News Detail
Dec 01, 2026
512 views
ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የተቀናጀ የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር መረጃ ስርዓት ትግበራ ማስጀመሪያ ውይይት ተካሄደ፡፡
ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የተቀናጀ የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር መረጃ ስርዓት ትግበራ ማስጀመሪያ ውይይት ተካሄደ፡፡
ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ( ጥር 6/2018 ዓ.ም)
በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የተቀናጀ የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር መረጃ ስርዓት (IFMIS) በይፋ መጀመሩ በዛሬው ዕለት ተበስሯል፡፡
ዛሬ ጥር 6/2018 ዓ.ም የፋይናንስ፣ የግዥ፣ የብቃትና ሰው ሀብት፣ የስትራቴጂክ ጉዳዮች፣ የንብረት፣ የውስጥ ኦዲት፣ የኢ.ኮ.ቴና ሌሎች አዲሱ የፋይናንስ አሰራር ስርዓት በቀጥታ የሚመለከታቸው ስራ አስፈጻሚዎችና ባለሙያዎች በተገኙበት የገንዘብ ሚኒሴቴር የIFMIS ባለሙያዎች በፋይናንስ አሰራር ስርዓቱ ዙሪያ ገለጻ አድርገዋል፡፡
በውይይቱ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ፣ ምርምር፣ ማህበረሰብ አገልግሎትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንትና የፕሬዝዳንቱ ተወካይ ዶ/ር ፓል ቦት አንደገለጹት በአሁኑ ሰዓት 43 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የተቀናጀ የፋናንስ አስተዳደር መረጃ ስርዓትን በስራ ላይ ማዋላቸውን ገልጸው የመንግስትን ውስን ሀብት በአግባቡና በተቀላጠፈ ሁኔታ ለመጠቀም የሚያስችል ስርዓት ሲሆን ለወረቀትና ለፕሪንተር የሚወጣውን ወጪ በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል ብለዋል፡፡
ስልጠናውን የወሰዱ ባለሙያዎች ከአሰራር ስርዓቱ ጋር በደንብ አንዲተዋወቁ ተከታታይ ልምምዶችን እና ችግሮች ሲያጋጥሟቸው የገንዘብ ሚኒስቴር ድጋፍ ሰጪ ባለሙያዎች ጋር በመነጋገር ስራቸውን እንዲያከናውኑ አሳስበዋል፡፡
የገንዘብ ሚኒስቴር የተቀናጀ የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር መረጃ ባለሙያ አቶ በዛብህ አረፈዓይኔ ገለጻውን የሰጡ ሲሆን አስከ አሁን ድረስ ስርዓቱን ለማስጀመር በርካታ ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን ገልጸው ከጥር 1/2018 ዓ.ም ጀምሮ የተቀናጀ የፋይናንስ አስተዳደር መረጃ ስርዓት /IFMIS/ በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የተጀመረ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በቀጣይ ጊዜያት የሚቀሩ ስራዎችን በማጠናቀቅ ባለሙያዎቹ ስርዓቱን በትክክል መፈጸም ሲችሉ ርክብክብ እንደሚደረግ የገለጹት አቶ በዛብህ እስከ ሚያዝያ 2018 ዓ.ም ድረስ ለባለሙያዎች የተለያዩ ድጋፎችን እና የስራ ላይ ስልጠናዎችን በመስጠት ቀሪ ስራዎች ይጠናቀቃሉ ብለዋል፡፡