News Detail

ክስተቶች
Feb 06, 2026 166 views

የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ልዑካን ቡድን በጅማ ሜቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር የሚገኙ አረጋዊያንን ጎበኘ፤ ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት (ጥር 29/2018 ዓ.ም)

ሜቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር ከ8500 በላይ የሚሆኑ አቀመ ደካማ አረጋውያንን አስጠግቶ ከእርዳታ ሰጪ ድርጅቶችና ግለሰቦች በሚገኝ ድጋፍ የሚተዳደር ሲሆን በአሁኑ ሰዓት የተለያዩ ድጋፎች እንደሚያስፈልጋቸውም በጉብኝቱ ወቅት ያገኘናቸው በጎ ፈቃደኞች አብራርተዋል።

የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ስፖርት ልኡክ ቡድን መሪና አና የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ዲን መምህር ምትኩ ዱባለ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት እነዚህን የሀገር ባለውለታዎች መጎብኘት ብሎም መደገፍ የሚያስደስትና በፈጣሪም የሚያስመሰግን ነው ብለዋል።

ሁሉም የሜቄዶንያን የዩቱዩብ ቻናል ሰብስክራይብ በማድረግ እገዛ እንዲያደርግላቸውም ጥሪ አስተላልፈዋል።

Recent News
Follow Us