News Detail
Oct 10, 2025
264 views
ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የ2018 የትምህርት ዘመን የቁልፍ ተግባራት ስምምነት ፊርማ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በዛሬው ዕለት ተፈራርሟል።
ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የ2018 የትምህርት ዘመን የቁልፍ ተግባራት ስምምነት ፊርማ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በዛሬው ዕለት ተፈራርሟል።
ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት (መስከረም 30/2018 ዓ.ም)
የትምህርት ሚኒስቴር ዲኤታ አቶ ኮራ ጡሸኔ፣ የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ድሪባ ኢትቻ እና የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ስራ አመራር ቦርድ ም/ሰብሳቢ ፕሮፌሰር አጀቡ ኑርፈታ ተፈራርመዋል።
በHEMIS አተገባበር ላይ የመምህራን፣ የሰራተኞች፣ የተማሪዎች እና አጠቃላይ መረጃዎች በአግባቡ ተካተው መያዝ እንዳለባቸው እና ዩኒቨርሲቲዎች ልየታቸውን /Differenciation/ መሠረት በማድረግ መስራት ይኖርባቸዋል ተብሏል።
አለም አቀፍዊነትና አጋርነትን ለማጠናከር ዩኒቨርሲቲዎች በሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ደረጃ አክሬዲትድ እንዲሆኑ ትኩረት ሰጥተው መስራት እንዳለባቸውም ተገልጿል
የዘንድሮው ዓመት ስምምነት ከወትሮው በተለየ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራበት እንደሚገባም ተገልጿል፡፡
በቀጣይም የትምህርትን ጥራት፣ ተደራሽነትና አካታችነትን በማሳደግ፤ እንዲሁም በትምህርት ዘርፉ ላይ ዲጂታላይዜሽንን በማስፋፋት ረገድ በርካታ ተግባራት እንደሚከናወኑ ተመላክቷል።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት የተግባራት ስምምነቱን ከዩኒቨርሲቲው ም/ፕሬዝዳንቶች፣ ጽ/ቤት ኃላፊና ስራ አስፈጻሚዎች ጋር ወደፊት የሚፈራረሙ ይሆናል።