News Detail
የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የስራ እድል ፈጠራና ልማት ማዕከል ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች የሕይወት ክህሎት ስልጠና ሰጠ፤
ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት (ጥቅምት 22/2018 ዓ.ም)
የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የስራ እድል ፈጠራና ልማት ማዕከል ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች የሕይወት ክህሎት ስልጠና ሰጥቷል፤
ስልጠናው ለሁል አዲስ ገቢ ተማሪዎች ተሰጠ ሲሆን የአካዳሚክ፣ ምርምር፣ ማህበረሰብ አገልግሎትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ልዩ እረዳት ደ/ር ጀምበሩ ዓለሙ ስልጠናውን አስጀምረዋል‹፡፡ ዶ/ር ጀምበሩ እንደገለጹት የህይወት ክህሎት ስልጠና መውሰዳችሁ በራስ መተማመናችሁ እንዲጨምርና ከእራሳችሁ ጋር እና ከሌሎች ጓደኞቻችሁ ጋር የሚኖራችሁን ተግባቦት እንዲዳብር ያደርጋል ብለዋል፡፡
የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የስራ እድል ፈጠራና ልማት ማዕከል ዳይሬክተር መምህር ካላዩ እቋር በበኩላቸው ስልጠናው የተዘጋጀው አዲስ ገቢ ተማሪዎች ከቤተሰብ ተለዩተው የተለያዩ ባህል፣ ቋንቋ እና እምነት ካላቸው ተማሪዎች ጋር ስለሚገናኙ እነዚህ ልዩነቶች ውበት መሆናቸውን ተረድተው እርስ በእርስ ተከባብረው ተፋቅረው እንዲኖሩ የሚረዳቸው ስልጠና እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
የወሰዳችሁት ስልጠና በዩኒቨርሲቲ ቆይታችሁ የሚጠቅሟችሁ እንደ ሰዓት አጠቃቀም፣ የወደፊት ግብ ማስቀመጥና እራሳችሁን እንዴት መምራት እንዳለባችሁ ግንዛቤ የሚፈጥርላችሁ ስለሆነ እዚህ በጽንሰ ሀሳብ ደረጃ የወሰዳችሁትን ስልጠና በእለት ተዕለት ህይወታችሁ ውስጥ በተግባር ላይ በማዋል እንድትጠቀሙበት አደራ ለማለት እወዳለሁ ብለዋል፡፡