News Detail

ክስተቶች
Nov 10, 2025 289 views

የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ደሊቨሮሎጂና መምህራን ልማት ማስተባበሪያ ለአዲስ ተቀጣሪ መምህራን ስልጠና ሰጠ፤

The Executive Director of the Women and Social Affairs Unit of the University of Gambella, in collaboration with the Gambella Regional State Office of HIV/AIDS Prevention and Control, provided an awareness training to students;

ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት (ህዳር 1/2018 ዓ.ም)

በአካዳሚክ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ስር የሚገኘው የመምህራን ልማትና ደሊቨሮሎጂ ማስተባበሪያ ያዘጋጀውን ስልጠና በዛሬው እለት አዲስ ለተቀጠሩ መምህራን ስልጠናውን እየሰጠ ይገኛል፡፡

በዚሁ ወቅት የአካዳሚክ፣ ምርምር ፣ ማህበረሰብ አገልግሎትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንትና ልዩ ረዳት ጀምበሩ አለሙ (ዶ/ር) እንደገለጹት ውጤታማ መማር ማስተማር እንዲኖር ከሚያስችሉ ዘዴዎች መካከል አንዱ የማስተማር ስነ-ዜዴ በመሆኑ በሚሰጣችሁ የኢንዳክሽን ስልጠና ውስጥ ተካቶ ስለሚገኝ ተሳታፊዎች ስልጠናውን በጥሞና እንዲከታተሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ስልጠናውን እየሰጡ የሚገኙት ከዚህ ቀደምም በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የኢንዳክሽን ስልጠና ሲሰጡ የነበሩት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህርና ተመራማሪ ደሱ ዊርቱ ሁንዴሳ (ዶ/ር) ሲሆኑ ስልጠናው እስከ ነገ ህዳር 2/2018 ዓ.ም ድረስ ቀጥሎ የሚሰጥ ይሆናል፡፡

 

Recent News
Follow Us