጥረት ፤
- የሕንጻ ግንባታዎች በተባለዉ ጊዜ መድረስ አለመቻል ፤
4.2.2 የተወሰዱ የመፍትሄ እርምጃዎች፤
ሀ. ከክህሎት አንፃር
- በተደጋጋሚ ደንብና መመሪያ እየተከተሉ እንዲሠሩ በቃል እና በጽሁፍ ለሁሉም ስራ ክፍሎች ተገልጾላቸዋል፤
- በዩኒቨርሲቲዉ የዘጎች ቻርተር እንዲዘጋጅ ኮሚቴ ተቋቁሟል፤
- ባሉት ባለሙያዎች በመሸፈን እና የመጀመሪያ ዲግሪ ምሩቃን ቅጥር ተፈጽሟል፤
ለ. ከአመለካከት አንፃር፤
- በስራ ክፍሎች የስራ ግልጸኝነት እንዲኖር ዉይይት ተደርጓል፤
- ከስራ ገበታቸዉ ያለ በቂ ምክንያት በሚቀሩ ሠራተኞች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ተደርጓል፤
- ስራዎች ሲሠሩ ወዲያዉኑ ማስታወሻ እንዲይዙ አቅጣጫ ተስጥቶ የሪፖርት ፎርማት ለሁሉም የስራ ክፍሎች ተደራሽ ተደርጎል፤
ሐ. ከግብዓት አንፃር፤
- በበጀት አጠያየቅ ዙሪያ ደንብና መመሪያ የተከተለ እንዲሆን ለሁሉም የስራ ክፍሎች ደብዳቤ ተጽፏል፤
- ከበየነ መረብ የተለያዩ መጽሐፍቶችን በማዉረድና ፕሪንት ተደርጎ እና በማባዛት ለአገልግሎት እንዲዉል ተድርጓል፤
- ላቦራቶሪ/ የተግባር ትምህርት ወዳለበት ዩኒቨርሲቲዎችና ተቋማት በመላክ እንዲለማመዱ ተደርጓል፤
- ለኢንተርኔት አገልግሎት ችግሮች ዘላቂ መፍትሄ ይሆን ዘንድ አዲስ የተጀመረዉ ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ “ICT” ፕሮጀክት ግንባታ እየተካሄደ ይገኛል፤
መ/ ከአቅም በላይ ለሆኑ ችግሮች፡-
- ግለሰቦች የመጠጥ ዉሃ በቦቴ መኪና እንዲያቀርቡ ከመደረጉ በተጨማሪ የባሮ ወንዝ ዉሃ በመሳብና በማጣራት ለአገልግሎት ዉሏል፤ እንዲሁም ለዘላቂ መፍትሄዉ ጥልቅ የመጠጥ ዉሃ ጉድድ ቁፋሮ ተደርጎ የዉሃ መስመር ዝርጋታ ከክልሉ ዉሃ ስራዎች ድርጅት ጋር ዉል በመፈራረም በሂደት ላይ ይገኛል፤
- የሕንጻ ፕሮጀክቶች ግንባታ በተባለዉ ጊዜ ያላደረሱ አንዳንድ ኮንትራክተሮች ዉላቸዉ ተkርጦ ሌሎች ተkራጮች እንዲጋበዙበት በሂደት ላይ ይገኛል፤
አፈጻጸም በሰንጠረዥ
ሰንጠረዥ 5፡-የ2013 ዓ.ም የ1ኛ ሩብ ዓመት የድርጊት መርሃ–ግብር አፈጻጸም ሪፖርት፣
እይታ | ስቲራተጅክግብ | የታቀዱዋናዋናተግባራት | ክብደት (20) | መለኪያ | ነባራዊመነሻ | ኢላማ | የዓመቱ ዕቅድ 1ኛ ሩብ ዓመቱ ክንውን ጋር በንፅፅር ስዘጋጂ | ያልተከናወኑተግባራት | ||||||||||
ስታንደርድ | የተከናወኑተግባራት | ስታንደርድ | አፈፃፀም(%) | የአፈፃፀምውጤት (%) | ||||||||||||||
መጠን | ጥራት | ጊዜ በሰዓት | ወጪ | መጠን | ጥራት | ጊዜ | ወጪ | |||||||||||
ተገልጋይ | ግብ .1፡ -የደንበኞችናባለድርሻአካላትንዕርካታማሳደግ | 15 | % | 65 | 85% | 20 | 100% | 2400 ሰዓት | 25 | 20 | 18 | 25 | 22 | 3.3 | ||||
