የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና አካዳሚክ ሠራተኞች ለአገር መከላከያ ሠራዊት የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ ።

ህዳር 09/2013 ዓ.ም ጋምቤላ-ኢትዮጵያ የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳርና አካዳሚክ ሠራተኞች በዛሬው ዕለት ህዳር 09/2020 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ በመሰብሰ በሰሜኑ የሐገራችን ክፍል የህግ የበላይነትን ለማስከበር መስዋዕትነት እየከፈለ ለሚገኘው የሐገር መከላከያ ሠራዊት ከወር ደሞወዛቸው የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ተስማምተዋል። Click here for more...የዩኒቨርሲቲው ሠራተኞች የገንዘብ ድጋፍ ያደረጉት በአመራር ደረጃ የሚገኙና አመራር ደረጃ ባልሆኑ የአስተዳደር ሠራተኛና በመምህርነት ደረጃ ተብሎ ለሁለት በመክፍል ነው ። በአመራር ደረጃ ያልሆኑ የአስተዳደር ሠራተኞችና መምህራን ከወር ደሞዛቸው 10% ለጀግናው የሐገር መከላከያ ሠራዊት ለመስጠት የተስማሙ ሲሆን በከፍተኛ፣ መካከለኛና ዝቅተኛ አመራር ደረጃዎች የሚገኙ ሠራተኞች ደግሞ 20% ከወር ደሞወዛቸው ለመስጠት ቃል ገብተዋል ። በፍላጎትም ማንኛውም ግለሰብ ከወር ደሞወዙ የፈለገውን ያክል መለገስ የሚችል መሆኑን በስብሰባው ላይ ተጠቅሷል ። በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲው እንደ አንድ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም የሚጠበቅበትን ለመወጣት ለሐገር መከላከያ ሠራዊት የሚሆን 1ሚሊዬን ብር ድጋፍ ማድረጉን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡጅሉ ኡኮክ የገለፁ ሲሆን ከራሳቸው የወር ደሞወዝ 40 % ለመስጠትም በመድረኩ ፊት ቃል ገብተዋል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *