News Detail

ማስታወቂያ
Dec 13, 2025 505 views

በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲና በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የተጀመረው የጋምቤላ ክልል ቋንቋዎችን ድጂታይዝድ የማድረግ ስራ በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ እንደሆነ  ተገለጸ፤

በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲና በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የተጀመረው የጋምቤላ ክልል ቋንቋዎችን ድጂታይዝ የማድረግ ስራ በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ እንደሆነ  ዛሬ በተደረገው የመውጫ ስብሰባ ላይ ተገልጸ፤ በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የቋንቋ ጥናትና የትርጉም ልማት ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ረዳት ፕሮፌሰር ከፍያለው አብዲሳ እንደገለጹት ቋንቋዎቹ ተተርጉመው ድጂታይዝ ከመደረጋቸው በላይ ታሪክና ማንነት ሊያስተዋውቁ ስለሚችሉ ጠቀሜታው የጎላ ነው ብለዋል፡፡ 

በመሆኑም ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የአካባቢውን ማህበረሰብ ቋንቋዎች ለማሳደግ ያሳየውን ቁርጠኝነት በማድነቅ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ፣ ምርምር፣ ማህበረሰብ አገልግሎትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዝዳንት ተወካይና ልዩ ረዳት ዶ/ር ጀምበሩ አለሙ በበኩላቸው በዚህ ስራ ላ የተሳተፉትን መምህራን እና የቋንቋ ባለሞያዎች አመስግነው ከዚህ በኋላ በክልሉ ላይ ምርምር ለመስራት የሚፈልጉ መንገዱ ተመቻችቶላቸዋል ብለዋል፡፡ በቀጣይ በውይትና በተለያዩ መንገዶች ወደ ህብረተሰቡና ተጠቃሚዎች የምናወርድበትን መድረኮች ማመቻቸት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡ 

የማህበረሰብና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክተር መ/ር ገብረእግዚአብሄር አሳየኸኝ በበኩላቸው የስራ ክፍላችን ከዚህ ቀደም ሲሰጠው ከነበረው አገልግሎት በጣም ትልቁና ለክልሉ ቋንቋ ባለቤቶች ትልቅ ፋይዳ ያለው ተግባር እንደተከናወነ ገልጸው የአካባቢውን የቱሪዝም ሀብት ለመጠቀም የቋንቋዎች መተርጎምና ድጂታይዝ መደረግ ቀጥተኛ ግንኜነት እንዳለው ገልጸው በተሰራው ስራ ደስተኛ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

የEthiopian Language Box ፕሮጀክት ሀሳብ አመኝጪ ዶ/ር ሰካሀር 3ቱን የክልሉን ቋንቋዎች ድጂታይዝ ላድረግ በነበረው ሂደት ውስጥ የነበሩትን መልካም ተሞክሮዎች ለታዳሚዎች አቅርበዋል፡፡
 
ይህ ስራ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ያሉት ታዳሚዎቹ ከዚህ በኋላ የናይሎቲክ ቋንቋዎችን ለማጥናት ፍላጎት ያላቸው ተመራማሪዎች መልካም አጋጣሚ እንደተፈጠረላቸው ገልጸው በቀጣይ መዝገበ ቃላትና መጽሃፍት መታተምና መሰራጨት እንዳለባቸው ጠቁመዋል፡፡ 

Recent News
Follow Us