የደንበኞችንፍላጎትመሰረትያደረገጥራትያለውአገልግሎትመስጠት (15%) | 15 | % | 65 | 85% | 20 | 100% | 2400ሰዓት | ያደገ የደንበኞችና የባለድርሻ አካላት ዕርካታ | 25 | 20 | 18 | 25 | 22 | 3.3 | ||||
እይታ | ስቲራተጅክ ግብ | የታቀዱ ዋና ዋና ተግባራት | ክብደት (20) | መለኪያ | ነባራዊመነሻ | ኢላማ | የዓመቱ ዕቅድ 1ኛ ሩብ ዓመት ክንውን ጋር በንፅፅር ስዘጋጂ | ያልተከናወኑ ተግባራት | ||||||||||
ስታንደርድ | የተከናወኑ ተግባራት | ስታንደርድ | አፈፃፀም % | የአፈፃፀምውጤት % | ||||||||||||||
መጠን | ጥራት | ጊዜበሰዓት | ወጪ | መጠን | ጥራት | ጊዜ | ወጪ | |||||||||||
ተገልጋይ | ግብ 2፡- የደንበኞችንናየባለድርሻ አካላትን ቁጥር መጨመር | 5 | በቁጥር | 6028 | 9442 | 9442 | 100 | 2400 | 20 | 25 | 15 | 25 | 21.25 | 2.13 | ||||
የቅድመ ምረቃ ትምህርት ቁጥር መጨመር | 3 | በቁጥር | 6028 | 9442 | 9442 | 100 | 2400 | ያደገ የደንበኞችና የባለድርሻ አካላት ዕርካታ | 20 | 25 | 15 | 25 | 21.25 | 2.13 |
እይታ | ስቲራተጅክግብ | የታቀዱዋናዋናተግባራት | ክብደት (10) | መለኪያ | ነባራዊመነሻ | ኢላማ | የዓመቱ ዕቅድ 1ኛ ሩብ ዓመቱ ክንውን ጋር በንፅፅር ስዘጋጂ | ያልተከናወኑተግባራት | ||||||||||
ስታንደርድ | የተከናወኑተግባራት | ስታንደርድ | አፈፃፀም % | የአፈፃፀምውጤት % | ||||||||||||||
መጠን | ጥራት | ጊዜበሰዓት | ወጪ | መጠን | ጥራት | ጊዜ | ወጪ | |||||||||||
ፋይናንስ | ግብ 3፡-የሃብትአጠቃቀምውጤታማነትንማሻሻል | 4 | % | 85% | 100% | 24 | 100% | 2880 ሰዓት/ | 22 | 25 | 20 | 24 | 22.75 | 2.3 | ||||
የተገኘን ሀብት በአግባቡናዉጤታማ በሆነ መልኩ መጠቀም | 4 | % | 85% | 100% | 24 | 100% | 2880 ሰዓት/ | ፍትሃዊ፤ ዉጤታማና ቀልጣፋ የሀብት አጠቃቀም | 22 | 25 | 20 | 24 | 22.75 | 2.3 |
እይታ | ስቲራተጅክግብ | የታቀዱ ዋና ዋና ተግባራት | ክብደት(10) | መለኪያ | ነባራዊመነሻ | ኢላማ | የዓመቱ ዕቅድ 1ኛ ሩብ ዓመቱ ክንውን ጋር በንፅፅር ስዘጋጂ | ያልተከናወኑ ተግባራት | ||||||||||
ስታንደርድ | የተከናወኑ ተግባራት | ስታንደርድ | አፈፃፀም % | የአፈፃፀምውጤት % | ||||||||||||||
መጠን | ጥራት | ጊዜበሰዓት | ወጪ | መጠን | ጥራት | ጊዜ | ወጪ | |||||||||||
