News Detail
Feb 18, 2026
205 views
የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አገልግሎትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ከጋምቤላ ከተማ ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ ተማሪዎች ስለመንገድ ደህንነት ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡
ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት (የካቲት 10/2018 ዓ.ም)
የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አገልግሎትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ከጋምቤላ ከተማ ለተውጣጡ በጎ ፍቃደኛ ተማሪዎች የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ የሚያስችል የመንገድ ደህንነት ስልጠና እየሰጠ ነው፡፡
የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ፣ ምርምር፣ ማህበረሰብ አገልግሎትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፓል ቦት በዚሁ ወቅት እንደገለጹት ተማሪዎች ይህንን ስልጠና በመውሰድ ከሚመለከታቸው የትራፊክ ፖሊስ አባላት ጋር በመተባበር በከተማችን እየደረሰ ያለውን የትራፊክ አደጋ ለመከላከልና ለመቀነስ በጋራ እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡
የማህበረሰብና ቴክኖሎጂ ሽግግር መምህር ገብረእግዚአብሄር አሳየኸኝ በበኩላቸው ተማሪዎችም ሆኑ ወላጆች መንገድ በሚያቋርጡበት ወቅት ለትራፊክ አደጋ እንዳይጋለጡ በማገዝ ተማሪዎች የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡
ስልጠናውን እየሰጡ የሚገኙት የአደጋ ስጋትና ዘላቂ ልማት ትምህርት ክፍል ሀላፊ የሆኑት አደላ ተመስገን ሲሆኑ ስልጠናው እስከ ነገ የካቲት 11/2018 ዓ.ም ድረስ የሚቀጥል ይሆናል፡፡