News Detail

ክስተቶች
Dec 03, 2018 182 views

ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲና የክርስቲያን በጎ አድራጎት እና ልማት ማህበራት ህብረት (CCRDA) የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።

ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲና የክርስቲያን በጎ አድራጎት እና ልማት ማህበራት ህብረት (CCRDA)
የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።
ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት (ህዳር 17/2018 ዓ.ም)
ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲና የክርስቲያን በጎ አድራጎት እና ልማት ማህበራት ህብረት (CCRDA) ችግር ፈች በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል።
የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ድሪባ ኢትቻ በተቋሙ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን አስመልክቶ ገለፃ ያደረጉ ሲሆን በተለይም በክልሉ ባለው እምቅ የተፈጥሮ ሀብት ማህበረሰቡ ይበልጥ ተጠቃሚ እንዲሆን የምርምር ስራዎችና ዕውቀት መር የሆነ የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልፀዋል።
ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲና የክርስቲያን በጎ አድራጎት እና ልማት ማህበራት ህብረት (CCRDA) በምርምርና ፣ ፈጣን ምላሽ ሰጪ ምርምሮች ፣በጋራ ትምህርት ፕሮግራሞች፣ የሰላም ፖሊሲዎችን በማሻሻልና ፖሊሲዎችን በማስተዋወቅ፣ በማህበረሰብ ውይይቶች፣ የማህበረሰብ መሪዎችን፣ ተማሪዎችንና ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎች አቅም ግንባታ፣ በሰላም ግንባታና እርቀ ሰላም፣ በእውቀት ልውውጥ፣ ፎረሞችን እና ኮንፈረንሶችን በጋራ ለማዘጋጀት ተስማምተዋል።
የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ድሪባ ኢትቻ እና የክርስቲያን በጎ አድራጎት እና ልማት ማህበራት ህብረት (CCRDA) የፕሮጀክት አስተባባሪ ወ/ሮ ራሄል ህለተወርቅ ተቋሞቻቸውን ወክለው በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነቱን ተፈራርመዋል።
በፊርማ ስነ-ሰርዓቱ ላይ የአስተዳደርና ቢዝነስ ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዮናስ ከፍያለውን ጨምሮ የዩኒቨርሲቲው ባለድርሻ አካላትና የክርስቲያን በጎ አድራጎት እና ልማት ማህበራት ህብረት (CCRDA) አመራሮች ተገኝተዋል።
Recent News
Follow Us