News Detail
Nov 15, 2025
147 views
የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት ለመምህራን ስልጠና ሰጠ፤
የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት ለመምህራን ስልጠና ሰጠ፤
ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት (ህዳር 6/2018 ዓ.ም)
የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት ለመምህራን ስልጠና ሰጥቷል፡፡ ስልጠናው ትኩረት ያደረገው በስታትስቲካል ሶፍትዌር ላይ ሲሆን ይህም የሚሰሩ ምርምሮች በትክክለኛ መረጃ ላይ የተሞረከዙና ውጤታማ እንዲሆኑ ያስችላል ሲሉ የአካዳሚክ፣ምርምር፣ ቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፓል ቦት ገልጸዋል፡፡
ጥራት ያላቸው ጆርናሎች በበዩነ-መረብ ባሳተምን ቁጥር አብዘሀኞቹ በማጣቀሻነት ስለሚጠቀሟቸው ዩኒቨርሲቲያችን እንዲታወቅ ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖራቸዋል፤ እንዲሁም ደረጃቸውን የጠበቁ ምርምሮች በሰራችሁ ቁጥር ለእናንተም ሆነ ለዩኒቨርሲቲው ያለው ፋይዳ የጎላ ስለሆነ ተያይዞ ማደግ ይቻላል ካሉ በኋላ መምህራን የወሰዱትን ስልጠና በተግባር ላይ እንዲያውሉት ዶ/ር ፓል አሳስበዋል፡፡
የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ጥናትና ምርምር ዳይሬክተር ዶ/ር እንዳለ ተስፋዬ በበኩላቸው ስልጠናው የሚሰሩ ምርምሮችን ደረጃ በማሳደግ ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጸው ዳይሬክቶሬቱ ባለፈው ዓመት የተለያዩ ስልጠናዎችን ለመምህራን መስጠቱን ጠቅሰዋል፡፡
በዘንድሮው ዓመትም የመምህራንን የምርምር አቅም የሚያጎለብቱ የተለያዩ ስልጠናዎች በእቅድ መያዛቸውን ጠቅሰው ስልጠናውን የወሰዱ መምህራን ለሌሎችም እንዲያጋሩ አሳስበዋል፡፡
ስልጠናውን የሰጡት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር ታጠቅ ጌታቸው ሲሆኑ በስልጠናው ላይ ቁጥራቸው ከሃምሳ የሚበልጡ መምህራን ተሳትፈዋል፡፡