ፋይናንስ | ግብ . 4 የውስጥገቢአቅምንማሳደግ | 6 | % | 8000000 | 9200000 | 12 | 100% | 2880 ሰዓት | 15 | 10 | 20 | 25 | 17.5 | 0.88 | ||||
የተለያዩአገልግሎቶችን በመስጠት ገቢ ማመንጫ ዘርፎችን በማቓቓም የፋይናነስ በጀት አገልግሎት መስጠት | 6 | % | 80 | 90% | 12 | 100% | 2880 ሰዓት | ያደገ የዉስጥ ገቢና የፋይናነስ አጠቃቀም | 15 | 10 | 20 | 25 | 17.5 | 0.88 |
እይታ | ስቲራተጅክግብ | የታቀዱዋናዋናተግባራት | ክብደት (40) | መለኪያ | ነባራዊመነሻ | ኢላማ | የዓመቱ ዕቅድ 1ኛ ሩብ ዓመቱ ክንውን ጋር በንፅፅር ስዘጋጂ | ያልተከናወኑተግባራት | ||||||||||
ስታንደርድ | የተከናወኑተግባራት | ስታንደርድ | አፈፃፀም % | የአፈፃፀምውጤት % | ||||||||||||||
መጠን | ጥራት | ጊዜበሰዓት | ወጪ | መጠን | ጥራት | ጊዜ | ወጪ | |||||||||||
የውሰጥ አሰራር | ግብ 5፡- የትምህርትጥራትናአግባብነትንማሳደግ | 4 | % | 80 % | 95% | 12 | 100% | 2400 ሰዓት | 23 | 25 | 22 | 25 | 23.75 | 1.2 | ||||
የአካዳሚክ ፕሮግራሞ ችንና ስርዓተ ትምህር ት በመተግበር፤በምር ምር ዙሪያ የአጋሮችን ግንኙነት በመፍጠር የትምህርት ጥራትን ማሳደግ | 2 | % | 80% | 95% | 12 | 100% | 2400ሰዓት | የደገ የትምህርት ጥራትና በምርምር ዙሪያ የተጠናከረ የአጋሮች ግንኙነት | 23 | 25 | 22 | 25 | 23.75 | 1.2 |
እይታ | ስቲራተጅክግብ | የታቀዱ ዋና ዋና ተግባራት | ክብደት | መለኪያ | ነባራዊመነሻ | ኢላማ | የዓመቱ ዕቅድ 1ኛ ሩብ ዓመቱ ክንውን ጋር በንፅፅር ስዘጋጂ | ያልተከናወኑ ተግባራት | ||||||||||
ስታንደርድ | የተከናወኑተግባራት | ስታንደርድ | አፈፃፀም % | የአፈፃፀምውጤት % | ||||||||||||||
መጠን | ጥራት | ጊዜበሰዓት | ወጪ | መጠን | ጥራት | ጊዜ | ወጪ | |||||||||||
የዉስጥ ዐሰራር | ግብ፡-6 የትምህርትጥራትና ተደረሽነትንማሳደግ | 10 | % | 75% | 80% | 5 | 100% | 2400 ሰዓት | 24 | 25 | 18 | 25 | 23 | 0.69 | ||||
በተለያዩ መርሃ ግብሮች አዳዲስ የቅድመ ምረቃና ድህረ ምረቃ ፕሮግራሞችን ማስፋፋት | 5 | % | 75 % | 80% | 5 | 100% | 2400ሰዓት | ያደገ የትምህርት ጥራትና ተደራሽነት | 24 | 25 | 18 | 25 | 23 | 0.69 |
እይታ | ስቲራተጅክግብ | የታቀዱ ዋና ዋና ተግባራት | ክብደት | መለኪያ | ነባራዊመነሻ | ኢላማ | የዓመቱ ዕቅድ 1ኛ ሩብ ዓመቱ ክንውን ጋር በንፅፅር ስዘጋጂ | ያልተከናወኑተግባራት | ||||||||||
ስታንደርድ | የተከናወኑ ተግባራት | ስታንደርድ | አፈፃፀም % | የአፈፃፀምውጤት % | ||||||||||||||
