News Detail

ክስተቶች
Feb 19, 2026 227 views

የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ግዥ ስራ አስፈጻሚ በግዥ ጨረታ ላይ ለሚሰሩ ባለድርሻ አካላት ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፤

የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ግዥ ስራ አስፈጻሚ በግዥ ጨረታ ላይ ለሚሰሩ ባለድርሻ አካላት ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፤

ህዝባነ ዓለም አቀፍ ግንኙነት(የካቲት 12/2018 ዓ.ም)

የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ግዥ ስራ አስፈጻሚ በግዥ ጨረታ ላይ ለሚሰሩ ባለድርሻ አካላት ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፤ ስልጠናው በዋናነት ትኩረት ያደረገባቸው ነጥቦች ተግባርና ኃላፊነት፣መሰረታዊ የመንግስት ግዥ ድንጋጌዎች፣ የግዥ ዘዴ፣ የግዥ ሥልት፣የግንባታ ሥራ ግዥ አፈጻጸም፣ የጨረታ ሥነ-ስርዓት፣ የግዥ ውል አስተዳደርና የውል አለመግባባቶች የሚፈቱበት ሥርዓት፣ አቤቱታ እና ይግባኝ አቀራረብና አወሳሰን ሥርዓት፣ የጥፋተኝነት ሪፖርት አቀራረብ እና ልዩ ልዩ ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች የሚሉት ናቸው::

ስልጠናውን እየሰጡ የሚገኙት በመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን የግዥ ስልጠና ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ውብሸት መንግስት ሲሆኑ ስልጠናው እስከ ነገ የካቲት 13/2018 ዓ.ም ቀጥሎ ሚውል ይሆናል።

Recent News
Follow Us