About

The Federal Democratic Republic of Ethiopia (FDRE) has implemented tremendous development changes in the country and one of the policies designed by the government to bring about rapid and sustainable development is the education and training policy. As it is known there were only two public universities in Ethiopia twenty years ago. Now, the number of public learning institutes have increased more than 45 in the country, among them is the Gambella University which is situated in Gambella People National Regional State (GPNRS) is one of the recently established higher education institutions in Ethiopia. Its cornerstone was laid by FDRE Prime Minister Hailemariam Desalegn and GPNRS president Gatluak Tut on 28th April, 2014.

Gambella University is located at Gambella town, the capital of GPNRS which is 766 km far from Addis Ababa. At the beginning the institution was established as Gambella Agricultural, Technical, Vocational and Educational Training (GATVET) College which was organized and managed by the former Ministry of Agriculture and Rural Development and GPNRS and Bureau of Agriculture and Rural Development from 2002 to 2012 to produce middle level Agricultural Developmental Agents. During ten years (2002-2012) more than 1,950 students were graduated on Animal Science, Natural Resource, Plant Science and Cooperative Departments in the Diploma program / (level IV). Moreover, more than 493 General Agriculture students were graduated within the Certificate Program.

Later on, based on the agreement made between the Ministry of Education and Regional stakeholders, it was affiliated with Mettu University and become the College of Agriculture and Natural Resource campus from 2012 to 2013/14 with (Animal Science, Plant Science, Natural Resource Management and Agricultural Economics) departments.

As an independent institution Gambella University was proclaimed by the Council of Ministry under Proclamation No. 317/2006 and assumes its institutional mandate. Right after, the establishment of Gambella University in 2014 opened a new chapter in the history of the Gambella Region and the people. Soon after, the University was introduced to the public and 514 students were assigned to study in College of

Agriculture and Natural Resource and Faculty of Business and Economics with thirteen Departments and currently there are 31  undergraduate programs and two Colleges   College of Agriculture and Natural Resource, College of Engineering and School of law  Faculty of Business and Economics, Faculty of social Science and Humanity, and Faculty of Natural and  Computational science. Additionally, the university already launch Postgraduate Program in Animal Production independently and three Postgraduate programs (Project Planning and Management, Development Studies and Master of Business Administration) in collaboration with Green Research Development Institute (GRDI).

Even though Gambella University is at its infancy stage, the host region has potential and gifted natural resources (Livestock, Fish, Apiculture, Park, Soil, Forest, Multi Crops and Minerals) and internally committed academic, supporting staff and reliable stakeholders. Based on the university’s strategic plan GmU is „envisaging to be one of the recognized academic and research center in Africa by 2030‟ in its core four strategic pillars namely Educational Quality and Relevance, Research and Technology Transfer, Community Service and Partnership, and Good Governance of the university is to realize it’s given mission by HEI Proclamation No. 650/2009 Article 4.

  1. 1. የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ ገፅታ

ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ዕውቅና ከማግኘቱ በፊት የተገነባው በግብርና ቢሮ ተመርጦ ለገበሬዎች ማሰልጠኛ ማዕከልነት FTC) የተቋቋመ ነበር፤ ይሁን እንጂ በዚህ ፕሮግራም መቀጠል አልቻለም፡፡በ1994 ዓ.ም ወደ ጋምቤላ ግብርና ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ማሰልጠኛ (GATVET) ኮሌጅነት ተቀይሮ በአገር አቀፍ ፕሮግራም ስር ተማሪዎችን ተቀብሎ ማሰልጠን ጀመረ፡፡ከ1994 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 2004 ዓ.ም. ድረስ በመደበኛ፣ በኤክስቴንሽንና በክረምት መርሃ-ግብሮች በዘርፉ እያስተማረ ለ10 ተከታታይ ዓመታት ከ1950 ተማሪዎችን በላይ በዲፕሎማ አስመርቋል፡፡

በ2005 ዓ.ም. ኮሌጁ በመቱ ዩኒቨርሲቲ ሥር በመሆን በግብርናው መርሃ ግብር የመጀመሪያ ዲግሪ በእጽዋት ሳይንስ፣ በእንስሳት ሳይንስ፣ በአግሮ ኢኮኖሚክስና ተፈጥሮ ሃብት ማኔጅመንት በ2005ና 2006 ዓ.ም ተማሪዎችን ተቀብሎ አስተምሯል፡፡

