የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ስልጠና እና የበጎ ፍቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎች ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ፤

ሰኔ 14/2016 ዓ.ም

ጋምቤላ-ኢትዮጵያ

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ስልጠና እና የበጎ ፍቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎች ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ፤

ፕሮግራሙን ሰላም ሚኒስቴርና ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ በመተባበር ያዘጋጁት ሲሆን የክረምት በጎ ፍቃድ ተማሪዎች ለአምስት ቀናት ያህል በሰላም ግንባታ፣ በብሄራዊ መግባባትና በማህበራዊ ትስስር ዙሪያ ስልጠና ከወሰዱ በኋላ ለ25 ቀናት ደግሞ የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎችን የሚያከናውኑ ይሆናል።

በዚህ የክረምት በጎ ፍቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎች ላይ 465 ተማሪዎች የሚሳተፉ ይሆናል።