News Detail

ማስታወቂያ
Dec 03, 2025 211 views

የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት የፕሬዝዳንትና ም/ፕሬዝዳንት ምርጫ ተካሄደ፤

የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት የፕሬዝዳንትና ም/ፕሬዝዳንት ምርጫ አካሄዱ፤ ከሁሉም ኮሌጆች፣ ፋካሊቲና ትምህርት ቤት ከየትምህርት ክፍሎች ሂደቱን ጠብቆ የተመረጡት የተማሪዎች ህብረት ስራ አስፈጻሚዎች በዛሬው እለት ባደረጉት ስብሰባ የተማሪዎች ህብረት ፕሬዝዳንት፣ ምክትል ፕሬዝዳንትና ጸሓፊ መርጠዋል፡፡ 

ምርጫው ፍትኃዊና ዲሞክራሲያዊ እንዲሆን የተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክቶሬትና የአካዳሚክ ፕሮግራሞች ዳይሬክቶሬት አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ምርጫው እንዲፈጸም አድርገዋል፡፡

በዚሁ መሰረት ተማሪ ጋች ኮንግ ከአግሪ ቢዝነስ ፕሬዝዳንት፣ ተማሪ ናኦል ሞሲሳ  ከህግ ትምህርት ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት እንዲሁም ተማሪ ኒያል ዳክ ከማዕድን ኢንጂነሪንግ ጸሃፊ በመሆን ተመርጠዋል፡፡ 

የአካዳሚክ ፕሮግራሞች ዳይሬክተር ዶ/ር ሽብሩ ዘሪሁን ምርጫው የተማሪዎች ህብረትን ደንብና መመሪያ ተከትሎ የተከናወነ መሆኑን ገልጸው ለተመራጭ ተማሪዎች የስራ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡ ዛሬ ጠመረጣችሁ ፕሬዝዳንት፣ ም/ፕሬዝዳንትና ጸሃፊ ከፍተኛ ኃላፊነት ያለባችሁ መሆኑን ተገንዝባችሁ ከዩኒቨርሲቲው መምህራን እና ሠራተኞች እንዲሁም ከአመራሮች ጋር በመግባባትና ጠንክሮ በመስራት ዩኒቨርሲቲያችንን በጋራ ማሳደግ ይኖርብናል ብለዋል፡፡ 
ዶ/ር ሽብሩ ጨምረው እንደገለጹት የዩኒቨርሲቲውን አጠቃላይ ሁኔታ በመገንዘብ በምትሄዱበት ሁሉ ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲን ማስተዋወቅና ከዩኒቨርሲቲያችሁ ጎን መቆም ይኖርባችኋል ብለዋል፡፡

የተማሪዎች አገልግሎት ዲን መ/ር አዳነ ዱሬሳ በበኩላቸው ምርጫ የሚካሄደው ትክክለኛ መስራትና የተማሪዎችን መብት ማስከበር የሚችል፣ ከራሱ ይልቅ የተማሪዎችን ጥቅም በማስቀደም ከቅሬታ ይልቅ መፍትሄ ይዞ መምጣት የሚችሉ አቅም ያላቸው ተማሪዎችን ወደፊት ማምጣት ያስፈልጋል ካሉ በኋላ ምርጫውን ለሸነፉ ተማሪዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ 

Recent News
Follow Us