News Detail
Apr 25, 2026
523 views
ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ በተማሪዎች ሰላም ፎረም አስተባባሪነት የተማሪዎች ስፖርት ፌስቲቫል አካሄደ፤
ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት (ሚያዝያ 17/2018 ዓ.ም)
የዩኒቨርሲቲው ሰላም ፎረም በተማሪዎች መካከል ሰላምን፣ ወንድማማችነትን እና አብሮነትን ለማጠናከርበየተማሪዎች መካከል የስፖርት ውድድሮች ተካሂደዋል።
በስፖርት ውድድሩ ላይ ትገኝተው ንግግር ያደረጉት የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መሰረታዊ አግልግሎት ዲን ዶ/ር ተስፋዬ ዱጋሳ የስርፖርት ውድድሩ ከእንቅስቃሴና የስፖርት ክህሎትን ከማሳደግ ባለፈ ለሰላምና ለወዳጅነትን የሚሰብክ መሆን ይገባዋል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በጧቱ ፕሮግራም የሩጫ ውድድር የተካሄደ ሲሆን ከሰዓት በኋላ ደግሞ የእግር ኳስ ጨዋታ ተደርጓል።
እንደዚህ ዓይነት መሰል ውድድሮች በየጊዜው መካሄዳቸው አቅም ያላቸው ተማሪዎች እንዲመረጡና ዩኒቨርሲቲውን ወክለው የተለያዩ ውድድሮች ላይ እንዲሳተፉ እድል የሚፈጥር ሲሆን ዩኒቨርሲቲው ዘንድሮ በተካሄደው 10ኛው የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ስፖርት ፌስቲቫል ላይ በመሳተፍ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበ መሆኑ ይታወሳል።