መጠን | ጥራት | ጊዜበሰዓት | ወጪ | መጠን | ጥራት | ጊዜ | ወጪ | |||||||||||
የዉስጥ ዐሰራር | ግብ.7፡- የአጋሮችንናየህብረተሰቡንተሳትፎ ማሳደግ | 10 | በቁጥር | 7 | 12 | 5 | 100 | 2880ሰዓት | 25 | 23 | 20 | 25 | 23.25 | 0.7 | ||||
ከተቃሙ ጋርልሰሩ የሚች ሉ አጋሮችን ቁጥር መጨመር ና ማስፋፋት | 5 | በቁጥር | 7 | 12 | 5 | 100% | 2880 ሰዓት | ያደገ የአጋሮች ቁጥርና ተሳትፎ | 25 | 23 | 20 | 25 | 23.25 | 0.7 |
እይታ | ስቲራተጅክ ግብ | የታቀዱ ዋና ዋና ተግባራት | ክብደት | መለኪያ | ነባራዊመነሻ | ኢላማ | የዓመቱ ዕቅድ 1ኛ ሩብ ዓመቱ ክንውን ጋር በንፅፅር ስዘጋጅ | ያልተከናወኑ ተግባራት | ||||||||||
ስታንደርድ | የተከናወኑ ተግባራት | ስታንደርድ | አፈፃፀም % | የአፈፃፀም ውጤት % | ||||||||||||||
መጠን | ጥራት | ጊዜበሰዓት | ወጪ | መጠን | ጥራት | ጊዜ | ወጪ | |||||||||||
የዉስጥ አሰራር | ግብ፡- 8 የጥናትና ምርምር ጥራት ማሳደግ | 5 | % | 70 | 85 | 15 | 100% | 2880 ሰዓት/ | 20 | 20 | 25 | 25 | 22.5 | 1.12 | ||||
ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምር ማካሄድ | 2 | % | 70 | 85 | 15 | 100% | 2880 ሰዓት/ | የተገኙ ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምር ዉጤቶች | 20 | 20 | 25 | 25 | 22.5 | 1.12 |
እይታ | ስቲራተጅክግብ | የታቀዱ ዋና ዋና ተግባራት | ክብደት(10) | መለኪያ | ነባራዊ | ኢላማ | የዓመቱ ዕቅድ 1ኛ ሩብ ዓመቱ ክንውን ጋር በንፅፅር ስዘጋጂ | ያልተከናወኑ ተግባራት | ||||||||||
ስታንደርድ | የተከናወኑ ተግባራት | ስታንደርድ | አፈፃፀም % | የአፈፃፀም % | ||||||||||||||
መጠን | ጥራት | ጊዜበሰዓት | ወጪ | መጠን | ጥራት | ጊዜ | ወጪ | |||||||||||
ፋይናንስ | ግብ9፡የማህበረሰብአገልግሎትጥራትማሻሻል /6 % | 6 | በቁጥር | 8 | 15 | 7 | 100% | 2880 | 25 | 25 | 24 | 25 | 24.75 | 1.24 | ||||
ሁሉን አቀፍ የማህበረሰብ አገልግሎት መስጠት፣ | 6 | በቁጥር | 8 | 15 | 7 | 100% | 2880 | የተሰጠ የማህበረሰብ አገልግሎት | 25 | 25 | 24 | 25 | 24.75 | 1.24 |
እይታ | ስቲራተጅክግብ | የታቀዱ ዋና ዋና ተግባራት | ክብደት(10) | መለኪያ | ነባራዊመነሻ | ኢላማ | የዓመቱ ዕቅድ 1ኛ ሩብ ዓመቱ ክንውን ጋር በንፅፅር ስዘጋጂ | ያልተከናወኑተግባራት | ||||||||||
