
ህዳር 15/2013 ዓ.ም
ጋምቤላ-ኢትዮጵያ
ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የለውጥ አመራርና የካይዘን ስልጠና ሰጠ፡፡ ስልጠናው በተቋማዊ ለውጥ ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት የተሰጠ ሲሆን የስልጠናው ዓላማም በካይዘን አጠቃላይ ጽንሰ ሀሳብና ትግበራ ላይ ግንዛቤ ለማስጨበጥ የተዘጋጀ ነው፡፡ click here for more… ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ከተማ ጥላሁን ሲሆኑ ስልጠናው ከለውጥ መሳሪያዎች አንዱ ስለሆነው ካይዘን በመሆኑና ጠቀሜታው ከፍተኛ ስለሆነ ሁሉም በስልጠናው ላይ የሚሳተፉ ዲኖችና ዳይሬክተሮች በትኩረት እንዲከታተሉና ጥሩ የስልጠና ቆይታ እንዲሆንላቸው በመክፈቻ ንግግራቸው ገልጸዋል፡፡ ስልጠናውንም የሰጡት የኮመን ኮርሶች አስተባባሪና የማኔጅመንት ትምህርት ክፍል መምህር የሆኑት መ/ር ነጻነት ስዩም ሲሆኑ ስልጠናው እስከ ነገ ህዳር 16/2013 ዓ.ም ድረስ የሚሰጥ ይሆናል፡፡
