News Detail
የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች መሰረታዊ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች ገለፃ (Orientation) ሰጠ፤
ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት (ጥቅምት 23/2018 ዓ.ም )
የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች መሰረታዊ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲውን መተዳደሪያ ደንብ አስመልክቶ ገለፃ (Orientation) ሰጥቷል።
ተማሪዎችን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት መልካም ምኞታቸውን የገለጹት የአካዳሚክ ፕሮግራምች ዳይሬክተር ዶ/ር ሽብሩ ዘሪሁን በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ስትማሩ ከነበረው የትምህርት ከባቢ ወደ ዩኒቨርሲቲ ስትመጡ ከቤተሰብ ክትትል ውጭ በመሆናችሁ እራሳችሁን መምራትና ከሌሎች ተማሪዎች ጋር በጋራ መኖር የምትጀምሩበት ወቅት በመሆኑ ከአላስፈላጊ ነገሮች እራሳችሁን ቆጥባችሁ በትምህርታችሁ ላይ ብቻ ትኩረት አድርጋችሁ ውጤታማ መሆን ይጠበቅባችኋል ብለዋል፡፡
ሰዓት በማክበርና ማህበራዊ ሚዲያን ለአዎንታዊ ፋይዳ ብቻ በመጠቀምና በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ውስጥ የተፈቀዱና ያልተፈቀዱ ነገሮችን እንድታውቁና በዩኒቨርሲቲ ቆይታችሁ በመልካም ስነ-ምግባር ታንጸችሁ እንድትወጡ የሚረዳችሁ ስለሆነ ገለጻውን በጥሞና እንድትከታተሉ ሲሉ ዶ/ር ሽብሩ አሳስበዋል፡፡
ስልጠናውን የሰጡት የሳይኮሎጂስቶች ቡድን መሪና የተማሪዎች ስብዕና ግንባታ ምክትል ዲን ተወካይ አቶ መሰንበት ጥሩነህ ሲሆኑ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲው ያስቀመጠውን የተማሪዎች መተዳደሪያ ደንብ አክብረው መንቀሳቀስ እንዳለባቸው አብራርተው መተዳደሪያ ደንቦችን ተላልፈው ሲገኙ ማስጠንቀቂያ ከመስጠት ጀምሮ እስከ መሰናበት የሚያደርስ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው ዘርዘር አድረገው አብራርተዋል።
በመጨረሻም ተማሪዎች ግልጽ ያልሆኑ ጥያቄዎችን እና አስቴየቶችን አቅርበው የአካዳሚክ ፕሮግራሞች ዳይሬክተር ዶ/ር ሽብሩ ዘሪሁን እና አቶ መሰንበት ጥሩነህ ማብራሪያ ሰጥተውበታል፡፡