News Detail
የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ከምክትል ፕሬዝዳንቶችና ሌሎች መካከለኛ አመራሮች ጋር የአፈፃፀም ውል ስምምነት ፊርማ ተፈራረሙ።
ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት (ጥቅምት 13/2018 ዓ,ም)
የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ከምክትል ፕሬዝዳንቶችና መካከለኛ አመራሮች ጋር 2ኛውን ዙር የአፈፃፀም ውል የፊርማ ስነ-ስርዓት አካሂደል።
የ2ኛው ዙር የአፈፃፀም ውል ስምምነት ዋና ዓላማ በምርምር፣ በመማር ማስተማርና በማህሀረሰብ አገልግሎት ዘርፍ የሚሰሩ ዋና ዋና ስራዎች ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑን የአፈፃፀም ውሉን የመወያ ሰነድ ያቀረቡት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ድሪባ ኢትቻ ለካውንስል አባላት አስረድተዋል።
ፕሬዝዳንቱ የተለያዩ የትምህርት ፖሊሲዎች እና ኢኒሼቲቮች እየመጡ መሆናቸውን ገልፀው ከአነዚህም መካከል የአፈጻጸም ውል ስምምነቱ አንዱ መሆኑን ተናግረዋል::
የፊርማው ዓላማ ተጠያቂነትን ለማስፈን፣ የከፍተኛ ትምህርት መረጃ አያያዝ ስርዓት/HEMIS በትክክል ለመፈጸም፣ የዩኒቨርሲቲ ልየታን /Differentiation እና የትኩረት መስክን መሰረት አድርጎ መስራት እንዲሁም ከዓለም አቀፋዊነትና አጋርነት ጋር ስለሚያያዝ Acrreditation ላይ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት እንዳለበት አቅጣጫ የተሰጠ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
የአፈጻጸም ውል ስምምነቱ ለ2ኛ ጊዜ የሚተገበር በመሆኑ በ2017 ዓ.ም የነበሩ ክፍተቶችን ለመለየትና የማስተካከያ እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል ስለሆነ በ2018 በርትተን በመስራት የተሸለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ እጅ ለእጅ ተያይዘን እንስራ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ድሪባ ኢትቻ ከምክትል ፕሬዝዳንቶች ጋር ከተፈራረሙ በኋላ በስራቸው ከሚገኙ ስራ አስፈጻሚዎች ጋር ተፈራርመዋል፡፡
የዩኒቨርሲው አካዳሚክ፣ምርምር፣ቴክኖሎጅ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፓል ቦት ውሉን ተፈፃሚ ማድረግ እንደሚገባ ገልፀው ይህንን ለማድረግም በየጊዜው የግንዛቤ ማስጨበጫ ይሰጣል ብለዋል።
አካዳሚክ፣ ምርምር፣ ቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፓል ቦት በስራቸው ከሚገኙ ድኖችና ዳይሬክተሮች ጋር ተፈራርመዋል፡፡
የአስተዳደርና ቢዝነስ ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዮናስ ከፍያለው በበኩላቸው ተጨባጭና ትክክለኛ መረጃ ለባለ ድርሻ አካላት መስጠት እንደሚገባ ገልፀው ውሉ ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ ለተግባራዊነቱ ሁሉም እንዲረባረብ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የአስተዳደርና ቢዝነስ ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዮናስ ከፍያለው በበኩላቸው እንዲሁ በስራቸው ከሚገኙ ስራ አስፈጻሚዎች ጋር ተፈራርመዋል፡፡
ወደፊት ዲኖች ከትምህርት ክፍል ኃላፊዎች ጋር፣ ስራ አስፈጻሚዎች ከቡድን መሪዎች ጋር እንዲሁም ዳይክተሮች ከአስተባባሪዎች ጋር የሚፈራረሙ ይሆናል፡፡