News Detail
የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በጀዌ ስደተኛ ጣቢያ ለሚገኙ ስደተኞች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።
ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት (መጋቢት 26/2018 ዓ.ም)
የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አገልግሎትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት በጀዌ ስደተኛ ጣቢያ ለሚገኙ ስደተኞች ስለ ውጤታማ ግንኙነት (Effective Communication) ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።
ስልጠናውን በንግግር ያስጀመሩት የጀዌ ስደተኞች ማዕከል የፕሮቴክሽን ኃላፊ አቶ መብራህቶም ገ/ዮሐንስ እንደገለጹት እንደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ይህንን ተነሳሽነት ወስዶ ለስደተኞች ስልጠና ለመስጠት ወደ ማዕከሉ መምጣቱን አመስገነው ስደተኞች እህትና ወንድሞቻችን ከአካባቢው ነባር ህዝቦች ጋር በፍቅር፣ በመከባበርና በአንድነት እንዲኖሩ የሚያደርጋቸው ዋነኛው ቁልፍ ነገር ውጤታማ ግንኙነት (Effective Communication) ነው ብለዋል።
በቀላሉ ልንፈታቸው የምንችላቸው ጉዳዮች ባልጠበቅነው ፍጥነት ወደ ግጭት የሚያመሩት በመካከላችን ውጤታማ ግንኙነት ባለመኖሩ ነው።
ስለሆነም ይህ ስልጠና ስደተኞችና የበአካባቢው ነባር ህዝቦች መካከል መልካም ግንኙነትን ለመፍጠርና በሰላም አብሮ ለመኖር ዓይነተኛው መንገድ እንደሆነ አቶ መብራህቶም ገልጸዋል።
ስልጠናውን እየሰጡ የሚገኙት ደግሞ የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ኃላፊና በማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ፋካሊቲ የአለም አቀፍ ግንኙነትና ፖለቲካል ሳይንስ መምህር የሆኑት ዶ/ር ናርዶስ ሀዋዝ ናቸው።
በስልጠናው ላይ አንድ መቶ የሚሆኑ ሰልጣኞች እየተሳተፉ የሚገኝ ሲሆን ስልጠናው ነገም ቀጥሎ የሚውል ይሆናል።