News Detail

ክስተቶች
Feb 12, 2026 206 views

የተፈረመውን የአፈጻጸም ስምምነት መሠረት በማድረግ ሁሉም ባለድርርሻ አካላት ዕቅዳቸውን ሊፈፅሙ እንደሚገባ የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ድሪባ ኢትቻ ገለጹ፤

ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት (የካቲት 5/2018 ዓ.ም)

የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ካውንስል የ2018 ዓ.ም ስራ አፈጻጸም ሪፖርትን በዛሬው ዕለት ገምግሞ አጽድቋል፡፡

የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ድሪባ ኢትቻ የ2018 ዓ.ም የ6 ወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማን ሲያስጀምሩ እንደተናገሩት የተፈራረምነውን የውል ስምምነት መሠረት በማድረግ ሁሉም ባለድርሻ አካል የያዘውን ዕቅድ በጥራት መከወን አለበት ሲሉ አሳስበዋል።

ከዚህ በተጨማሪም የተለያዩ ስራዎች ሲሰጡ ጥራቱን እና ጊዜውን በጠበቀ መልኩ ተሰርቶ ለሚመለከተው አካል መቅረብ ወይም መላክ ይኖርበታል ብለዋል።

በአሁኑ ሰዓት ዩኒቨርሲቲው በጥሩ የለውጥ መስመር ላይ መሆኑን የጠቀሱት ፕሬዝዳንቱ ለለውጥ የመጣን ሰዎች እንደመሆናችን መጠን ተደጋግፈን ጠንክረን በመስራት ዩኒቨርሲቲውን አረግጓዴ፣ ጽዱ እና ከሌሎች ግንባር ቀደም ዩኒቨርሲቲዎች ተርታ ልናሰልፈው ይገባናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ተከናውነው በሪፖርቱ ያልተካተቱ ተግባራት እንዲካተቱና ከዚህ የ6 ወራት የስራ አፈጻጸም ውጤት በመነሳት በቀሪ 6 ወራት የልተከናወኑ እና በእቅድ የያዝናቸውን ስራዎች በስኬት ለማጠናቀቅ መረባረብ እንደሚገባ ተጠቅሷል፡፡

ሪፖርቱን ያቀረቡት የስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ ቡድን መሪ አቶ ሩፋኤል በቀለ ሲሆኑ በቀረበው ሪፖርት ላይ ሰፊ ውይይት ከተደረገበት በኋላ በሙሉ ድምፅ ፀድቋል።

Recent News
Follow Us