News Detail
Feb 28, 2025
180 views
ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ገቢ ተማሪዎችን ተቀበለ
ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት (ጥቅምት 18/2018 ዓ.ም)
ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ በ2018 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው የተመደቡ አዲስ ገቢ ተማሪዎችን ከትላንት ጥቅምት 17/2018 ዓ.ም ጀምሮ ሲቀበል ቆይቷል፡፡ ከአዲስ መደበኛ ተማሪዎች በተጨማሪ ቀደም ሲል የአቅም ማሻሻያ ትምህርታቸውን በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ሲከታተሉ የነበሩና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ያመጡ ተማሪዎችንም ተቀብሏል፡፡