News Detail
Feb 06, 2026
155 views
የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች የThematic Research ንድፈ-ሀሳብ ግምገማ እያካሄዱ ነው። ህዝብና ዓለም ዓቀፍ ግንኙነት (ጥር 28/2017 ዓ.ም)
የዩኒቨርሲቲው ተመራማሪዎች ተጨባጭ የሆኑ የምርምር ንድፈ-ሀሳብ ግምገማ እያካሄዱ ይገኛሉ።
የምርምር ግምገማውን ያስጀመሩት የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ፣ ምርምር፣ ቴክኖሎጅ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ተወካይና ልዩ ረዳት ዶ/ር ጀምበሩ ዓለሙ የዩኒበርሲቲው መምህራን ከመማር ማስተማር በተጨማሪ የምርምር ስራዎችን እየሰሩ መሆኑን ገልፀው ተመራማሪዎች የችግሮችን ምንጭ አጥንተው የማህበረሰቡን ችግር ሊፈቱ የሚችሉ ተጨባጭ የምርምር ስራዎችን መስራት እንዳለባቸው መልክታቸውን አስተላልፈዋል።
የምርምር ግምገማው በዩኒቨርሲቲው ምርምር፣ ህትመትና ስነ-ምግባር ዳይሬክቶሬት አስተባባሪነት እየተካሄደ የሚገኝ ሲሆን የምርምር፣ ህትመትና ስነ-ምግባር ዳይሬክተር ዶ/ር እንዳለ ተስፋዬ ከቀረቡት 19 የምርምር ንድፈ-ሀሳቦች መካከል መስፈርቱን ያሟሉ 11 ምርምሮች ለግምገማ የቀረቡ መሆኑን ገልጸዋል።