News Detail

ክስተቶች
Feb 12, 2025 263 views

ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ በጋምቤላ ክልል የሚገኙ የአኙዋ፣ የኑዌርና እና የማጃንግ ቋንቋዎች በበይነ-መረብ ላይ ዶክሜንት ለማድረግና ለመማር እንዲቻል ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር እየሰራ ይገኛል፡፡

ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ በጋምቤላ ክልል የሚገኙ የአኙዋ፣ የኑዌርና እና የማጃንግ ቋንቋዎች በበይነ-መረብ ላይ ዶክሜንት ለማድረግና ለመማር እንዲቻል ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር እየሰራ ይገኛል፡፡
ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት (ህዳር 23/2018 ዓ.ም)
ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ በጋምቤላ ክልል የሚገኙ የአኙዋ፣ የኑዌርና እና የማጃንግ ቋንቋዎች በበይነ-መረብ ላይ ዶክሜንት ለማድረግና ለመማር እንዲቻል ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር “Ethio Language Box.” በሚል ፕሮጀክት እየተሰራ የሚገኝ ሲሆን ቋንቋዎቹ የሞባይል መተግበሪያ ተዘጋጅቶላቸው በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ተተርጉመው የሚቀርቡ ይሆናል፡፡
ቋንቋዎቹን መማር የሚፈልግ ማንኛውም ሰው በበይነ-መረብና በሞባይል መተግበሪያ በጽሁፍና በድምጽ ማግኘት የሚችል ሲሆን ዩኒቨርሲቲው የአካባቢውን ቋንቋ ከማሳደግና ከማስተዋወቅ አንጻር እያከናወነ ያለው ተግባር ይበል የሚያሰኝ ነው፡፡
ስራው በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ በማህበረሰብና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት አስተባባሪነት እየተከናወነ የሚገኝ ሲሆን በማስጀመሪያ ፕሮግራሙ ላይ የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ድሪባ ኢትቻ ተገኝተው ቡድኑን አበረታተዋል፡፡
Recent News
Follow Us