ስታንደርድ | የተከናወኑ ተግባራት | ስታንደርድ | አፈፃፀም % | የአፈፃፀምውጤት % | ||||||||||||||
መጠን | ጥራት | ጊዜ | ወጪ | መጠን | ጥራት | ጊዜ | ወጪ | |||||||||||
ፋይናንስ | ግብ 10፡- የተክኖሎጅሽግግር ልማትናየኢንዱስትርትስስርን ማሳደግ | 4 | በቁጥር | 60 % | 75% | 15 | 100% | 2880ሰዓት | 10 | 15 | 20 | 15 | 15 | 0.6 | ||||
በተቁዋሙ የቴክኖሎጂ ልማት ማሻሻያ እና የሽግግር ስራዎችን ማጠናከር | 4 | በቁጥር | 60 % | 75% | 15 | 100% | 2880ሰዓት | የጎለበተ የቴክኖሎጂ ሽግግር እና የዳበረ የዩኒቨርሲቲ ኢንዱስትሪ ትስስር | 10 | 15 | 20 | 15 | 15 | 0.6 |
እይታ | ስቲራተጅክ ግብ | የታቀዱ ዋና ዋና ተግባራት | ክብደት (40) | መለኪያ | ነባራዊመነሻ | ኢላማ | የዓመቱ ዕቅድ 1ኛ ሩብ ዓመቱ ክንውን ጋር በንፅፅር ስዘጋጂ | ያልተከናወኑተግባራት | ||||||||||
ስታንደርድ | የተከናወኑ ተግባራት | ስታንደርድ | አፈፃፀም % | የአፈፃፀምውጤት% | ||||||||||||||
መጠን | ጥራት | ጊዜበሰዓት | ወጪ | መጠን | ጥራት | ጊዜ | ወጪ | |||||||||||
የውሰጥአሰራር | ግብ.11፡-ምቹ የስራ አካባቢን በመፍጠርና የህዝብ ግንኙነት ሥራዎችን በማጠናከር ተቋማዊ ባህልን ማጓልበት | 5 | % | 60% | 75% | 15 | 100% | 2880 ሰዓት | 18 | 20 | 22 | 25 | 21.25 | 0.64 | ||||
የሕዝብና የውጪ ግንኙነት ድጋፍ አገልግሎት መስጠት፣ | 3 | % | 60% | 75% | 15 | 100% | 2880ሰዓት | የተፈጠረ ምቹ የስ ራ አካባቢ ፤የተጠ ናከረ የህዝብና ዉጪ ግንኙነት እና የጎለበተ የስራ ባህል | 18 | 20 | 22 | 25 | 21.25 | 0.64 |
እይታ | ስቲራተጅክ ግብ | የታቀዱ ዋና ዋና ተግባራት | ክብደት(10) | መለኪያ | ነባራዊመነሻ | ኢላማ | የዓመቱ ዕቅድ 1ኛ ሩብ ዓመቱ ክንውን ጋር በንፅፅር ስዘጋጂ | ያልተከናወኑ ተግባራት | ||||||||||
ስታንደርድ | የተከናወኑ ተግባራት | ስታንደርድ | አፈፃፀም % | የአፈፃፀምውጤት % | ||||||||||||||
መጠን | ጥራት | ጊዜበሰዓት | ወጪ | መጠን | ጥራት | ጊዜ | ወጪ | |||||||||||
የዉስጥ አሰራር | ግብ፡-12 ተቋማዊ ለውጥና መልካም አስተዳደርን ማጠናከር | 3 | በቁጥር | 70% | 85% | 15 | 100% | 2880 ሰዓት | 15 | 20 | 18 | 25 | 19.5 | 0.78 | ||||
