በዛሬው ፈጣን አለም ባላሰለሰ ትምህርት እና የክሂሎት እድገት ውስጥ መሳተፍ ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ እጅግ አስፈላጊ ሆኗል። በረፍት ላይ ላላችሁ ተማሪዎች፣ ለወጣት ባለሞያዎች፣ ራሳቸሁን በእውቀት በመገንባት በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ በጎ ተፅዕኖ ለመፍጠር ለምትጓጉ ሁሉ የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ ፕሮጀክት ቀዳሚ ሊያደርጋችሁ ተሰናድቶላችኋል። የትምህርት እና የእውቀት መነሻችሁ እና ያላችሁበት ደረጃ ምንም ይሁን ያላችሁን ክሂሎት ለማሳደግም ሆነ አዲስ ነገር ለማወቅ ለምትሹ ሁሉ ሰፊ የእድል በር ተከፍቶላችኋል። በመላው ኢትዮጵያ ያላችሁ የክሂሎት አበልፃጊዎች፣ አሣዳጊዎች፣ ዩኒቨርሲቲዎች ይኽንን ፕሮጀክት እና እንቅስቃሴዎቹን እንዲደግፉ ጥሪ አቀርባለሁ። ውድ ባለተሰጥዖዎች ፣ የኢትዮጵያችን ጥንካሬ በእናንተ እድገት ላይ የተመሠረተ ነው። ለመመዝገብ: http://www.ethiocoders.et In today’s fast-paced world, continuous learning and skills development are more important than ever. To all students on break, young professionals, and those eager for personal growth and making a positive impact locally and beyond: the 5 Million Coders initiative has been launched to help you stay ahead, regardless of your career stage or goals. Whether you’re looking to enhance your current skills, learn something new, or prepare for future opportunities, this initiative is designed for you. I also strongly encourage everyone involved in skill-building in Ethiopia—incubators, accelerators, universities, and others—to fully embrace this initiative. Our nation’s strength lies in your growth!” Register through: http://www.ethiocoders.et
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ስልጠና እና የበጎ ፍቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎች ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ፤
ሰኔ 14/2016 ዓ.ም ጋምቤላ-ኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ስልጠና እና የበጎ ፍቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎች ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ፤ ፕሮግራሙን ሰላም ሚኒስቴርና ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ በመተባበር ያዘጋጁት ሲሆን የክረምት በጎ ፍቃድ ተማሪዎች ለአምስት ቀናት ያህል በሰላም ግንባታ፣ በብሄራዊ መግባባትና በማህበራዊ ትስስር ዙሪያ ስልጠና ከወሰዱ በኋላ ለ25 ቀናት ደግሞ የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎችን የሚያከናውኑ ይሆናል። በዚህ የክረምት በጎ ፍቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎች ላይ 465 ተማሪዎች የሚሳተፉ ይሆናል።
ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ተፈታኞችን እየተቀበለ ይገኛል፤
ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የ2016 ዓ.ም የአገር-አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና በመጀመሪያ ዙር የሚፈተኑ በቁጥር 6175 የሚሆኑ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎችን ከቀን 30/10/2016 ዓ.ም ጀምሮ በመቀበል ላይ ይገኛል፡፡ ዉድ ተማሪዎቻችን እንኳን ወደ ነገዉ ዩኒቨርሲቲያችሁ በሠላም መጣችሁ እያልን በዩኒቨርሲቲያችን ዉስጥ መልካም የቆይታ እና የፈተና ጊዜ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን፡፡
የ2016 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆነ
*************** (ኢ ፕ ድ) የ2016 የትምህርት ዘመን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆነ። የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ሐምሌ 3-5 ለማህበራዊ ሳይንስ፤ ሐምሌ 9-11 ቀን 2016 ዓ.ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በበይነ መረብና በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በወረቀት ይሰጣል። የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ከሰኔ 30 እሰከ ሐምሌ 01ቀን 2016 ዓ.ም እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ሐምሌ 6-7 ቀን 2016 ዓ.ም ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ይሆናል። ተፈታኞችና የሚመለከታቸው ሁሉ ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳስቧል። ሚያዝያ 21 ቀን 2016 ዓም