ህዳር 08/2013 ዓ.ም ጋምቤላ- ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት ህዳር 8 ቀን 2013 ዓ.ም ከረፋዱ 5፡ 30 ላይ በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ “ለሐገር መከላከያ ሠራዊት ክብር እቆማለሁ!” መርሃ ግብር ለአንድ ደቂቃ ያክል ቀኝ እጅን ግራ ደረት ላይ በማሳረፍና ለአንድ ደቂቃ በማጨብጨብ ሥነ -ሥርዓቱ ተካሔዷል ። click Gambella University በሥነ -ሥርዓቱ ላይ አራቱም የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንቶችና ሠራተኞች የተገኙ ሲሆን ዓላማውም ግንባር ላይ ፣ ለሀገር ሉዓላዊነትና የህግ የበላይነትን ለማስከበር በተሠማራበት ሁሉ ከፍተኛ ድል እያስመዘገበ ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሰራዊት በክብር መቆማቸውን ለማሳየት ነው ። ክብርና ሞገስ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት!!