የለዉጥ መሳ ሪያዎችን በመተግበር፤ ስነ-ምግባር የማሻሻል እና ሙስናን የመከላከል ድጋፍ መስጠት፣ | 3 | በቁጥር | 70 % | 85% | 15 | 100% | 2880 ሰዓት | የተጠናከረ የተቁዋማዊ ለዉጥና መልካም አስተዳደር | 15 | 20 | 18 | 25 | 19.5 | 0.78 |
እይታ | ስቲራተጅክግብ | የታቀዱ ዋና ዋና ተግባራት | ክብደት (10) | መለኪያ | ነባራዊመነሻ | ኢላማ | የዓመቱ ዕቅድ 1ኛ ሩብ ዓመቱ ክንውን ጋር በንፅፅር ስዘጋጂ | ያልተከናወኑተግባራት | ||||||||||
ስታንደርድ | የተከናወኑ ተግባራት | ስታንደርድ | አፈፃፀም % | የአፈፃፀምውጤት % | ||||||||||||||
መጠን | ጥራት | ጊዜበሰዓት | ወጪ | መጠን | ጥራት | ጊዜ | ወጪ | |||||||||||
የዉስጥ አሰራር | ግብ፡-13 የባለብዙዘርፈጉዳዮችንአሰራርማጎልበት | 3 | በቁ/ር | 60% | 80 | 20 | 100% | 2400 ሰዓት | 15 | 20 | 18 | 25 | 19.5 | 0.59. | ||||
የስርዓተ ፆታን በተመለከተ ግንዛቤ ሊያስጨብጡ የሚችሉ ስልጠናዎችን መስጠት በተቋሙ የሴቶችን ሚና ማሳደግ እና ተሳትፎን መጨመር | 3 | በቁ/ር | 60% | 80 | 20 | 100% | 2400 ሰዓት | የጎለበተ የባለ ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች አሰራር | 15 | 20 | 18 | 25 | 19.5 | 0.59. |
እይታ | ስቲራተጅክግብ | የታቀዱ ዋና ዋና ተግባራት | ክብደት(30) | መለኪያ | ነባራዊመነሻ | ኢላማ | የዓመቱ ዕቅድ 1ኛ ሩብ ዓመቱ ክንውን ጋር በንፅፅር ስዘጋጂ | ያልተከናወኑ ተግባራት | ||||||||||
ስታንደርድ | የተከናወኑ ተግባራት | ስታንደርድ | አፈፃፀም % | የአፈፃፀምውጤት % | ||||||||||||||
መጠን | ጥራት | ጊዜበሰዓት | ወጪ | መጠን | ጥራት | ጊዜ | ወጪ | |||||||||||
መማርናዕድገት | ግብ.14 የሰው ኃይል ዕውቀት ፤ክህሎትና ተነሳሽነት ብቃት ማሳደግ ፤ | 8 | በቁጥር | 75 % | 85% | 10 | 100% | 2880ሰዓት | 25 | 23 | 20 | 25 | 23.25 | 2.33 | ||||
ለበጀት ዓመቱ የአስተዳደር ሰራተኞች እና የመምህራን ቅጥር ማካሄድ፣ | 5 | % | 75% | 85% | 10 | 100% | 2880 ሰዓት | የመምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች ቅጥር ተከናውኗል ፤ | 25 | 23 | 20 | 25 | 23.25 | 2.33 |
እይታ | ስቲራተጅክግብ | የታቀዱ ዋና ዋና ተግባራት | ክብደት (30) | መለኪያ | ነባራዊመነሻ | ኢላማ | የዓመቱ ዕቅድ 1ኛ ሩብ ዓመቱ ክንውን ጋር በንፅፅር ስዘጋጂ | ያልተከናወኑ ተግባራት | ||||||||||
ስታንደርድ | የተከናወኑ ተግባራት | ስታንደርድ | አፈፃፀም % | የአፈፃፀምውጤት % | ||||||||||||||
