News Detail

ክስተቶች
Apr 21, 2026 471 views

የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጅ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት የመንገድ ደህንነትን አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያየ፡፡

ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት (ሚያዝያ 13/2018 ዓ.ም )

የዩኒቨርሲቲው ቴክኖሎጅ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት የመንገድና የትራንስፖርት አገልግሎት ደህንነትን አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡

ውይይቱን በጋራ የመሩት የዩኒቨርሲቲው መምህራን ዴቪድ ዋንግ እና ቻር ሉዋል እንደገለጹት የውይይቱ ዋና ዓላማ ደህንነቱ የተጠበቀ የመንገድና የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲኖር ግንዛቤ ለመስጠትና የተጠናከረና ቀጣይነት ያለው የክትትልና ግምገማ ስርዓት እንዲኖር ለማድረግ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በውይይቱ ላይ የተገኙት የክልሉ የተሸከርካሪ ማህበራት ተወካዮች፣ የትናስፖርት አገልግሎት ባለሙያዎችና የቀበሌ አመራሮች በበኩላቸው በትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የሚታየው የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ ፣ የመንገድና የመናኸሪያ የጽዳት ሁኔታ እንዲስተካከል እንዲሁም ከከተማ እስከ ወረዳ ድረስ ደህንነቱ የተጠበቀ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲኖር አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

በመጨረሻም የዩኒቨርሲቲው አስተዳደርና ቢዝነስ ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዮናስ ከፍያለው የዩኒቨርሲቲው ዋና ተልዕኮ መማር ማስተማር፣ ምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት መስጠት መሆኑን በመግለጽ በቀጣይ የመንገድና የትራንስፖርት አገልግሎት ችግሮችን ለማስተካከል በማህበረሰብ አገልግሎት በኩል ከክልሉ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይቱ እንደሚደረግና ቀጣይነት ያለው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እንደሚሰጡ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

Recent News
Follow Us