የ2016 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆነ

***************

(ኢ ፕ ድ)

የ2016 የትምህርት ዘመን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆነ።

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ሐምሌ 3-5 ለማህበራዊ ሳይንስ፤ ሐምሌ 9-11 ቀን 2016 ዓ.ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በበይነ መረብና በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በወረቀት ይሰጣል።

የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ከሰኔ 30 እሰከ ሐምሌ 01ቀን 2016 ዓ.ም እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ሐምሌ 6-7 ቀን 2016 ዓ.ም ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ይሆናል።

ተፈታኞችና የሚመለከታቸው ሁሉ ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳስቧል።

ሚያዝያ 21 ቀን 2016 ዓም