ኮሌጁ ወደ ዩኒቨርሲቲ እንዲያድግ የጋምቤላ ክልል ያቀረበው ጥያቄ ይሁንታ በማገኘቱ ሚያዚያ 20/2006 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝና በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጋትሏክ ቱት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ፡፡ ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ነሐሴ 30 ቀን 2006 ዓ.ም በሚኒስተሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 317/2006 መሰረት እውቅና አግኝቶ በወቅቱ በኮሌጁ ይተዳደሩ የነበሩትን ህንጻዎችና ቁሳቁሶች ከነበረው የሰው ኃይል ጋር በማጣመር ወደ መደበኛ መማር ማስተማር ስራው በይፋ ገባ፡፡

በወቅቱ ዩኒቨርሲቲው ጀማሪ በመሆኑ ከአጎራባች ዩኒቨርሲቲዎች ተሞክሮዎችን በመቀመር የተቋሙ ተልዕኮ፣ራዕይና እሴት እንዲሁም መሪ ቃል ቀርጾ በእቅድ ውስጥ እንዲካተት በማድረግ መደበኛ ስራውን ጀመረ ፡፡ ዩኒቨርሲቲው እንደ ማንኛውም ከፍኛ ትምህርት ተቋም ዓላማውን ለማሳካት በአራት ፕሮገራሞች ማለትም በመማር ማስተማር፣በጥናትና ምርምር፣በማህበረሰብ አገልግሎትና በመልካም አስተዳደር ዘርፍ እየሰራ የሚገኝ ሲሆን በ2022 በአፍሪካ ደረጃ ታዋቂ   የመማር ማስተማርና የምርምር ማእከል የመሆን ራዕይ ሰንቆ እየሰራ ይገኛል ፡፡

 ዩኒቨርሲቲው ከተመሰረተ ጥቂት ዓመታትን ቢያስቆጥርም ባነገበው በፍጥነት የማደግ ተስፋ በአፍሪካ ውስጥ በ2022 አንዱ የምርምርና ልህቀት ማዕከል ለመሆን ያቃደውን ራዕይ መሬት ያወርድ ዘንድ በክልሉ ያለውን እምቅ የተፈጥሮ ሃብት በመጠቀም (ዓሳ፣ፓርክ፣ አፈርና ውሃ፣ የቁም እንስሳት፣ እጽዋት፣ አዝዕርት እንዲሁም ሌሎች ማዕድናትን) ቁርጠኛ ከሆኑ ምሁራንና አጋዥ አካላት ጋር በመሆን በጥናትና ምርምር ዘርፍ ተስፋ ሰጭ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል ፡፡

ከአምስት ዓመት በፊት መሰረት የተቀመጠለት ይህ ዩኒቨርሲቲ የመማሪያ ክፍልና የተማሪዎች መኝታ ክፍሎች እጥረት በወቅቱ የነበረበት ቢሆንም ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመነጋገር አስራ አንድ ህንጻዎች በአፋጣኝ ተገንብተው ለአገልግሎት በቅተዋል፡፡

በዚህ መሰረት ከዓመት ወደ ዓመት የቅበላ አቅሙን እያሳደገ በመምጣትና ፕሮግራሞቹን በማስፈት በ2012 ዓ.ም በግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ፤ በምህንድስናና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ፤ በቢዝነስና ምጣኔ ሐብት ፋካሊቲ፤ በማህበራዊና ሥነ-ሰብ ፋካሊቲ፤በተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ፋካልቲ፣ በህግ ትምሀርት ቤትና ድህረ ምረቃ ትምሀርት ቤት የታቀፈ ሲሆን በአጠቃለይ በ31 ትምህርት ክፍሎችና በ4 ድህረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመማር ማስተማር ስራውን እያከናወነ ይገኛል ፡፡

ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ በሃገራችን ከሚገኙ 45  የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መከካከል አንዱ ሲሆን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በበርሃዋ ገነት ጋምቤላ ከተማ የሚገኝ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ነው፡፡ዩኒቨርሲቲው ነሐሴ 30/ 2006 ዓ.ም በሚኒስቴሮች ም/ቤት አዋጅ ቁጥር 317/2006 ተቋቁሞ ስያሜውን ካገኘ በኋላ እንደ ከፍትኛ ትምህርት ተቋም ብቁና ተወዳዳሪ የሰው ሃይል በማፍራት ረገድ  አገራችን የጀመረችውን የዕድገት ጎዳና ለማስቀጠል፡-

