በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት ” ማህበረሰብ አቀፍ አስተማማኝ ሰላም እና ዘላቂ ልማት ለክልላዊና አገራዊ ዕድገት ” በሚል መሪ ቃል ክልሉ አፈጉባኤ አዳራሽ ታላቅ ኮንፈረንስ አካሄደ።

ሚያዝያ 21/2013 ዓ.ም

በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት” ማህበረሰብ አቀፍ አስተማማኝ ሰላም እና ዘላቂ ልማት ለክልላዊና አገራዊ ዕድገት ” በሚል መሪ ቃል በክልሉ ም/ቤት አደራሽ ኮንፈረንስ ተካሔደ ።
ሚያዝያ 20/2013 ዓ.ም
ጋምቤላ -ኢትዮጵያ

በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት ” ማህበረሰብ አቀፍ አስተማማኝ ሰላም እና ዘላቂ ልማት ለክልላዊና አገራዊ ዕድገት ” በሚል መሪ ቃል በክልሉ ም/ቤት አደራሽ የማህበረሰብና ልማት ኮንፈረንስ ተካሔደ ።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ ኡጁሉ ኡኮክ በመድረኩ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በማስተላለፍ የዕለቱን የክብር እንግዳ የክልሉን ፕሬዝዳንት ወደ መድረክ የጋበዙ ሲሆን ክቡር ፕሬዝዳንት አቶ ኡመድ ኡጅሉ የመክፍቻ
ንግግር በማድረግ ኮንፈረንሱን በይፋ አስጀምረዋል ። ክቡር ፕሬዝዳንት አቶ ኡሞድ ኡጁሉ በሰላም ኮንፈረንሱ ማስጀመሪያ ላይ እንዳሉት ዘመናትን የተሻገረ በደም የተሳሰረ በብዝሃነታችን ውስጥ ያለውን አንድነት ለማስቀጠል ሁሉም ዜጋ ሃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል ። ክቡር ፕሬዝዳንቱ አክለውም ዩኒቨርሲቲው በሰላም ግንባታ ዙሪያ እያበረከተ ላለው አስተዋጽዖ የክልሉ መንግስት ከፍተኛ አድናቆት ያለው መሆኑን ጠቅሰው በሰላም ግንባታ ዙሪያ ለሚያደርገው ማንኛውም ጥረት የክልሉ መንግስት ከዩኒቨርሲቲው ጎን እንደሚቆም ገልፀዋል ።
በኮንፈረንሱ ላይ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ተወካዮች ፣ የሰላም ሚኒስቴር ተወካይ፣ የ9 የሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎች ( የኢትዮጵያ ሲቭል ሰርቪስ ፣ የደምቢዶሎ ፣ የአሶሳ ፣ የመቱ ፣ የሚዛን ቴፒ ፣ የጅማ ዩኒቨርቲዎች ) የምርምር ማህበረሰብ አገልግሎት ፕሬዝዳንቶች ፣ የክልሉ ካቢኔ ከፍተኛ ሥራ ኃላፊዎች ፣ የክልሉ ዋና አፈጉባኤና ም/ አፈጉ ባዔዎች ፣ የዞን አስተዳዳሪዎች፣ የኦሮሚያ ፣ የደቡብና የቤኒሻንጉል የአጎራባች ክልል ዞን ዋና አስተዳዳሪዎች ፣ የተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት የተውጣጡ ባለድርሻ አካላት ፣ የዩኒቨርሲቲያችን ፕሬዝዳንትና ም/ፕሬዝዳንቶች ፣ ዳይሬክተሮች፣ ቡድን መሪዎችንና አስተባባሪዎች ተሳትፈዋል ።

በኮንፈረንሱ ላይ 4 ለውይይት የሚሆኑ ጥናታዊ ጽሁፍች ቀርበዋል ። የመጀመሪያዉን የውይይት መነሻ ጽሁፍ “Peace and Peaceful Coexistence በሚል ርዕስ ያቀረቡት የዩኒቨርሲቲያችን ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡጅሉ ኦኮክ ናቸው ። ሁለተኛው የውይይት መነሻ ጽሁፍ Conflict reconciliation ” በሚል ርዕስ ያቀረቡት የጋምቤላ መምህራንና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ጋትሏክ ሮን ሲሆኑ በተጨማሪም ” Development Opportunities of Gambella Region and its Challenges ” በሚል ጥናት ያቀረቡት ደግሞ የዩኒቨርሲቲው ምር/ማህ/ አገ/ትና ኢን/ትስስር ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጋትሏክ ጋትኮስ ናቸው ። የመጨረሻውን የውይይት ጽሁፍ ያቀረቡት ደግሞ መምህር ሉል ዴቪድ “Sustainable Development” በሚል ርዕስ ሲሆን በቀረቡት 4ቱም ጥናታዊ ጽሁፎች ላይ ሰፊ ውይይት ተካሒዶባቸዋል ።
4ቱንም የውይይት መነሻ ጽሁፎች በተመለከተ በዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ም/ፕሬዝዳንት ዶክተር ከተማ ጥላሁን አወያይነት ከመድረኩ በተነሱ የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ዙሪያ ጥናት አቅራቢዎቹ ማብራሪያ ሰጥተዋል ። በመጨረሻም የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ም/ቦርድ ሰብሳቢና የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ላክዴር ላክባክ በመድረኩ ከተለያዩ አካላት ለተነሱ አስተያየቶች ማብራሪያ በመስጠት ኮንፈረሱን በንግግር ዘግተው የዕለቱ መድረክ ተጠናቋል ። ለበለጠ መረጃ   https://www.facebook.com/www.gmu.edu.et ይጎብኙ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *