News Detail
Jan 12, 2025
191 views
"ተግዳሮቶችን በመቋቋም የኤች አይ ቪ ኤድስ ምላሽን ዘላቂነት እናረጋግጣለን" በሚል መሪ ቃል የዓለም ኤች አይ ቪ ኤድስ ቀን በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ተከበረ፤
"ተግዳሮቶችን በመቋቋም የኤች አይ ቪ ኤድስ ምላሽን ዘላቂነት እናረጋግጣለን" በሚል መሪ ቃል የዓለም ኤች አይ ቪ ኤድስ ቀን በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ተከበረ፤
ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ( ህዳር 22/2018 ዓ.ም)
"ተግዳሮቶችን በመቋቋም የኤች አይ ቪ ኤድስ ምላሽን ዘላቂነት እናረጋግጣለን" በሚል መሪ ቃል የዓለም ኤች አይ ቪ ኤድስ ቀን በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው እለት ተከብሮ ውሏል፤
የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ፣ምርምር፣ ቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ተወካይና ልዩ ረዳት ዶ/ር ጀምበሩ ዓለሙ የእለቱን ውይይት በንግግር የከፈቱ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የትምህርትና ቅስቀሳ ስራው እየተቀዛቀዘ በመምጣቱ የኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭት እየተስፋፋ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
ኤች አይ ቪ ኤድስ ወጣቱን እና አምራች ዜጋን እየጎዳ ያለ በሽታ በመሆኑ የዩኒቨርሲቲያችን ተማሪዎች ለዚህ ወረርሽኝ ተጋላጭ በመሆናቸው የተለያዩ ክበባትን በማቋቋም እንዲሳተፉ በማድረግ ግንዛቤ እንዲያገኙና እራሳቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን ከበሽታው እንዲከላከሉ ማድረግ ይገባል ብለዋል፡፡
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ምህረት ከበደ የውይይት መነሻ ጽሁፍ ያቀረቡ ሲሆን በሽታውን ለመከላከል የሚደረጉ ጥረቶች መቀዛቀዛቸውን እና መንግስታዊ ያልሆኑ የረድኤት ድርጅቶች የሚያደርጉት ድጋፍም በከፍተኛ ሁኔታ እቀነሰ መምጣቱን ከቀረበው ጽሁፍ አመላክተዋል፡፡
የቀረበውን ጽሁፍ መነሻ አድርጎ በየዩኒቨርሲቲው ውስጥ በሽታውን ለመከላከል ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራ አስተያየቶች የተሰጡ ሲሆን ሠራተኞችና ተማሪዎች የደም ምርመራ በማድረግ እራሳቸውን እንዲያውቁ ጥረት መደረግ አለበት ተብሏል፡፡
በመጨረሻም በበሽታው ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች የአነድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት ተደርጎላቸዋል።