News Detail

ክስተቶች
Nov 09, 2025 392 views

የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮችአካቶ ትግበራ ስራ አስፈጻሚ ከጋምቤላ ክልል ኤች. አይ. ቪ. ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ለተማሪዎች የግንዛቤ ማሰጨበጫ ስልጠና ሰጠ፤

ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት (ጥቅምት 29/2018 ዓ.ም)

የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ስራ አስፈጻሚ ከጋምቤላ ክልል ኤች. አይ. ቪ. ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ለዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች የግንዛቤ ማሰጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል፤

ስልጠናውን ያስጀመሩት የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ፣ምርምር፣ቴክኖሎጅ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ተወካይና ልዩ አማካሪ ዶ/ር ጀምበሩ ዓለሙ ኤች አይ ቪ ወጣቱንና አምራች ዜጎችን አያጠቃ ያለ አደገኛ በሽታ በመሆኑ ተማሪዎች የሚሰጣቸውን ስልጠና በሚገባ ተከታትለውና የተሻለ እውቀት አግኝተው ከዚህ ገዳይ በሽታ እራሳቸውን እንዲጠብቁ አስተላልፈዋል።

የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ምህረት ከበደ ስልጠናው በየዓመቱ የሚሰጥ መሆኑን ገልፀው የስልጠናው ዓላማ ተማሪዎች የተሻለ ግንዛቤ አግኝተው ራሳቸውን ከበሽታው እንዲጠብቁና በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የደም ምርመራ አድርገው ራሳቸውን እንዲያውቁ ለማድረግ ነው ብለዋል።

ስልጠናውን የሰጡት የክልሉ ኤች. አይ.ቪ. ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት ባለሙያዎች አቶ ሲሳይ ተመስገንና አቶ ብርሃኑ አሰፋ ሲሆኑ ኤች. አይ. ቪ. ኤድስ በዓለማችን መከሰቱ ከታወቀበት እ.ኤ.አ ከ1981 ጀምሮ ከ39 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በዚሁ በሽታ ምክንያት ህይወታቸውን እንዳጡ ገልፀው በየዓመቱ በኤች. አይ.ቪ የሚያዙ 1.2 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች እንዳሉና 630,000 ሰዎች ለህልፈት እንደሚዳረጉ መረጃዎች ያሳያሉ ብለዋል።

በተጨማሪም ተማሪዎች በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የደም ምርመራ አድርገው ውጤታቸውን ያወቁ ሲሆን በቀጣይ ስልጠናው ይበልጥ ተጠናክሮ የሚሰጥ መሆኑ ተገልጸል።

 

Recent News
Follow Us