News Detail
Mar 26, 2026
301 views
የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት ለመምህራን የከፍተኛ ዲፕሎማ ፕሮግራም ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፤
ህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት (መጋቢት 18/2018 ዓ.ም)
የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት ለመምህራን የከፍተኛ ዲፕሎማ ፕሮግራም ስልጠና እየሰጠ ይገኛል። ስልጠናው መምህራን በከፍተኛ ትምህርት ተቋም ለማስተማር የሚያስችላቸውን እውቀት የሚጨብጡበት ሲሆን አብዘሀኞቹ መምህራን ከዚህ በፊት ስልጠናውን ወስደው አጠናቀዋል።
በስልጠናው ላይ ቁጥራቸው ከ 60 በላይ የሚሆኑ መምህራን እየተሳተፉ ሲሆን ስልጠናውን ወስደው ሲያጠናቅቁ የምስክር ወረቀት የሚያገኙ ይሆናል።