  • በ2007 ዓ.ም 947 ተማሪዎችን ተቀብሎ በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም ማለትም በግብርናና ተፈጥሮ ሃብት ኮሌጅና በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ፋክሊቲ በድምሩ በ13 ዲፓርትመንቶች ማስተማሩን ቀጠለ፡፡ በዚህ ዓመት በመቱ ዩኒቨርሲቲ ስር ከነበሩት በመደበኛው መርሃ-ግብር ወንድ 131 ሴት 57 ድምር 188 በእረፍት ቀናት መርሃ-ግብር ወንድ 98 ሴት 30 ድምር 128 በድምሩ 316 ተማሪዎችን ለመጀመሪያ ጊዜ ለማስመረቅ ችሏል፡
  • በ2008 ዓ.ም በ4 ፋካሊቲ በ18 ትምህርት ክፍሎች 1,668 ተማሪዎችን በመቀበል እና በመቱ ዩኒቨርሲቲ ስር ከነበሩት በመደበኛው መርሃ-ግብር ወንድ 201 ፣ሴት 75፣ ድምር 276  በእረፍት ቀናት መርሃ-ግብር  ወንድ 42 ፣ሴት 8 ፣ድምር 50   በድምሩ 326 ተማሪዎችን አስመርቋል ፡፡
  • በ2009 ዓ.ም በ5 ፋካሊቲ በ27 ትምህርት ክፍሎች 2,176 ተማሪዎችን በመቀበል በመደበኛው መርሃ-ግብር ወንድ 226 ሴት 217 ድምር 443 ፣ በእረፍት ቀናት ወንድ 120 ሴት 35 ድምር 155፣ በክረምት መርሃ-ግብር ወንድ 248 ሴት 23 ድምር 271 በድምሩ 869 ተማሪዎችን ለማስመረቅ ችሏል፡፡
  • በ2010 ዓ.ም በ1 ኮሌጅ በ4 ፋካሊቲ በ2 ትምህርት ቤቶች እና በ31 ትምህርት ክፍሎች 3,978 ተማሪዎችን በመቀበል በመደበኛው ወንድ 446 ሴት 293 ድምር 739 በእረፍት ቀናት ወንድ 143 ሴት 40 ድምር 183 ፣ በክረምቱ መርሃ-ግብር ወንድ 39 ሴት13 ድምር 52፣ በድምሩ 974 ተማሪዎችን አስመርቋል ፡፡
  • በ2011 ዓ.ም በ2 ኮሌጅ በ3 ፋካሊቲ በ2 ትምህርት ቤቶች እና በ31 ትምህርት ክፍሎች 5,015 በቅድመ ምረቃ 330 በድህረ-ምረቃ ፕሮግራም በድምሩ 5,345 ተማሪዎችን በመቀበል በመደበኛ መርሃ-ግብር ወንድ 354 ሴት 194  ድምር 548 ፣  በእረፍት ቀናት ወንድ 277 ሴት 57 ድምር 334  ፣ በክረምት መረሃ -ግብር ወንድ 40፣ ሴት10፣  ድምር  50 በድምሩ 932 ፣በሁለተኛ ዲግሪ በእረፍት ቀናት መርሃ-ግብር ወንድ 49 ሴት 1 ድምር 50 ተማሪዎች በጠቅላላ 982 ተማሪዎች አስመርቋል ፡፡ ባጠቃላይ ከ2007 -2011 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ  በመደበኛው፣ በእረፍት ቀናትና  በክረምት መርሃ-ግብሮች 3,289 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡
  • በ2012 ዓ.ም በ2 ኮሌጀች፣ በ3 ፋካሊቲዎች፣በአንድ ህግ ትምህርት ቤት፣ በድህረ-ምረቃ ትምህርት ቤትና  እና በ31 ትምህርት ክፍሎች በቅድመ ምረቃ በመደበኛው ወንድ 2,183 ሴት 1,284 ድምር 3,467 ፣ በቅድመ-ምረቃ በእረፍት ቀናት ወንድ 1,361 ሴት 412 ድምር 1,773 ፣ በቅድመ-ምረቃ በክረምት መርሃ ግብር ወንድ 382 ሴት 137 ድምር 519  ጠቅላላ በቅድመ-ምረቃ  መርሃ ግብር ወንድ 3,926 ሴት 1,833 ድምር 5,759 ፣በድህረ -ምረቃ ፕሮግራም በእረፍት ቀናት ወንድ 253 ሴት 16 ድምር 269  በጠቅላላ ዩኒቨርሲቲው  6,028 ተማሪዎችን ተቀብሎ እያስተማረ ይገኛል፡፡
  • ዩኒቨርሲቲው የሰው ኃይልን ከማሟላት አንፃር 770  የአስተዳደር ሠራተኞች  እምዲሁም 544 የሀገር ውስጥ መምህራንና 34 የውጭ ሀገር መምህራን ያሉት ሲሆን  በአጠቃላይ 1348 ሠራተኞች አሉት፡፡
Share the contents abroad