መጠን | ጥራት | ጊዜበሰዓት | ወጪ | መጠን | ጥራት | ጊዜ | ወጪ | |||||||||||
መማርናዕድገት | ግብ 15፡- ለተቋማዊ ዕድገት የሚያግዙግብዓቶችንመሰረተልማትማሳደግ | 7 | በቁጥር | 60 | 80% | 20 | 100% | 2880 ሰዓት | 25 | 24 | 23 | 25 | 24.25 | 1.21 | ||||
የተቋሙን አገልግቶች በICT የተደገፈ ለማድረግ የሚያስችሉ ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ በማድረግ የተቋሙን የአሰራር ሂደት ዘመናዊ ማድረግ; | 3 | % | 60% | 80% | 20 | 100% | 2880ሰዓት | በመሰረተ ልማትና ግብዓቶች አቅርቦት የጎለበተ ተቁዋም | 25 | 24 | 23 | 25 | 24.25 | 1.21 | ||||
እይታ | ስቲራተጅክግብ | የታቀዱ ዋና ዋና ተግባራት | ክብደት(10) | መለኪያ | ነባራዊመነሻ | ኢላማ | የዓመቱ ዕቅድ 1ኛ ሩብ ዓመቱ ክንውን ጋር በንፅፅር ስዘጋጂ | ያልተከናወኑ ተግባራት | ||||||||||
ስታንደርድ | የተከናወኑ ተግባራት | ስታንደርድ | አፈፃፀም % | የአፈፃፀምውጤት % | ||||||||||||||
መጠን | ጥራት | ጊዜበሰዓት | ወጪ | መጠን | ጥራት | ጊዜ | ወጪ | |||||||||||
ፋይናንስ | ግብ 16፡-የአመራርአደረጃጀትና አሠራር ሥርዓት ብቃት ማሻሻል | 10 | 85 | 95% | 10 | 100% | 2880ሰዓት | 23 | 24 | 20 | 25 | 23 | 1.15 | |||||
የሕግ ድጋፍ አገልግሎት በመስ ጠት፣ ህጎችና ደንቦች ስራ ላይ እንዲዉሉ ማድረግ | 10 | 85 | 95% | 10 | 100% | 2880ሰዓት | የተሸሻለ የአመራር፤ የአደረጃጀትና የአሰራር ስርዓት | 23 | 24 | 20 | 25 | 23 | 1.15 |
እይታ | ስቲራተጅክግብ | የታቀዱ ዋና ዋና ተግባራት | ክብደት(10) | መለኪያ | ነባራዊመነሻ | ኢላማ | የዓመቱ ዕቅድ 1ኛ ሩብ ዓመቱ ክንውን ጋር በንፅፅር ስዘጋጂ | ያልተከናወኑ ተግባራት | ||||||||||
ስታንደርድ | የተከናወኑ ተግባራት | ስታንደርድ | አፈፃፀም% | የአፈፃፀምውጤት % | ||||||||||||||
መጠን | ጥራት | ጊዜበሰዓት | ወጪ | መጠን | ጥራት | ጊዜ | ወጪ | |||||||||||
ፋይናንስ | ግብ.17 የክትትል ድጋፍ ግምገማና ግብረመልስአሰራርን ማጎልበት | 5 | % | 80% | 95% | 15 | 100% | 2880ሰዓት | 24 | 24 | 20 | 25 | 23.25 | 1.16 | ||||
የስራ ላይ የክትትልና ድጋፍ ማጠናከሪያ ሥራዎችን ማከናወን፣ | 5 | % | 80% | 95% | 15 | 100% | 2880ሰዓት | በተቁዋሙ የጎለበተ የክትትል ፤የድጋፍ፤ የግምገማና የግብረ መልስ ሂደት | 24 | 24 | 20 | 25 | 23.25 | 1.16 |