News Detail

ክስተቶች
Mar 09, 2026 255 views

የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አገልግሎትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ለተመረጡ ክልል ሴክተር መስሪያ ቤት ባለሙያዎች የኮምፒውተር ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፤

ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት (የካቲት 30/2018 ዓ.ም)

የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አገልግሎትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ለክልሉ ሴክተር መስሪያ ቤት ባለሙያዎች የኮምፒውተር ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፤

የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አገልግሎትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት በክልሉ የተለያዩ ዞኖችና ወረዳዎች በመንቀሳቀስ እውቀት መር የማህበረሰብ አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን ይህ ስልጠና ግን የተዘጋጀው የክልል መስሪያ ቤት ባለሙያዎች መሰረታዊ የኮምፒውተር እውቀታቸውን አዳብረው የተቀላጠፈ አገልግሎት በመስጠት ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ለማስቻል እንደሆነ የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ፣ ምርምር፣ ማህበረሰብ አገልግሎትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ተወካይና ልዩ ረዳት ዶ/ር ጀምበሩ አለሙ ስልጠናውን ባስጀመሩበት ወቅት ተናግረዋል፡፡

ዶ/ር ጀምበሩ አክለው እንደገለጹት ዘመኑ የዲጅታል ዘመን አንደመሆኑ መጠን የኮፒውተር እና የቴክኖሎጂ እውቀት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸው ስልጠናው የተሳካ እና ያማረ እንዲሆን ተመኝተዋል፡፡

ስልጠናው መሰረታዊ የኮምፒውተር እውቀት በተጨማሪ የመረጃ ደህንነት Cyber Security) እና የፋይል አያያዝን የሚያካትት ሲሆን ለተከታታይ አምስት ቀናት የሚሰጥ ይሆናል፡፡

Recent News
Follow Us