News Detail

ክስተቶች
Feb 15, 2026 179 views

ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ለስፖርት ልዑካን ቡድን የምስጋና ፕሮግራም አዘጋጀ።

ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት (የካቲት 7/2018 ዓ.ም)

ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ በጅማ ዩኒቨርሲቲ በተዘጋጀው 10ኛው የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የስፖርት ፌስቲቫል ላይ ለተሳተፉ የስፖርት ልዑካን ቡድን የምስጋና ፕሮግራም አዘጋጀ።

የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ድሪባ ኢትቻ ልዑካን ቡድኑ በውስን የስፖርት አይነቶች ተሳትፎ ውጤት ይዞ መመለሱ ብቻ ሳይሆን ክልሉን እና ዩኒቨርሲቲውን በማስተዋወቅ እንዲሁም ተቋሙ ወክሎ ከሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች በተሻለ ደረጃ እንዲገኝ በጋራ በመስራት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል።

አያይዘውም ፕሬዝዳንት ዶ/ር ድሪባ ኢትቻ ዘንድሮ በተካሄደው ውድድር በ5 ጨዋታዎች ብቻ የተሻለ ውጤት ሊመዘገብ በመቻሉ በሚቀጥለው ዓመት ሌሎች የስፖርት ዓይነቶችንና የተሻለ ተሳትፎ ያላቸው ተጫዋቾችን በመጨመር እና የስፖርት ቁሳቁሶችን በማሟላት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸው የስፖርት አካዳሚ በማቋቋም በክልሉ ያለውን የስፖርት አቅምና ተሰጥኦ በመጠቀም ከዩኒቨርሲታው በተጨማሪ ክልሉን ማስተዋወቅ እንደሚገባ ገልፀዋል።

በመጨረሻም ለአሰልጣኞችና አስተባባሪዎች እንዲሁም ለስፖርተኞች በዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንትና ምክትል ፕሬዝዳንቶች የምስጋና የምስክር ወረቀት የተበረከተላቸው ሲሆን በተጨማሪም ለልዑካን ቡድኑ የምሳ ግብዣ ተደርጎላቸዋል።

Recent News
Follow Us