News Detail

ክስተቶች
Mar 28, 2026 286 views

የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በቢዝነስ ኢንኩዩቤሽን እና ፈጠራ ላይ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፤

ህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት (መጋቢት 19/2018 ዓ.ም)

የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በቢዝነስ ኢንኩዩቤሽን እና ፈጠራ ላይ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።

ስልጠናው ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ፣ ምርምር፣ ማህበረሰብ አገልግሎትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ተወካይ እና ልዩ ረዳት ዶ/ር ጀምበሩ አለሙ እንደገለጹት ይህ ስልጠና የቢዝነስ ሀሳብ ያላቸው መምህራን እና ተማሪዎች ሀሳባቸውን ወደ ተጨባጭ ቢዝነስ ለመቀየር የሚያስችላቸውን እውቀት የሚጨብጡበት በጣም ጠቃሚ ስልጠና መሆኑን አስገንዝበዋል።

በመጨረሻም ተሳታፊዎች ስልጠናውን በንቃት እንዲከታተሉ አሳስበዋል።

በስልጠናው ላይ ከጋምቤላ ከተማ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፣ ከጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የፌዴራል አዳሪ ትምህርት ቤት እና ከጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ለተመረጡ ተማሪዎች እና መምህራን እየሳተፉ ይገኛሉ።፡

)

Recent News
Follow Us