News Detail

ክስተቶች
Apr 02, 2026 285 views

የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ዳይሬክቶሬት ለመካከለኛ የአመራሮች የአመራርነት ክህሎት ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፤

ህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት (መጋቢት 24/2018 ዓ.ም)

የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ፕሮግራሞች ዳይሬክቶሬት ለዲኖች፣ ለዳይሬክተሮች እና ለስራ አስፈጻሚዎች የአመራርት ክህሎት ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፤

በዚሁ ወቅት ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ፣ ምርምር፣ ቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ተወካይና ልዩ ረዳት ዶ/ር ጀምበሩ አለሙ እንደገለጹት በፍጥነት እየተለዋወጠ በሚገኘው የትምህርት ዓለም ውስጥ አመራርነት (Leadership) በአቋምና ወንበር በመያዝ ብቻ የሚገለጽ ሳይሆን ሌሎችን በማሳመን፣ በትብብርና በፈጠራ ለአንድ የጋራ ዓላማ በማነሳሳት የተቋምን ራዕይ ከግብ ማድረስ ነው ብለዋል፡፡

ዶ/ር ጀምበሩ አክለው እንደተናገሩት ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የአካባቢውን ጸጋ መሰረት ያደረጉ የትኩረት መስኮች ያሉት ሲሆን እነዚህንም የትኩረት መስኮች ለማሳካት ብቁ ብቻ ሳይሆን አብሮ በመስራት ለቀጣይ እድገት ቁርጠኛ የሆኑ መሪዎችን ይጠይቃል፤ በመሆኑም ይህ ስልጠና የእነዚህን መሪዎች አቅም ለማጠናከር የተነደፈ በመሆኑ በአመራር ልምዶቻችን ላይ ለመወያየት፣ እርስ በእርስ ለመማማር እና እንደ መካከለኛ አመራሮች ውጤታማነታችንን የሚያሳድጉ ተግባራዊ አቀራረቦችን ለመዳሰስ እድል የሚከፍት መሆኑን ገልጸው ሰልጣኞች ስልጠናውን በንቃት እንዲከታተሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ስልጠናው ነገም ቀጥሎ የሚውል ይሆናል፡፡

Recent News
Follow Us