
ታህሣስ 07/2013 ዓ.ም
ጋምቤላ- ኢትዮጵያ
ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ በኮቪድ 19 ምክንያት ተቋርጦ የቆየውን የመማር ማስተማር ሥራ እንደገና ለማስቀጠል ታህሳስ 5 እና 6 2012 ዓ.ም ለተመራቂ ተማሪዎች ጥሪ በማድረግ በተጠቀው ቀን በመልካም አቀባበል ወደ ዩኒቨርሲቲው ገብተዋል ።
ዩኒቨርሲቲው በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ወቅት የትምህርትና ስልጠና ተቋማት ውስጥ የመማር ማስተማር ሥራን በጥንቃቄ ለመምራት በወጣው መመምሪያ ዙሪያ በዛሬው ዕለት ታህሳስ 07/2013 ዓ.ም ለተመራቂ ተማሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርታዊ ስልጠና ሰጥቷል ።
ስልጠናው በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በወጣው የኮቪድ ፕሮቶኮል መመሪያ መሠረት በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ወቅት በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የመማር ማስተማር ስራው በምን ሁኔታ መመራት እንዳለበት ፣ ተማሪዎች በግቢው ውስጥ በሚቆዩበት ጊዜ ኮቪድን ከመከላካል አንፃር ማድረግ ያለባቸውንና የሌለባቸውን መሠረታዊ ቁምነገሮች ላይ ትኩረት ያደረገ ነበር።
