News Detail
የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት የተለያዩ መመሪያዎቾንና ፖሊሲዎችን አፀደቀ።
ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት (የካቲት 11/2018 ዓ.ም)
የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት የተለያዩ መመሪያዎቾንና ፖሊሲዎችን መርምሮ አፀድቋል።
ሴኔቱን የመሩት የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ድሪባ ኢትቻ በመክፈቻ ንግግራቸው ዩኒቨርሲቲውን ለማሳደግ ኃላፊነት የተሰጣቸው አካላት የተሰጣቸውን ኃላፊነት በሚገባ ለመወጣት ተጨማሪ ስራዎችን መስራት እንደሚገባቸው አሳስበው ባለድርሻ አካላት የዩኒቨርሲቲውን የትምህርት ካላንደር፣ የተለያዩ መመሪያዎችን እና ፖሊሲዎችን ለሴኔት አባላት እንዲያቀርቡ ጋብዘዋል።
በዚህም መሰረት የዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራር ጽ/ቤት ኃላፊ መምህር አየለ ያያ የዩኒቨርሲቲውን የአካዳሚክ ካላንደር ያቀረቡ ሲሆን እድሜያቸው ለመምረጥ የደረሱ ተማሪዎች ምርጫው ከመድረሱ 15 ቀን በፊት ትምህርታቸውን አጠናቀው ወደ ቤተሰቦቻቸው በመሄድ የመምረጥ መብታቸውን ተጠቅመው ሀገራዊ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ መንግስት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የሁለተኛ ወሰነ ትምህርት የሚጠናቀቅበትን እና የተማሪዎች ምርቃት ቀን ከሀገራዊ ምርጫ ቀደም ብሎ እንዲከናወን ሴኔቱ ወስኗል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ የተለያዩ የጥናትና ምርምር መመሪያዎች በዶ/ር እንዳለ ተስፋዬ ቀርበዋል፤ ከእነዚህም መካከል Research thematic areas, Research & Publication Guide Line, Publication and Dessimination policy, Research Funding Policy and procedure ሲሆኑ ሴኔቱ አስተያየት ከሰጠባቸው በኋላ አጽድቋቸዋል፡፡
Guide Lines for Continuing Education Programs በመምህር ቸኮል አለሙ፣ የዩኒቨርሲቲው የትምህርትና ስልጠና ዕድል አሰጣጥ መመሪያ በዶ/ር ከተማ ጥላሁን፣ የተለያዩ 8 የትምህርት ጥራት ፖሊሲዎች በዶ/ር ቻንድራ እንዲሁም የሞጁል ዝግጅት ማሻሻያ መመሪያ በመምህር ኃይሉ ተረፈ ለሴኔት አባላት ቀርበዋል።
የሴኔት አባላትም በቀረቡት የተለያዩ መመሪያዎችና ፖሊሲዎች ላይ ሰፊ ውይይት ካደረገ በሗላ የቀረቡ መመሪያዎችን እና ፖሊሲዎችን በሙሉ ድምጽ አጽድቋቸዋል።
በመጨረሻም የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ድሪባ ኢትቻ ሰነዶችን ያቀረቡ አካትን አመስግነው ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ መመሪያዎች በሴኔቱ ተገምግመው የሚፀድቁ መሆኑን በመግለጽ ስራዎችን በተገቢው መንገድ መስራት የሚችሉ ባለድርሻ አካላት በመኖራቸው ዩኒቨርሲቲው ባለ ብሩህ ተስፋ መሆኑን ገልጸዋል፡፡