News Detail
የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የስራ ዕድል ፈጠራና ልማት ማዕከል ለመምህራን ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፤
ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት (የካቲት 12/2018 ዓ.ም)
የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ስራ ዕድል ፈጠራና ልማት ማዕከል በስራ ዕድል ፈጠራ ላይ ትከረት ያደረገ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።
ስልጠናውን በንግግር ያስጀመሩት የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ድሪባ ኢትቻ በንግግራቸው እንደገለጹት ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ እንደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ለሀገራቸው እድገት ከፍተኛ ሚና የሚጫወቱ ብቁና ተወዳዳሪ ዜጎችን በማፍራት ረገድ የድርሻውን እየተወጣ እንደሆነ ገልጸው፤ የምንስመርቃቸው ተማሪዎች መቀጠርን እንደ ብቸኛ አማራጭ የሚጠብቁ ተቀጣሪ ሳይሆኑ ስራ ፈጣሪ /Entrepreneur/ እንዲሆኑ መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡
ይህ የስራ እድል ፈጠራ ስልጠና ስራ አጥነትን መቀነስ ብቻ ሳይሆን መምህራን ከመደበኛ ስራቸው ባሻገር የራሳቸውን ተጨማሪ ገቢ ማግኘት የሚችሉበትን ምቹ ሁኔታ የሚፈጠር እና ስልጠናውን መሰረት በማድረግ የተወሰኑ የቢዝነስ መነሻወችን ለመጀመር ትልቅ በር ይከፍታል ብለዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው የራሱን ኢንተርፕራይዝ በማቋቋም መምህራን በሞያቸው ጥናትና ምርምሮችን እንዲሁም የማማከር አገልግሎት በመስጠት የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ከማድረጋቸው ባሻገር ተጨማሪ የገቢ ምንጭ የሚያገኙበት ሁኔታ እንደሚፈጠር ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው ጠቅሰዋል፡፡
ወደ ቢዝነስ የሚቀየረው ዋኛው ነገር ሀሳብ ስለሆነ ሀሳብ ያለው ሰው የራሱን ስራ በመፍጠር ከድህነት በቀላሉ መውጣት ይችላል፤ ስለሆነም ባህላዊ አሰራርን በመቀነስ ዘመናዊና ፈጠራ የታከለበት ስራ በመስራት ራስን ማሳደግ እንደሚቻል ተጠቅሷል፡፡
ፕሬዝዳንቱ ጨምረው እንደገለጹት የትኩረት መስኮቻችን የአካባቢውን ጸጋ መሰረት ያደረጉ በመሆናቸው እና ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ለልማትና ለዕድገት የሚመች ስትራቴጂካዊ ቦታ ላይ ያለ በመሆኑ እድሉን ተጠቅመን በጋራ ከሰራን በሁለንተናዊ መልኩ ዩኒቨርሲቲውን በማሳደግ ሌሎች ግንባር ቀደም ዩኒቨርሲቲዎች የደረሱት ደረጃ ልናደርሰው ይገባል ብለዋል።
ስልጠናውን የሰጡት የብሉማርክ አማካሪ ጅርጅት ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ነስሩ ቃሲም ሲሆኑ ስልጠናው እስከ የካቲት 13/2018 ዓ.ም ድረስ የሚቀጥል ይሆናል፡፡