News Detail

ክስተቶች
Apr 09, 2026 503 views

የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት ለምርቃት ብቁ የሆኑ ተማሪዎችን ውጤት ገምግሞ አፀደቀ፤

ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት (ሚያዝያ 1/2018 ዓ.ም)

የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት በያዝነው 2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለምርቃት ብቁ የሆኑ ተማሪዎችን ውጤት ገምግሞ አጽድቋል።

የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ድሪባ ኢትቻ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት ባለፉት ሶስት ሩብ ዓመታት ዩኒቨርሲቲው በጥሩ አፈጻጸም ላይ እንደሚገኝ ገልጸው ለመመረቅ ብቁ የሆኑ ተማሪዎችን ሴኔቱ ገምግሞ እንዲያጸድቅ አሳስበዋል።

የሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክተር መ/ር አየለ ያያ ለምርቃት ብቁ የሆኑ ተማሪዎችን ውጤት በዝርዝር ለሴኔቱ አቅርበዋል።

በዚህም መሠረት ሴኔቱ ውይይት ካደረገ በኋላ 123 ተማሪዎች የሚጠበቅባቸውን መስፈርት አሟልተው የተገኙ በመሆናቸው እንዲመረቁ በሙሉ ድምፅ ወስኗል።

Recent News
Follow Us