
ጋምቤላ-ኢትዮጵያ
ጥቅምት-25/2013 ዓ.ም
ቀደም ሲል እንደተለመደው ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ በየዓመቱ አዲስ ለሚቀጠሩ መምህራን የኢንዳክሽን ስልጠና በመስጠት አዲስ ለሚጀምሩት ስራ የአእምሮና የስነልቦና ዝግጅት እንዲያደርጉ እንዲሁም የተቋሙን የአሰራር ስርዓትና የመማር ማስተማሩን ስራ በደንብ እንዲተዋቁ ለማድረግ ይዘጋጃል፡፡ በመሆኑም ስልጠናው ከትላንት ጥቅምት 25-26/2013 ዓ.ም ጀምሮ እየተሰጠ ሲሆን ቁጥራቸው ከ30 የሚበልጡ ሰልጣኞች ስልጠናውን እየተከታተሉት ይገኛሉ፡፡