News Detail
Jan 13, 2026
199 views
የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጅ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ለሴት ሰራተኞችና ተማሪዎች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፤
ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት (የካቲት 5/2018 ዓ.ም)
የዩኒቨርሲቲው ቴክኖሎጅ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ፆታን መሰረት ያደረገ ጥቃትን አስመልክቶ ለተቋሙ ሴት ሰራተኞችና ተማሪዎች ስልጠና እየሰጠ ነው።
ስልጠናውን ያስጀመሩት የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ፣ ምርምር፣ ቴክኖሎጅ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፓል ቦት ስልጠናው ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን ለመከላከል ትልቅ አቅም የሚፈጥር በመሆኑ በስልጠናው ላይ የተገኙ ሴት ሰራተኞችና ተማሪዎች እየተሰጠ ያለውን ስልጠና በሚገባ ተከታትለው በተግባር እንዲያውሉት አሳስበዋል።
ስልጠናውን በጋራ እየሰጡ የሚገኙት በዩኒቨርሲቲው ማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ፋካልቲ የሳይኮሎጅ ትምህርት ክፍል መምህር ጂፕ ሬክና የስርዓተ ፆታ ትምህርት ክፍል መምህር ሞገስ መኮንን ሲሆኑ ከዛሬ የካቲት 5-6/2018 ዓ.ም ለተከታታይ ሁለት ቀናት የሚሰጥ ይሆናል።