News Detail
Feb 08, 2026
150 views
እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን!
ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ በ3 ጨዋታዎች 3 የብር ሜዳሊያዎችን አሸነፈ። (February 8/2026)
የቅርጫት ኳስ አሰልጣኝ በሆኑት መ/ር ሙላተ በያን የተመራው የጋምቤላ ቅርጫት ኳስ ቡድን የዛሬውን ጨምሮ ሁለት የብር ሜዳሊያ የሰበሰበ ሲሆን ዛሬ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር ባካሄደው የ 5 ለ 5 የወንዶች የቅርጫት ኳስ ጨዋታ ዩኒቨርሲቲያችን ከፍተኛ ፉክክር ያደረገ ቢሆንም 45 ለ 54 በሆነ ውጤት የብር ሜዳሊያ አሽናፊ ሆኗል።
ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ በ10ኛው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ስፖርት ፊስቲቫል ላይ በተለያዩ ውድድሮች ላይ በመሳተፍና የተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎችን በማከናወን ከፍተኛ እንቅስቃሴ ሲያደርግ ነበር።
ዩኒቨርሲቲው በቀጣይ ዓመት በቂ የሆነ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ በበርካታ የስፖርት ዓይነቶችና ውጤታማ የሚያደርጉትን በመለየት ከዘንድሮው ዓመት በበለጠ ብዙ ዋንጫዎችን እና የወርቅ ሜዳሊያዎችን የሚሰበስብበት ዓመት እንደሚሆን አቅም የታየበት የውድድር ጊዜ ነበር።
በመጨረሻም የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ቡድንን በመደገፍ ከጎናችን ለነበራችሁ 10ኛው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ስፖርት ፊስቲቫል ተሳታፊዎችና የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ፌስቡክ ገጽ ተከታዮች ምስጋናችን ከልብ ነው።