News Detail
Apr 26, 2026
482 views
ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ STEM CENTER ለአዳሪ ትምህርት ቤትና ለ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን ሲሰጥ የነበረውን ስልጠና አጠናቀቀ ።
ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ STEM CENTER ለአዳሪ ትምህርት ቤትና ለ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን ሲሰጥ የነበረውን ስልጠና አጠናቀቀ ።
ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት (ሚያዝያ 18/2018 ዓ.ም)
የዩኒቨርሲቲው STEM CENTER ለፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት፣ ለጋምቤላ ክልል ሴቶች አዳሪ ትምህርት ቤትና በጋምቤላ ከተማ ለሚገኙ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን ሲሰጥ የነበረውን የኤሌክትሮኒክስና ቪርቹዋል ኮምፕዩተር ስልጠና አጠናቋል።
የኤሌክትሮኒክስና የቪርቹዋል ኮምፕዩተር የተግባር ስልጠናውን ከሚያዝያ 17-18/2018 ዓ.ም ድረስ በተከታታይ ለሁለት ቀናት በጋራ የሰጡት በዩኒቨርሲቲው ኢንጅነሪንግና ቴክኖሎጅ ኮሌጅ የኤሌክትሪካልና ኮምፕዩተር ኢንጅነሪንግ ትምህርት ክፍል መምህራን የሆኑት ዶል ጎኝ እና ጋትላት ቦዝ ናቸው።
በተግባር ስልጠናው ላይ የተገኙ የአዳሪ ትምህርት ቤት እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን ስልጠናው በብዙ ነገሮች ላይ ዕውቀት እንዲያገኙ የሚያደርግ መሆኑን ገልጸው በተለይም መምህራን እረፍት ላይ በሚሆኑበት በክረምት ወቅት ለሁሉም እንዲዳረስ ቢደረግ የሚል አስተያዬት ሰጥተዋል።
በመጨረሻም በዩኒቨርሲቲው ቴክኖሎጅ ሽግግርና ማህበረሰብ አግልግሎት ዳይሬክቶሬት የ STEM CENTER አስተባባሪ የሆኑት መምህር መንግስቱ ዘላለም በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ እንደገለጹት ለ4ኛ ዙር የተሰጠ እንደሆነና ወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀው ተማሪዎች ከታች ክፍል ጀምሮ ስለቴክኖሎጅ እንዲያውቁ ማድረግና የተሻለ ዕውቀት ያለው ተማሪ ማፍራት እንደሚገባ አሳስበዋል።
ይህንንም ለማድረግ መምህራን በዕውቀትና በስነ- ልቡና ተማሪዎችን ለማገዝ መዘጋጀት እንዳለባቸው ገልጸዋል።