News Detail
Feb 19, 2026
164 views
የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ ለባለድርሻ አካላት ስልጠና ሰጠ።
ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት(የካቲት 12/2018 ዓ.ም)
የዩኒቨርሲቲው ስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ የከፍተኛ ትምህርት አስተዳደር መረጃ ስርትን አስመልክቶ ለባለድርሻ አካላት ስልጠና ሰጥቷል።
ስልጠናውን የሰጡት በዩኒቨርሲቲው ስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ ባለሙያ አቶ እንዳልካቸው አድማሱ ሲሆኑ ስልጠናው በዋናነት ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ከገቡ ጀምሮ ትምህርታቸውን አጠናቀው እስከ ሚመለሱ ድረስ ያለው ሙሉ የትምህርትና የግል መረጃ እንዲሁም የሰራተኞች ሙሉ መረጃ ጥራት ባለው መልኩ ተመዝግቦ እንዲያዝና ለሚመለከተው አካል እንዲተላለፍ ለማድረግ ያለመ ነው።
የተሰጠውን ስልጠና አስመልክቶ ሰልጣኞች ጥያቄዎችን የጠየቁ ሲሆን ጉዳዩ በሚመለከታቸው አካላት መልስ ተሰጧል።
በስልጠናው የተገኙት የአካዳሚክ፣ ምርምር፣ ቴክኖሎጅ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ልዩ ረዳት ዶ/ር ጀምበሩ ዓለሙ የተቋሙ ባለድርሻ አካላት በሚሰጣቸው ፎርማት መሠረት መረጃዎችን በጥራት በመመዝገብና ለስትራቴጂክ ጉዳዮች በማሰተላለፍ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ መልዕክት አስተላልፈዋል።