News Detail

ክስተቶች
Jan 22, 2026 178 views

ለጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ልዑካን ቡድን የአሸኛኘት ስነ-ስርዓት ተደረገላቸው፤

ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት (ጥር 14/2018 ዓ.ም)

የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ልዑካን ቡድን አሸኛኘት ተደረገላቸው፡፡ 10ኛው የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ስፖርት ፌስቲቫል በጅማ ዩኒቨርሲቲ አስተናጋጅነት ከጥር 17/2018 ዓ.ም ጀምሮ የሚካሄድ ሲሆን በዚህ የስፖርት ፌስቲቫል ላይ ለመሳተፍ የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ስፖርት ቡድን አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎችን ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

በዛሬው ዕለት በተካሄደው የሽኝት ፕሮግራም ላይ ንግግር ያደረጉት የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ድሪባ ኢትቻ ስፖርተኞች በራስ መተማመንን እና ስነ-ምግባርን በመላበስ ከስፖርታዊ ውድድሩ ባሻገር ክልሉን እና ዩኒቨርሲቲውን በማስተዋወቅ የአምባሳደርነት ሚና ሊጫወቱ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ ጋምቤላ ክልል በእምቅ የተፈጥሮ ሀብቷ የታወቀች እንዲሁም የተለያዩ የኢትዮጽያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በጋራ የሚኖሩባት ክልል መሆኗን በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ተማሪዎች ማስተዋወቅ እንዳለባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመጨረሻም የስፖርትን ዓላማ በመረዳት ፍጹም ጨዋነት፣ ወዳጅነትና አብሮነት በተሞላበት መልኩ ጫወታቸውን እንዲያካሂዱ ገልጸው ለቡድኑ የመልካም ምኞት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ በ6 የስፖርት ዓይነቶች የሚወዳደር ይሆናል፡፡

Recent News
Follow Us