News Detail

ክስተቶች
Feb 07, 2026 152 views

የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የባህል ቡድን አባላት የተለያዩ አዝናኝ ፕሮግራሞችን ለተማሪዎች አቀረቡ።

ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት(ጥር 30/2018 ዓ.ም).

የዩኒቨርሲቲው የባህል ቡድን አባላት የተለያዩ አዝናኝና አስተማሪ የሆኑ ፕሮግራሞችን ለተማሪዎች አቅርበዋል።

የባህል ቡድን አባላቱ በዩኒቨርሲቲው የስራ እድል ፈጠራና ልማት ማዕከል ዳይሬክቶሬት አስተባባሪነት አዝናኝና አስተማሪ የሆኑ ባህላዊና ዘመናዊ ሙዚቃዎችን እና ዉዝዋዜዎችን ለዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች አቅርበዋል።

የዩኒቨርሲቲው ስራ እድል ፈጠራና ልማት ማዕከል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር መምህር ካልአዩ እቋር ፕሮግራሙ ተማሪዎች የማጠቃለያ ፈተና ተፈትነው ባጠናቀቁበት ወቅት ለ3ኛ ጊዜ የቀረበ መሆኑን ገልፀው አዝናኝና አስተማሪ የሆኑ ባህሎችን የሚለዋወጡበት፣ የበለጠ እርስ በርስ የሚቀራረቡበት፣መተሳሰብንና ወንድማማችነትን የሚያዳብሩበት መሆኑን ገልፀው ወደፊትም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

Recent News
Follow Us